2017-05-12 17:20:00

የማሪያም ዘፋጢማ ግልጸት ታሪክ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 1917 ዓ.ም. በአሁኑ ሰዓት  የለኢሪያ ፋጢማ ሰበካ በሆነው ክልል በኮቫ ዳ ኢሪያ አቅራቢያ በዚያን ዓመተ ምሕረት የ 10 ዓመት ዕድሜ የነበራት ሉቺያ ደ ኸሱስ ከሁለት የአክስቷ ልጆች ከሆኑት በዚያኑ ዓመተ ምሕረት የዘጠኝና የሰባት ዓመት እድሜ ከነበራችው ፍራንቸስኮ ማርቶና ጃቺንታ ማርቶ ጋር በመሆን በጋራ በጎቻቸውን በዚያ የክልል አቅራቢያ ለግጦሽ አሰማርተው እያሉ ሁሌ እንደሚያደርጉት እንደ ካቶሊካውያን  የመቍጸሪያ ጸሎት ይደግሙና ቤት መሳይ እዛው የሚገኘው ድንጋዮችን በማሰባሰብ እንደ ማንኛው በእድሜያቸው ክልል እንደሚገኙት ህፃናት ሁሉ ለመጫወት ያክል እየሰሩ (በአሁኑ ወቅት የማርያማዊ ዘፋጢማ ባሲሊካ የተገነባበት ክልል ነው) በመጫወት ላይ እያሉ አንድ ትልቅ ብርሃን ይመለከታሉ፡  ሆኖም የመብረቅ ብርሃን ነው ብለው በማመን ከልሉን ለቀው ለመሄድ እየተዘጋጁ እያሉ መልሰው አንዲት ብርሃኗና ንጻቷ እጅግ ከፀሐይ በላይ የደመቀ በእጆቿ ነጭ መቍጽሪያ የያዘች ሴት ካንድ በሉጥ (የዛፍ ዓይነት) ዘፍ (በአሁኑ ሰዓት የግልጸት ቤተ ጸሎት የተገነባበት ሥፍራ ነው) በላይ ሆና ትገለጽላቸዋለች። 

ለሦስቱ እረኞችም የተገለጸች ማርያም ካለ ማቋረጥ እንዲጸልዩ ምክር ለግሳ ወደ ኮቫ ዳ ኢሪያ ለቀጣይ እምስት ወር አሥራ ሦስተኛው ቀን በሚውልበት ዕለት እንዲሄዱ ጥሪ ታቀርብላቸዋለች። እነርሱም በተከታታይ ሰኔ 13 ቀን፡ ሐምሌ 13 ቀን (ነሐሴ 19) ቀን መስከረም 13 ቀንና እንዲሁም ጥቅምት 13 ቀን 1917 ዓ.ም. ወደ ኮቫ ዳ ኢሪያ በመሄድ በተከታታይ 13ኛው ቀን በሚውልበት ዕለት ግልጸቷን ይታደላሉ።

ነገር ግን ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. የዚያ ክልል ከንቲባ በጉዳዩ የተበሳጨ ልጆቹ ያዩት ግልጸት ውሸት ነው ብለው አምነው ለሁሉም እንዲናገሩ በተለያየ መልኩ ያስፈራራቸው ስለ ነበር ወደ ኮቫ ዳ ኢሪያ ሳይሄዱ ቀርቷል። ስለዚህም  በዚያን ወር ማለትም ልክ ነሐሴ 19 ቀን 1917 ከአልኹስትረል ክልል 500 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዶ ቫሊኞስ ክልል በጎቻቸውን አሰማርተው እያሉ ማርያም ትገለጽላቸዋለች።

እ.ኤ.አ. ህዳር 13 ቀን 1917 ዓ.ም. የመጨረሻውና አምስተኛው ግልጸት ሲቀበሉ በክልሉ አርሱም ስለ ግልጸተ ማርያም ለክልሉ ሕዝብ በመሰማቱ ምክንያት ከ 70 ሺሕ በላይ የሚገመት ሕዝብ አብሮአቸው እዛው እንደተገኘና ማርያም በዚያ ግልጸት ወቅትም በሥፍራው ለእርሷ ክብር አንድ ቤተ ጸሎት እንዲገነባ አደራ ትላለች። በዚያኑ ዕለት ያ ሁሉ አብሮአቸው የነበረው ሕዝብ ሦስቱ ሕፃናት ስለ ግልጸት የተናገሩት ያበሰሩትን ሁሉ እውነተኛነቱን ያረጋግጣሉ።

ከዛም ብዙ ቆይቶ ሉቺያ የቅድስስት ዶሮተያ ደናግል ማኅበር አባል ሆና በምንኩስና ጥሪ ውስጥ እያለች እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 1925 ዓ.ም. እንዲሁም የካቲት 15 ቀን 1926 ዓ.ም. በስፐይን በሚገኘው በምትኖርበት የፖንተቨድራ ገዳም እያለች የማርያም ግልጸት ትታደላለች። በመቀጠልም እ.ኤ.አ. ሰነ 13 እና 14 ቀን 1929 ዓ.ም. ሌሊት በገዳም ዘቱይ እያለች ማርያም ዳግም በመገለጥ ጸሎተ መቁጸሪያ ምስጢራት አስተንትኖ በመቅጸሪያ ምስጢራት ንስሐ ሱታፌ በቅዱስ ቁርባን እርሱም በንጹሕ ልብ ማርያም ላይ ለሚፈጸም ሐጢኣት ቀኖናና ሩሲያ ለቅዱስ ንጹህ ልበ ማርያም ትሰጥና ለእርሷ ትወፈይም ዘንድ የሚቀርብ መንፈሳዊ ተግባር ነው ስትል እንድትፈጽመው በአደራ ታዛታለች።

