Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ሥርዓተ አምልኮ \ የእሁድ ስብከቶች

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስብከታቸው "እግዚኣብሔር ድንጋይ የሆነውን ልብ ወደ ሥጋ ልብ የመቀየር ብቃት አለው" ማለታቸው ተገለ።

ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት።

04/05/2017 11:34

“ከሕግ ውጭ የሚሆኑትን ሰዎች ሁሉ የሚያወግዘውን የደነደነ ልብ እግዚኣብሔር ያለሰልሳል”። ይህንን ዐረፍተ ነገር የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዚያ 22/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብክ የተወሰደ ነው። “የእግዚኣብሔር ርኅራኄ የደነደነውን የድንጋይ ልብ አውጥቶ በምትኩ በሥጋ ልብ እንደ ሚተካው ማወቅ ያስፈልጋል” ብለዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

“ቅዱስ ኢስጢፋኖስ እንደ ኢየሱስ ለእግዚብሔር ታዛዥ መሆኑን መስክሮ አልፏል” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ታዛዥነቱ ለስደት እና ለመከራ ዳርጎት እንደ ነበረም ጨምረው ጠቅሰዋል። በእለቱ ከሐዋሪያት ሥራ 7፡51 ጀምሮ በተነበበው እና ስለ ሰምዕቱ እስጢፋኖስ በሚገልጸው የመጀመሪያው ምንባብ ላይ ትኩረታቸውን ባደረገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች ለእግዚኣብሔር ታዛዥ መሆናቸውን መግለጽ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

“ቅዱስ እስጢፋኖስን ይወግሩት የነበሩ ሰዎች የእግዚኣብሔርን ቃል አልተረዱትም ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህም ምክንያት እስጢፋኖስ ወጋሪዎቹን እናንተ “አንገታችሁ የደነደነ እልኽኞች! ልባችሁ የተደፈነ ጆሮአችሁም የማይሰማ” ብሎዋቸው እንደ ነበር ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህም የእስጢፋኖስ አባባል እናንተ አረመኔዎች ከማለት ጋር ይስተካከላል ብለዋል።

“የእግዚኣብሔርን ቃል በተለያዩ መንገዶች እና እውነታዎች ውስጥ አስቀምጠን ለመረዳት መሞከር ያስፈልጋል” ያሉት ቅዱስነታቸው ለምሳሌም በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 24 ላይ የተጠቀሰው የኤማውስ መንገደኞች ታሪክ ላይ እንደ ተጠቀሰው የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከነበሩት መካከል ሁለቱ ኢየሱስ ከሞተ ቡኃል በድጋሚ ከሞት አይነሳም በሚል ስጋት ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ተለይተው ወደ ሀገራቸው ወደ ኤማሁስ በሚጓዙበት ወቅት ኢየሱስ በመንገድ ተገልጾላቸው እንደ ነበረ አውስተው ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን  “እናንተ የማታስተውሉ” ብሎዋቸው እንደ ነበረ አስታውሰዋል። “ይህም ኢየሱስ የተናገረው ቃል እስጢፋኖስ ከተናግረው ቃል ጋር በንጽጽር ሲታይ በጣም ከባድ የሚባል ቃል አልነበረም” ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ የኤማውስ መንገደኞች ስላልገባቸው እና ችግሮችን መጋፈጥ ስላልፈለጉ፣ እንዲሁም ፍርሃት ስለነበራቸው የፈጸሙት ተግባር ነበር እንጂ ክፉ ሰዎች አልነበሩም ራሳቸውንም “ለእውነታ ክፍት” ያደረጉ ሰዎች እንደ ነበሩም ጨምረው ገልጸዋል።

