2017-05-09 09:46:00

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው "እኛ የተጠራነው የዚህን ዓለም ሐሰተኛ የሆኑ ተሞክሮዎችን አውልቀን ለመጣል ነው" አሉ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበቡት የእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተመስርተው አስተምህሮ እንደ ሚሰጡ ይታወቃል። በትላንትና እለት ማለትም በሚያዝያ 29/2009 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቱዋል እና” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከመድገማቸው በፊት ባስተላለፉት አስተምህሮ ገለጹት “በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ ራሱን እንደ መላካም እና በጎቹን እንደ ሚያሰማራ መልካም እረኛ አድርጎ ማቅረቡን” (ዩሐንስ 10፡1-10) አስታውሰው “መልካም እረኝ የሆነው ኢየሱስ የሰው ዘሮች ሁሉ የመዳኛ በር ሆነ” ካሉ ቡኃላ “ምክንያቱም ሕይወቱን ስለ በጎቹ ሲል አሳልፎ ሰጥቶ ስለ ነበር ነው” ብለዋል።

በዚህ ወንጌል ውስጥ (ዩሐንስ 10፡1-10) የተጠቀሰው ኢየሱስ  ሁለት ዓይነት ገጽታዎች አሉት ያሉት ቅዱስነታቸው በእርግጥም ኢየሱስ ራሱን ለአገልግሎት ያዘጋጀ ኃላፊ ነበር ካሉ ቡኃላ “አንድ አስተዳዳሪ ወይም ባለ ስልጣን ለማስተዳደር ሕይወቱን ይሰጣል እንጂ በተቃራኒው ሌሎች ሰዎች ሕይወታቸውን እንዲሰውለት አይጠይቅም” ብለዋል። “መልካም የሆኑ አስተዳዳሪዎችን ግን ማመምን ይችላላል” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም እረኛው የመታዘዝ አዝማምያ የሚያሳዩትን እና እንደ ጓደኛ የሆነ፣ ጠንካራ እና በአብሮነት የሚያምን እንዲሁም የምያጽናና እና የሚያክም መስሎ የተሰማቸውን፣ እረኛ ድምጽ የሚከተሉትን በጎቹን ሁሉ መልካም ወደ ሆነ የግጦሽ ስፍራ ይመራቸዋል ብለዋል።

“ኢየሱስ ለእኛ የሚያሳየን ባሕሪ ይህንኑ ይመስላል” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት ችላ እየተባለ የሚገኝ ነገር ግን በክርስትና የሕይወት ተመኩሮ ውስጥ የሚገኙ መንፈሳዊነት እና ቅርበት የሚባሉ ሁለት ገጽታዎች እንደ ሚገኙ የገለጹት ቅዱስነታቸው እነዚህም ሁሉት ገጽታዎች ለየት ባለ መንገድ ከኢየሱስ ጋር የለንን ግንኙነት እንደ በግ እና እንደ መልካም እረኛ እንደ ሆነ እንዲሰማን ያደርጋል ብለዋል።

አንድአንዴ እምነታችንን ምክንያታዊ ለማድረግ በምንሞክርባቸው ወቅቶች ሁሉ የመስቀሉን ማህተም ትጉም፣ የሚስበውን እና የሚያነቃቃውን መልካም እረኛ የሆነውን የኢየሱስን ድምጽ እንዘነጋለን ብለዋል። ይህም የኤማውስ መንገደኞች የነበሩት ደቀ መዛሙርት ተመኩሮ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ከሙትን የተነሣው ጌታ ሲናገር በሰሙት ወቅት ልባቸው ይቃጠል እንደ ነበረው ዓይነት ነው ብለዋል።

“በኢየሱስ እንደ ተወደድን የሚሰማን ከሆነ ያ በጣም አስደሳች የሆነ ተመኩሮ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው “በኢየሱስ እንደ ተወደድኩኝ ይሰማኛል ወይ? በማለት ራሳችሁን ጠይቁ ካሉ ቡኃል እኛ ለእርሱ ባዳዎች ሳንሆን ነገር ግን ጓደኞች ወይም ደግሞ ወንድሞቹ ነን ብለዋል። ይሁን እንጅ የመልካም እረኛውን ድምጽ ሁሌ አጣርቶ መለየት ቀላል ነገር አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው ሁል ጊዜ የተለያዩ የጫጫታ ድምጾች እኛን የመረበሽ አደጋ ስላላቸው ማስተዋል ይጠበቅብናል ብለዋል።  ዛሬ እኛ የተጠራነው የእዚህን ዓለም ሐሰት የሆኑ ተመኩሮዎች አውልቀን በመጣል፣ ለየት ባለ ሁኔታ እርግጠኛና ለሕይወታችን ትርጉም የሚሰጠውን  ከሙታን የተነሳውን ኢየሱስን መከተል ይኖርብናል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተልም በዚህ በዓለማቀፍ ደረጃ ለጥሪ ጸሎት በምናደርግበት በዛሬው ቀን (ሚያዝያ 29/2009 ዓ.ም.) “ጌታ መልካም እረኞችን እንዲልክልን” መጸለይ ያስፈልጋል” ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.