Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ጉብኝቶች

“ከዚህ ቡኃላ ታላቅ አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታየ፣ ፀሐይን የለበሰች አንዲት ሴት ታየች፣ እርሱዋም ነብሰጡር ነበረች”

ቅዱስነታቸው በፋጢማ የመቁጠሪያይቷ እመቤተኣችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ። - AP

14/05/2017 15:01

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፖርቹጋል ሀገር በሚገኘው ፋጢማ በሚባል ስፍራ የዛሬ አንድ መቶ አመት ገደማ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለሦስት እረኛ ለነበሩ ሕጻናት በተገለጸችበት የመቁጠሪያይቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ለሁለት ቀን የምቆይ መንፈሳዊ ጉዞ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል። በግንቦት 5/2009 ዓ.ም. እረፋዱ ላይ በዚሁ የመቁጠሪያይቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል። በዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እነሆ!

“ከዚህ ቡኃላ ታላቅ አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታየ፣ ፀሐይን የለበሰች አንዲት ሴት ታየች፣ እርሱዋም ነብሰጡር ነበረች” (ራእይ 12፡1)። ከዚያም ኢየሱስ በወንጌል ለደቀ መዝሙሩ “ይችውልህ እናትህ!” (ዩሐንስ 19፡27) አለው። እናት አለን። እውነት ነው የምላችሁ እናት አለን! የዛሬ መቶ አመት ማሪያምን ያዩዋት እረኞች እንደ ገለጹት “በጣም የምታምር” እናት አለን። በዛን ምሽት ዣሽንታ (እ.አ. በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሕጻናት አንዱዋ ናት) ያየችውን ምስጢር ደብቃ መያዝ ስላልቻለች ለእናቷ “ዛሬ እመቤታችንን አየዋት” በማለት ነገረቻት። ሰማያዊቷን እናት አይተዋት ነበር። ብዙ ሰዎች ይህንን ግልጸት ለመጋራት ፈልገው ነበር፣ ነገር ግን ማሪያምን አላዩዋትም ነበር። ቅድስት ድንግል ማሪያም እዚህ የመጣችው ለመታየት ፈልጋ አይደለም። ወደ መንግሥተ ሰማይ በምንሄድበት ወቅት ለዘለዓለም እናያታለን።

የእምቤታችን ትንቢት የምያስጠነቅቀን እግዚኣብሔር የለሽ ሕይወት እንዳንኖር እና ፍጡራን እግዚኣብሔርን እናዳያረክሱት ማስጠንቀቅ ነው። ብዙን ጊዜ የዚህ ዓይነት ሕይወት ወደ ገሀነም እሳት የመምራት አደጋ አለው። ማሪያም የተገለጸችው የእግዚኣብሔር ብርሃን በውስጣችን እንዳለ ልትገልጽ እና ልትጠብቀን ልክ የመጀመሪያው ምንባብ ስነበብ እንደ ሰማነው “ልጇ ግን ወደ እግዚኣብሔር እና ወደ ዙፋኑ ተወሰደ” (ራእይ 12፡5) የሚለውን ለማስረዳት ነው። ከሉቺያ (እ.አ. በግንቦት 13/1917 ዓ.ም. ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሕጻናት አንዱዋ ናት) ታሪክ መረዳት እንደተቻለው እነዚህ ሦስቱ ሕጻናት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግላ ማሪያም በመነጨው የእግዚኣብሔር ብርሃን ተከበው እንደ ነበረ ያትታል። እግዚኣብሔር በሰጣት ብርሃን ጋርዳቸው ነበር። ሁሉም ባይሆኑም እንደ ብዙኅኑ መንፈሳዊ ተጓዥ ምዕመናን ተመኩሮ እና ልምድ የፋጢማዋ ማሪያም ከዚህም በበለጠ ሁኔታ በልብሶቹዋ እንደምትጋርደን ያስተምሩናል። በማሪያም ጥበቃ ሥር ራሳችንን በማድረግ ቅድስት ድንግል ማሪያም ሆይ ኢየሱስን መመልከት እንድንችል አስተምሪን ብለን ልንጠይቃት ይገባል።

ውድ መንፈሳዊ ተጓዥ ምዕመናን እናት አለን። እንደ ሕጻን ልጅ በእርሷ ላይ ዘንበል በምንልባቸው ወቅቶች ሁሉ በኢየሱስ ላይ መሰረቱን ባደረገ ተስፋ እንሞላለን። በሁለተኛነት ሲነበብ የሰማነው ምንባብ “በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የእግዚኣብሔርን ብዙ ፀጋ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በድል አድራጊነት ሕይወት ይኖራሉ” (ሮም 5፡17) ይለናል። ኢየሱስ ወደ ሰማይ ባረገበት ወቅት ከቅድስት ድንግል ማሪያም የነሳውን ሰባዊነታችንን ወደ ሰማያዊው እግዚኣብሔር ወሰደ። እስቲ እንደ አንድ ተዋኒያን ራሳችንን በመቁጠር በእግዚኣብሔር አብ ቀኝ እንደ ተቀመጥን አድርገን ተስፋ እናድርግ። ይህ ተስፋችን ሕይወታችንን ይምራው! ይህም ተስፋ ነው ሁልጊዜም እየማራን የሚገኘው።

እዚህ የተሰበሰብነው በዚህ ተስፋ በመሞላት በባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ልዩ ልዩ ጸጋዎችን የሰጠንን እግዚኣብሔ ለማመስገን ነው። ሁሉም ሰዎች ከማሪያም መጎናጸፊያ በሚመነጨው ብርሃን ሥር በማለፍ ወደ አራቱም የዓለም መዕዘናት አስረጭተዋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ተገልጻላቸው የእግዚኣብሔርን ጥልቅ የሆነ ብርሃን እና እርሱን እንድያመልኩ በልግጸቱ ወቅት ያስተማረቻቸውን የቅዱስ ፍራንቸስኮን እና የቅድስት ዣሽንታን አብነት በመከተል ይኖርብናል። ዘወትር ለኃጢያተኞች በሚያደርጉት ጸሎት እና በመንበረ ታቦት ውስጥ በስውር የሚገኘውን ኢየሱስን ለመቀበል በሚያሳዩት ፍላጎት ምክንያት እግዚኣብሔር በቋሚነት በሕይወታቸው ውስጥ ነበረ።

በእርግጥ እግዚኣብሔር የፈጠረን ለሌሎች የተስፋ ምንጭ እንድንሆን ነው። ሁላችንም የተሰጡንን ኃላፊነቶች ትክክለኛ በሆነ መንገድ እንድንወጣ ይጠይቀናል ያሳስበናልም። በማሪያም ጠባቂነት ትክክለኛው የሆነውንና በፋሲካ የበራውን የአዳኛችን የኢየሱስን የፊት ገጽታ በማሰላሰል ለዓለማችን ዘብ መቆም ይኖርብናል። በዚህም መልኩ ሚስዮናዊ በምትሆንበት ጊዜያት ሁሉ የሚበራውን፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ነጻ፣ ድኽ ነገር ግን በፍቅር የበለጸገች ወጣት እና ውብ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ፊትን በድጋሚ እንድንመለከት ትርዳን ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

14/05/2017 15:01