2017-05-09 13:33:00

"መንፈስ ቅዱስ ተዐምራትን ይሠራል, አዳዲስ ነገሮችንም እንዲከሰቱ ያደርጋል” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 30/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ሁል ጊዜ መንፈስ ቅዱስን እንድትቃወሙት የሚያደርጋችሁን ኃጢያት አስወግዳችሁ  ለእግዚኣብሔር አስገራሚ ክስተት ራሳችሁን ክፍት አድርጉ” ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በተነበበው እና ከሐዋሪያት ሥራ 11፡1-18 ላይ በተጠቀሰው ሐዋሪያው ጴጥሮስ ከአረማዊያን ወገን ወዳመኑ ሰዎች ቤት ስልምን እንደገባ ማስረዳቱን በሚያወሳው ታሪክ ላይ ተመርኩዘው የነበረ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ቤተ ክርስትያን እና ክርስትያኖች ሁል ጊዜ ወደ ፊት እንዲጓዙ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው በለዋል።

“መንፈስ ቅዱስ ተዐምራትን ይሠራል አዳዲስ ነገሮችንም እንዲከሰቱ ያደርጋል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ጉዳይ በግልጽ አንድ አንድ ሰዎችን ፍርሃት ውስጥ ይከታቸዋል ብለዋል።

መንፈስ ቅዱስ የእግዚኣብሔር ስጦታ ነው፣ ይህም ስጦታ ሁል ጊዜ የሚመጣው በአዳዲስ ነገሮች በምያስገርመን እግዚኣብሔር አማካይነት ነው። የክስተት አምላክ ነው. . .ለምን? ምክንያቱም እርሱ ሁሌም ነዋሪ የሆነ፣ በእኛ ያደረ፣ ልባችንን የምያንቀሳቅስ፣ በቤተ ክርስትያን የሚኖር እና ከእኛ ጋር የሚራመድ፣ በዚህም ጉዞዋችን የሚያስገርመን አምላክ ስለሆነ ነው። ዓለምን የመፍጠር ክህሎት ያለው እርሱ ብቻ ነው፣ በእየ እለቱ አዲስ ነገር የመፍጠር ክህሎት ያለው እርሱ ብቻ ነው። ሁሌም የምያስገርመን አምላክ ነው

ይህም አሉ ቅዱስነታቸው ይህ ነገር ብዙን ጊዜ ልክ ጴጥሮስ “አረማዊያን የእግዚኣብሔርን ቃል በመቀበላቸው የተነሳ” ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ሳይቀር ወቀሳ እንደ ደረሰበት ዓይነት “ችግር” ይፈጥራል ያሉት ቅዱስነታቸው ለእነርሱ ሐዋሪያው ጴጥሮስ የፈጸመው ተግባር በጣም ብዙ የሚባል ርቀት የተጓዘ ስለመሰላቸው እና በዚህም ጉዳይ “ተሰናክለው” “አንተ የቤተ ክርስቲያን አለት የሆንክ ጴጥሮስ! ወደ የት ነው? እየመራህን ያለኸው? እስከ ማለት ደርሰው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ለዚህ የተቃውሞ ቃል ጴጥሮስ ያየውን ራእይ በማጣቀሻነት በመተረክ መልሶ እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው “ይህም “እግዚኣብሔር ያሳየው ምልክት” ይህንን ጠንካራ ውሳኔ እንዲውስን እንደረዳውም ጨምሮ መግልጹንም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። “ጴጥሮስ የእግዚኣብሔርን አስገራሚ ክስተት መቀበል ችሎ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩ በተከሰተው ብዙ አስደናቂ ነገሮች በመታግዝ የገጠሙትን ትግዳሮቶች ሁሉ “ከሌሎች ደቀመዛሙርት ጋር በመሆን፣ በጉዳዮቹ ላይ በመነጋገር ጌታ በሚፈልገው መልኩ ወደ ፊት ለመጓዝ ስምምነት ላይ ደረሰው እንደ ነበረም” ጨምረው ገልጸዋል።

ከነብያት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ፣ መንፈስ ቅዱስን የመቃወም አባዜ ሁልጊዜም ነበር። ይህም መንፈስ ቅዱስን መቃወም ነው።  እስጢፋኖስ የሸንጎ አባላትንእናንተ እና አባቶቻችሁም ሳይቀሩ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁበማለት ከሶዋቸው የነበረው በዚሁ ተመስሳይ በሆነ ኃጢያት ነበር። አይሆንም! ሁልጊዜ እንዲህ ነበር የተሰራው በዚሁ መልኩ መቀጠል አለበት። ጴጥሮስ አዲስ ነገር እንዳይፈጥር፣ እንዲረጋጋም  ነገረውት ነበር. . .ማደንዘዣ ወስዶ ይህንን መቅበዝበዙን እንዲያስታግስ መከሩት. . .የእግዚኣብሔር ድምጽም በዚሁ መልኩ ተዘጋ። በመዝሙረ ዳዊት እግዚኣብሔር ለሕዝቡእንደ አባቶቻችሁ ልባችሁን አታደንድኑብሎ ነበር።

