2017-05-08 16:51:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች፥ ከወገኛነት (ተመጻዳቂነት)ና ከክህነታዊ ፈሪሳዊነት ታቀቡ


“ለመመስረቅ (ለይቶ ለማስተዋል እንዲቻል) መታነጽ እንጂ እራስን በገታራ ሕግና በአንድ ፍጹም ምስያ ነጻነት በስተ ጀርባ እራስን አለ መደበቅ”  ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እነዚያ በቅዱስ ኢግናዚዮስ ያማማር ሥልት መሠረት ባደረገ የክህነት ሕንጸት የሚሰጣቸው ጳጳሳዊ የካምፓኖ ዘፖሲሊፖ ዘርአ ክህነት ተማሪዎችን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን ሲሆን።

መኖራችን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያለው አቢይ እቅድ ለይቶ ለማወቅ የሚግባኝን ከሚለው አቃሎና አሳንሶ መኖር ከሚለው ልግስና የለሽ ከሆነው ከቆንቋናነት አመክንዮ መላቀቅ ያስፈልጋል።

ከኢየሱ ጋር የጠበቀ ግላዊ ወዳጅነት የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግና ወደዚሁ መንግሥት የሚመራውን መንገድ መመስረቅ (ለይቶ በማስተዋል መከተል) ያስፈልጋ። ይኽ ደግሞ የቅዱስ ኢግናዚዮስ የአማማር ሥልት የሚያመለክተው ሃሳብ ነው። በሕግ ላይ የሙጥኝ የማለቱ በሕግ ግትር ከማለትና ባንጻሩም ከቸልተኝነ እራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ከወገኛነት ተመጻዳቂነት ከፈሪሳዊ ክህነታዊነት በጠቅላላ ድርብ ህይወት ከመኖር የሚገባኝ ከሚለው ልግስና ከማያውቀው የቆንቋናነት አመክንዮ መራቅ ያስፈልጋል። እንዲህ ስናደርግ ብቻ ነው እያንዳንዳችን እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው እቅድ ለመለየት ማለትም ለመመስረቅ እንችላለን፡

ከዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር መገናኘት እጅግ ደስ እንደሚያሰኛቸው በዚህ አጋጣሚ የገለጡት ቅዱስ አባታችን፥

“የሰበካ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤትና ተማሪዎች መካከል ውስጠ ግኑኝነት ሊኖር ይገባል፡ ውስጠ ሰበካዊ ግኑኝነት፡ ይኽ በቅዱስ ኢግናዚዩስ የሕንጸት ስልት መሠረት ያደረገው ጳጳሳዊ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤተ ከተለያዩ ሰበካዎች የተወጣጡ ወጣቶች የሚማሩበት ነው፡ ስለዚህ ለውስጠ ሰበካዊ ግኑኝነት ተጨባጭ አብነት ነው።”

ይኽ የሰበካ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር ሥር የሚተዳደርና በኢጣሊያ ብቸኛ ትምህርት መሆኑ ገልጠው በሌሎች አገሮች ብዙ መኖራቸውንም አስታውሰዋል።

“ምንም ይሆን በማን ይመራ ሁሌ ኢየሱስን ከመፈለግ የእርሱ ወዳጅነትና ጓደኝነትን ከመፈለግ መቦዘን የለብንም። ሰብአዊነታችንን እንዲታደስ ከገታራ ምሁርነት፡ ደረቅ ከሆነው እውቀት እርሱም ሰብአዊነትን ከማይነካና ከማይለወጥ፡ መዝገበ ቃላተኛ ከሆነው ምሁራዊነትን መጠበቅ ወይም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ጥሪ ከጌታ ጋር ባለን ፍቅር የሚያልፍ የፍቅር ጉዞ ነው፡ ይኽ ጉዞ ልንከተለው የሚገባንን ጥሪ የሚያመላክት የለውጥ ሕይወት ነው”