ምክንያቱም አሉ ቅዱስነታቸው ሐሳባቸውን ለማስረጽ በማሰብ “ምክንያቱም እነዚህ ሁለት የኤማውስ መንገደኞች ኢየሱስ በተገለጸላቸው ወቅት ልባቸውን በመክፈት ቃሉ በውስጣቸው እንዲገባ በመፈቀድ ልባቸውን እንዲያናውጥ ፈቅደውለት እንደ ነበር” በማለት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በተቃራኒው እስጢፋኖስን ሲወግሩት የነበሩ ሰዎች ግን “በጣም ቁጡ ነበሩና ማዳመጥ የማይፈልጉ ሰዎች ነበሩ” ይህም የልባቸውን ደንዳናነት ያሳያል ብለዋል።

“ማንኛውም የተዘጋ ልብ መንፈስ ቅዱስ ዘልቆ እንዳይገባ ያግዳል” ያሉት ቅዱስነታቸው “በልባቸው ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ አልሰጡትም ነበር፣ ነገር ግን የዛሬው የመጀመሪያ ምንባብ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ሁሉንም ነገር ተረድቶ ሥጋ ለለበሰው ቃል ታዛዥነቱን መሰከረ ይህንንም ምስክርነት የፈጸመው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተ” እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። ስለዚህም አንድ የተዘጋ እና የደነደነ ልብ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲገባ የማይፈቅድ አንድ አረመኔ የሆነ ልብ እርሱ በራሱ ሙሉ መሆኑ ይሰማዋል” ብለዋል።

እኛ እነዚህን የኤማውስ መንገደኞች የነበሩትን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርትን እንመስላለን ምክንያቱም “ከብዙ ጥርጣሬያችን እና ኃጢያታችን የተነሳ ከኢየሱስ መስቀል ለመራቅ እንፈልጋለን፣ ከፈተናዎችም ለመሸሽ እንሞክራለን” ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ልባችንን ያሞቅልን ዘንድ ቦታ ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ “በሕግ አግባብ ብቻ መሄድ ይገባናል ብለው ሙጭጭ በማለት ኢየሱስን መስማት የማይፈልጉ ሰዎችን” እስጢፋኖስ “መጥፎ የሆኑ ሰዎች እንደ ሆኑ” ተናግሮ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን ስታመንዝር የተገኘችሁን ኃጢያተኛ የነበረችሁን ሴት ምሳሌ በማጣቀሻነት በመጥቀስ እንደ ገለጹት ”እያንድ አንዳችን በኢየሱስ እና የድንጋይ ልብ በነበራቸው ሰዎች ምክንያት ለፍርድ በቀረበችሁ አማንዝራይቷ ሴት ውይይት መኃል እንገኛልን” ካሉ ቡኃላ እቺን አመንዝራለች የተባለችውን ሴት በድንጋይ ሊወግሩዋት ለፈለጉ ሰዎች ኢየሱስ በቅድሚያ “ውስጣችሁን ተመልከቱ” ብቻ ብሎ መልሶላቸው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ “ዛሬ ይህንን የኢየሱስን ርኅራኄን እንምለከት፣ ይህንን የታዛዥነት ምስክርነት እንመልከት፣ ይህም ታላቅ ምስክርነት ነው፣ ነብሱን ለእኛ አሳልፎ የሰጠው ኢየሱስ ምንም እንኳን ኃጢያተኞች እና ደካሞች ብንሆንም ቅሉ እግዚኣብሔር ለእኛ ያለውን ርኅራኄ ያሳየናል” ብለዋል። በእዚህ በኢየሱስ እና ስታመነዝር የተገኘችሁን ሴት ለፍርድ ባቀረቡት  ደንዳና፣ ሙጭጭ ያለ፣ ለሕግ ብቻ የተገዛ እና ከሕግ ውጭ የሆኑትን በሚያወግዝ ልብ በነበራቸው ሰዎች መካከል በተደረገው ውይይት ውስጥ ራሳችንን በማስገባት አምላክ ልባችንን በፀጋው ያለሰልሰው ዘንድ መጠየቅ ይገባናል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

04/05/2017 11:34