የቅዱስነታቸው ስብከት በቀጣይነት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በተነበበው እና ስለ መልካም እረኛ በሚተርከው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ጌታ መቼም ቢሆን ልባችንን ደንዳና እንዳናደርግ ይጠይቀናል ብለዋል። “ጌታ ከእኛ የሚፈልገው የእርሱ ያልሆኑ ሌላ መንጋ እንዳለ እንድንረዳ ነው” በማለት ስብከትቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው “ነገር ግን አንድ መንጋ እና አንድ እረኛ ብቻ እንደ ሚያስፈልግም ጨምሮ መገለጹን አስታውሰዋል። እነዚህ አረማዊያን የሚባሉ ሰዎች ተወግዘው እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ወደ አማኝነት በተቀየሩበት ጊዜም ሳይቀር እንኳን “እንደ ሁለተኛ ደረጃ ወይም አናሳ አማኞች ተደርገው መቆጠራቸውን አስታውሰው፣ ምንም እንኳን ይህ በይፋ የተነገረ ጉዳይ ባይሆንም ቅሉ ነገር ግን በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነበር” ብለዋል።

ሁል ጊዜ የሚሠራበት አሰራር ይህ ነውየሚለው ሀረግ መንፈስ ቅዱስን ይቃወማል ብሎም በሩን ለመንፈስ ቅዱስ ይዘጋል፣ ነጻነትን እና ደስታን ይገድላል። ከእኛ ቀድሞ በመጓዝ ቤተ ክርስትያንን ወደ ፊት እንድትጓዝ የሚያደርገውን ለመንፈስ ቅዱስ ያለውን ተአማኝነት ይገድላል። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ከመንፈስ ቅዱስ ወይም ደግሞ ከዓለም ወይም ከሰይጣን መንፈስ መምጣት አለ መምጣቱን እንዴት ማወቅ እንችላለን? የሚል ጥያቄ ልናነሳ እንችል ይሆናል። ይህንን ለመለየት የፈለገ ሰው መሳሪያ የሆነውንና እያንደንዱ መንፈስ የሚሰጠንን  ትክክለኛ ውሳኔ ያምደርግ ፀጋ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይገባል።አንድ ሰው በእያንዳንዱ ሁኔታ እንዴ ነው ትክክለኛ ውሳኔ ማድረግ የሚችለው? መልሱም ደቀ መዛሙርቱ እንዳደረጉትመሰብሰብ፣ መወያየት እና መንፈስ ቅዱስ የሚጠቁመንን መንገድ ማየትሊሆን ይገባል። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ፀጋ ያልተሰጣቸው ሰዎች ወይም ደግም ይህ ይሰጣቸው ዘንድ የማይጸልዩ ሰዎች ግን እስከ ዛሬ ቀን ድረስ ዝግ ሆነው ይቀራሉ።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ጠቀሱት ክርስትያኖች ሊለማመዱት ከሚገባቸው ነገሮች መካከል “ትክክለኛ ውስኔ ማድረግ መማር፣ አንዱን ነገር ከሌላው የመለየት ችሎታ ባዳበር፣ አዳዲስ የሆኑ ነገሮችን መርምሮ ማወቅ፣ ከእግዚኣብሔር የሚመጣውን አዲስ ነገር ወይም ከዓለም እና ከሰይጣን መንፈስ በሚመጣው ታድሶ” መካከል ያለውን ትክክለኛ ልዩነት ለይቶ ማወቅ መማር ይኖርባቸዋል ብለዋል። “እምነት” በፍጹም የሚቀየር ነገር አይደለም በማለት በጽኖት የተናገሩት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በአንጻሩ እምነት የሚሰፋ እና ወደ እንቅስቃሴነት የሚያድግ ነው ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን አሳባቸውን ለማስረጽ በማሰብ በቀድሞዎቹ ዘመናት ከነበረው የሌሪንሱ መነኩሴ ከቅዱስ  ቪንሰንት አባባሎች መካከል “የቤተ ክርስቲያን እውነታዎች በወደፊቱ ነገሮች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ በእየ አመታቱ ይጠናከራሉ፣ በየጊዜያቱ ያድጋሉ፣ በጊዜያት ውስጥ ጥልቀትን ያገኛሉ፣ በጊዜያት እና በአመታት ብዛት እየጠነከሩ እና እየሰፉ በመምጣት ከቤተ ክርስትያን እድሜ ጋር ታዋቂነትን ያገኛሉ” የሚለውን ከጠቀሱ ቡኃላ ስህተት እንዳንሰራ እና በማያንቀሳቅስ ወጥመድ ውስጥ ገብተን እንዳንቀር የምያደርገንን ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን የምችልበትን ፀጋ ይሰጠን ዘንድ እግዚኣብሔርን ልንለምነው ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.