ውድ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች፥ የሕይወታችሁን እውነታ ፊት ለፊት ለመግጠም ለነግሮች ሁሉ በስም ለመጥራት ለተስፋ ለእውነት ለሌሎች በተለይ ደግሞ ለሕንጸት አለቆች ገዛ እራሳችሁን ክፍት ለማድረግ ከተመጻዳቂነት ከፈሪሳዊ ክህነታዊነት ካስመሳይነት ከድርብ ሕይወት ከመኖር ሁነት እራሳችሁን ለማላቀቅ አትፍሩ ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው በሕንጸት ጎዳና ማእከልነት ያለው ቅዉም ነገር ምስረቃ ወይንም መንገድ የመለየት ብቃት ነው፡ ካህን ሕዝበ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ድምጽ ለይቶና አውቆ እግዚአብሔር እንዲከተል የሚመራና የሚንከባከብ ነው፡ በዚህ ብዙ ሕዝብና ብዙ ጫጫታ ባለበት ሥፍራ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለይቶ ለመስማት ልባም ጆሮና ልባም ልብ ያስፈልጋ። በዚህ ብዙህነት ባህላዊና ሃይማኖታዊ ኅብረአዊነት እጅግ በጎላበት ኅብረ መልእክት በተስፋፋበት ዓለም ሕዝበ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ድምጽ እንዲለይ ማድረግ የካህኑ የእረኝነት ሓላፊነት ነው። ስለዚህ ካህኑ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ጥልቅ ትውውቅ ጥብቅ ትሥሥር ያለው ሆኖ እራሱን ቃለ እግዚአብሔር አማካኝነት ለማወቅ የሚተጋ በቃለ እግዚአብሔር የበረታ፡ ለገዛ እራሱ እውነትን የሚነግር እውነትን የሚናገር መሆን አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመ ት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ምስረቃዊ ሂደት (የመለየት ማስተዋል ብቃት) ጽናት የሚጠይቅ ምርጫ ነው፡ ፊት ለፊት ከሚቀመጡት አቀበት የሌላቸው የሚመስሉ ምቹ፡ ሕግ ብቻ እንዲጠብቀኝ በሚል በሕግ ላይ ገታራ መሆን ወይንም ደግሞ ቸልተኝነት ሁሉን ነገር እንደ ሚሆነው ይሆናል እየተባለ በልማድ ከመኖር ይልቅ ከዚህ ዓይነቱ ፈተና ለመላቀቅ አስተዋይ መሆን ያስፈልጋል፡ ይኽ ደግሞ ምስረቃዊነት ይባላል። ስለዚህ ተደላድየ የምኖርበት መስሎ ከሚታየኝ ዓለምና ቅድመ ፍርድ ሁሉ ተላቆ ገዛ እራስ ለእግዚአብሔር እቅድ ክፍት ማድረግ ማለት ነው። የሚናገረኝን የሚጠራኝን በእኔ ላይ እቅድ ያለው እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለው እቅድ ምን መሆኑ ለሚያሳውቀኝ ለጠሪው እግዚአብሔር ክፍት የሚያደርገኝ መንገድ ነው”

በቅዱስ ኢግናዚዮስ አገባብ መሰረት ወደ ክህነት መጓዝና ለክህነት ጥሪ መሰናዳት ማለት ገዛ እራስ ለእግዚአብሔር መንግሥት ማነጽ ማለት ነው። በእራስ ብቃት በግል ድሎት ተመቻችቶ መኖር ሳይሆን ዘወትር እግዚአብሔርን በብቃትና በትጋት ለማገልገል በሚለውና በሚሰጠው አገልግሎትና እግዚአብሔርን በመፈለጉና ፈልጎ ለማግኘት በሚደረገው ጉዞ ያለ መርካት መኖር ማለት ነው፡ መንፈስን ማስፋትን ማሳደግ የእግዚአብሔር ፍቅር ለመቀበል ተቀብሎ ለማስተናገድ ያስችላል። ስለዚህ ማስተዋል ማለት ፍቅርን ለማስተናገድ መሰናዳት ማለት መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችን፥

“ዘወትር የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ እንጂ በቁጥብነትና ለእራስ በመሳሳት ለጋስ ካለ መሆን የሚኖር ተራነትን የሚል ሕይወት ባለ መኖር እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያለውን እቅድ ለይቶ ለማወቅና እቅዱን ለመኖር አለ መፍራ፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት መፈለግ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍትህ መፈለግ ማለት ነው፡ እንዲህ ሲሆን በማሕበራችን በምንኖርበት ኅብረተሰብ በሚኖረን ግኑኝነት ሁሉ ፍትሕ በመኖር ከተሞቻችን በእግዚአብሔር መሓሪውና ቅን ፍቅር እንዲለወጥ የድኾችና የተገፉትን ድምጽ መስማትና ስለ እነርሱ ጠበቃ መሆን ማለት ነው” 

እንዳሉ የገለጠው ቃለ ምዕዳን የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሉ፥  ቅዱስ አባታችን የለገሱት፥

“ውስጣዊ ነጻነት ዘወትር መሻት፡ ይኽ ደግሞ ከባድ መሰላል ነው፡ ምክንያቱም ሰይጣን በኪስ ይገባልና። ውስጣዊ ነጻነት ሲኖርህ የሃብት አጠቃቀም ስልቱም ይሆርሃል። የገንዘብና ግኡዝ ሃብት ተገዥ ወይንም ደግሞ ባርያ ከመሆን ያድናል። ምክንያቱም ብኩንነት ትዕቢትና ትምክህት የሚያስከትል ትልቅ ፈተና ነው፡ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ኢየሱስ በመምሰል የሚያድጉ ከኢየሱስ ጋር የጠበቀ የግል ጓደንነትና ወዳጅነት ያላቸው ለድኾች ልዩ ትኩረት የሚሰጡና የሚያፈቅሩ መሆን ይገባቸዋል”

በማለት አጠቃለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.