እደሚታወቀውም ይህ የማርያም ትእዛዝ በዚያ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 1917 ዓ.ም. ሦስቱ የማርያም ግልጸት በመታደል ከማርያም ከተቀበሉት አንዱ መልእክትም እርሱ እንደነበርም በምሥጢረ ማርያም ዘፋጢማ በሚል ስያሜ በቤተ ክርስቲያን በታቀበው ሰነድ ውስጥ ተመልክቶ ይገኛል።

ከጥቂት ዓመታት በኋላም ሉቺያ እ.ኤ.አ በሚያዝያና በወርሓ ጥቅምት 1916 ዓ.ም.  ባሉት ጊዚያት ውስጥ በ 1917 ዓ.ም. ከማርያም ግልጸት በፊት አንድ መልእክ ለሦስት ጊዜ ተገልጦላት ሁለቴ በሎካ ዶ ባበጎ በአባቷ የጓሮ የአታክልት ሥፍራ መጀመሪያ በእያንዳንዱ ወር ልክ 13 ቀን ላይ በመገለጥ ጸሎትና ንስሐ እንዲያዘወትሩ አደራ እንዳላቸውን ገልጣ እንደነበርም የግልጸተ ማርያም ዘፋጢማ የታሪክ ማኅደር ውስጥ ተዘግቦ ይገኛል።

ግልጸቱ የታደሉት ማንነት

ሉቺያ ደ ኸሱስ፥ እ.ኤ.አ መጋቢት 22 ቀን 1907 ዓ.ም. በአልኹስትረል በፋጢማ ቁምስና ተወላጅ ስትሆን እ.ኤ.አ. ሰነ 7 ቀን 1921 ዓ.ም. ፖርቶ ከተማ በሚገኘው በቅድስት ዶሮተኣ ደናግል ማኅበር በሚመራው የቪላር ገዳም በመግባት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 1928 ዓ.ም. ጊዚያዊ ማሕላ ከፈጸመች በኋላ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 1934 ዓ.ም. ዓቢይ ማሕላ ፈጽማ እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 1948 ዓ.ም. ወደ ኮይምብራ በመዛወር የቅድስት ተረዛ ቀርመለሳውያን መናንያን ገዳም ውስጥ በመግባት እናቴ ማሪያ ሉቺያ ዘልበ ንጽሕት ድንግል በሚል የመጸውዕ ሥም እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 1949 ዓ.ም. በዚህ ገዳም ውስጥ ዓቢይ መሓላ ፈጽመዋል።

በዚህ ገዳም ውስጥ ስለ ግልጸተ ማርያም የሚያወሳውን ስእልን የቅብ ሥራ ለመከታተል የታዛወሩ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ገዳም ውስጥም እያሉ የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1982፡ በ 1991 ዓ.ም.ና በ2000 መንፈሳዊ ጉብኝት ለመታደል መብቃታቸው የሚያመለክተው የታሪክ ማኅደራቸው አክሎ እ.ኤ.አ. የታቲት 13 ቀን 2005 ዓ.ም. ኮይምብራ በሚገኘው በቅድስት ተረዛ ዘቀርመሎስ ግዳም እያሉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይገልጣል።

ፍራንቸስኮ ማርቶ፥ እ.ኤ.አ. ሰነ 11 ቀን 1908 ዓ.ም. በአልኹስትረል ተወልዶ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 4 ቀን 1919 ዓ.ም. ልክ በ 11 ዓመት እድሜው በሰማያዊ ቤት የተወለደ ሲሆን፡ እ.ኤ.አ. እስከ መጋቢት 13 ቀን 1952 ዓ.ም. በቁምስናው ከነበረበት የመቃብር ሥፍራ በኮቫ ዳ ኢሪኣ ባዚልካ ውስጥ ቅዱስ አጽሙ እንዲያርፍ መደረጉንም የቅዱሳን የታሪክ ማህደር ያመለክታል።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ.ግንቦት 13 ቀን በ 2000 ዓ.ም. ብፁዕና እንዳወጁትም ይታወሳል።

ጃቺንታ ማርቶ፥ የፍራንቸስኮ እህት እ.ኤ.አ. መጋቢት 11 ቀን 1908 ዓ.ም ተወልዳ እ.ኤ.አ. የካቲት 20 ቀን 1920 ዓ.ም. በሊስቦና በደረሰባት ህመም ምክንያትለረዥም ዓመት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየችና። ስቃይዋንና ሕመሟን ሁሉ ለነፍሳት ድህነትና ለሰዎች መለወጥ እንደ መስዋዕት በማቅረብ እንደተቀበለችውና በባሮነ ከሚገኘው የመቃብር ሥፍራ እ.ኤ.አ. መስከረም 12 ቀን 1935 ዓ.ም. ወደ የቤተስቦችዋ የመቃብር ሥፍራ መቃብሯ ከተዛወረ በኋላ እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 1951 ዓ.ም. የወድሟ ቅዱስ ኣጽም ባረፈበት በ ኮቫ ዳ ኢሪያ ባዚሊካ ውስጥ ቅዱስ  አጽሟ እንዲያርፍ ተደርጎ ሲያበቃ እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅዕና እንዳወጁላትም የቅዱሳኑ የታሪክ ማኅደር ያወሳዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.