Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ሥርዓተ አምልኮ \ የእሁድ ስብከቶች

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስብከታቸው "እናንተ እረኞች እንጂ የመንግሥት አገልጋይ ቄሳውስት አይደላችሁም" ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ለዓሥር የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች የክህነት ማረግ በሰጡበት ወቅት። - REUTERS

08/05/2017 16:30

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 29/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ የሮም ሀገረ ስብከት አባል ለሆኑ ለዓሥር የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች የክህነት ማረግ መስጠታቸው ታወቀ። በተመሳሳይ መልኩም በእለቱ ዓለማቀፍ የጥሪ ቀን በጸሎት ተከብሮ ማለፉ የታወቀ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሁል ጊዜ ርኅሩዎች ሁኑ፣ ቀልል ያለ ቋንቋ በመጠቀም የሰዎች ልብን ንኩ፣ እናንተ እረኞች እንጂ የመንግሥት አገልጋይ ቄሳውስት አይደላችሁም” ማለታቸውም ተገልጹዋል። በእለቱ ቅዱስነታቸው ያሰሙት ስብከት እንደ የአውሮፓዊያኑ የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በአራተኛው የፋሲካ ሳምንት ሰንበት በተነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ፣ በተለይም ደግሞ በእለቱ በተነበበው “እኔ መልካም እረኛ ነኝ” በሚለው የወንጌል ቃል ላይ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችልዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

እናንተ በኢየሱስ የተመረጣችሁት “የእርሱን የግል አስተምህሮ፣ የክህነት ሕይወቱን እና የመልካም እረኛነቱን ተልዕኮ ለማስቀጠል ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “በክርስቶስ የተመረጣችሁት ማንኛውንም ዓይነት ሥራ ለመሥራት ሳይሆን እነዚህን ቀደም ሲል የጠቀስኩዋቸውን አገልግሎቶች ለማከናወን ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው በእለቱ የማዕረገ ክህነት ለተቀበሉ 10 ካህናት አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት “የእግዚኣብሔርን ቃል በሚገባ አንብቡ አሰላስሉትም፣ በሚገባ ለማመን ይረዳችሁ ዘንድም በሕይወታችሁ ተለማመዱት፣ በእመንት ያገኛችሁትን አስተምሩ፣ ያስተማራችሁትንም በሕይወት ለመኖር ሞክሩ” ብለዋል።

“ስብከታችሁን በጣም በረቀቀ መልኩ አታድርጉ፣ ቀለል ባለ መልኩ የሰዎችን ልብ በሚነካ መልኩ አድርጉ፣ በዚህ መልኩ የሚደረግ ስብከት የሕይወት ምግብ ይሆናል” በማለት አጽኖት ሰጥተው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም በጥልቀት የምትኖሩት ሕይወት ለአማኞች የደስታ ምንጭ እና ድጋፍ ይሆናቸዋል” ካሉ ቡኃላ ነገር ግን በመልካም የሕይወት ምሳሌ ያልተደገው ቃል ምንም ትርጉም አይኖረውም ብለዋል።

“ሁለት ዓይነት ሕይወት የመኖር አባዜ ያላቸው ካህናት መኖራቸው በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚታይ ክፉ የሆነ በሽታ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ሰለዚህም “የምትሠሩትን ነገር እወቁ፣ የምታከናውኑትን ሥርዓተ አምልኩ ምሰሉ” በማለት አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

“ብዙ የነገረ መልኮት ትምህርት የተማረ እና አንድ ወይም ሁለት ምናልባትም ሦስት ጊዜ በተለያዩ ትምህርቶች አተመረቀ አንድ ካህን፣ የኢየሱስን መስቀል መሸከም ካልተማረ ምንም ጥቅም የለውም” ያሉት ቅዱስነታቸው “ምንላባት አንድ ጥሩ ምሁር ወይም ጥሩ አስተማሪ ሊሆን ይችል ይሆናል ነገር ግን ጥሩ ካህን አይደለም” ብለዋል።

“እባካችሁን ሁል ጊዜ ምሕረት አድራጊዎች ትሆኑ ዘንድ በክርስቶስ  እና በቤተ ክርስትያንም ስም ሆኜ እተይቃችዋለሁ!”  በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናንተም ራሳችሁ መሸከም የማትችሉትን  ክብደት በአማኞች ላይ አትጫኑ ካሉ ቡኃል እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎችን ኢየሱስ ግብዞች በማለት አውግዙዋቸው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

የካህናት ዋንኛው ተግባራቸው ሊሆን የሚገባው “ምንም እንኳን አሰልች እና አድካሚ ቢሆንም “የታመሙ ሰዎችን ለመፈለግ መጓዝ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “በበሽተኞች ውስጥ ሆኖ የሚሰቃየውን የክርስቶስን ሥጋ በዝምታ አትመልከቱ፣ የበሽተኞችን የሚሰቃየውን አካላቸውን በምትነኩበት ጊዜያት ሁሉ ይህ ተግባራችሁ ያነጻችዋል ወደ ክርስቶስም እንድትቀርቡ ያደርጋችዋል “ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “በመከራዎችም ውስጥ ስትገቡ እና የግል ኃጥያታችሁ ሳይገባችሁ በሚቀርበት ጊዜያት ሁሉ ክርስቶስን በማገልገል በሚገኘው ደስታ የተሞላችሁ ሁኑ እንጂ ሐዘንተኞች አትሁኑ!” ካሉ ቡኃላ “ለማገልገል እንጂ ለመገልገል ያልመጣውን” የመልካም እረኛን ምሳሌ መላበስ ያስፈልጋል ካሉ ብለው “እባካችሁን እናንተ ጌቶች፣ የመንግሥት አገልጋይ ቄሳውስቶች አይደላችሁም ነገር ግን እረኞች ናችሁ፣ የእግዚኣብሔር ሕዝብ እረኞች ናችሁ” ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

08/05/2017 16:30