2017-05-01 15:36:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "እግዚኣብሔር ለአማኞች የፈቀደላቸው የጽንፈኝነት ዓይነት የፍቅር ጽንፈኝነት ብቻ ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ የሁለት ቀን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። በሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም. በግብፅ የሰዓት አቆጣጠር 10፡00 ላይ በግብፅ የአየር ኃይል ስታድዬም ተገኝተው 30 ሺ ለሚጠጉ የካቶሊክ ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴ ማድረጋቸው መዘገባችን ይታወሳል። ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ለምዕመናን የሚፈቀድላቸው ጽንፈኝነት  የፍቅር ጽንፈኝነት ብቻ ነው” ማለታቸው ተገለጸ። ይህ ቅዱስነታቸው ያስራጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በግብፅ በሚኖሩ የካቶሊክ ማህበረሰብ በጣም ከተጠበቁት ጊዜያት አንዱ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በሌሊት ወደ ስታዲዬም በመንጎድ ጥብቅ የደኅንነት መቆጣጠሪያዎችን በማለፍ ይህንን ታላቅ እና ታሪካዊ ክስተት ለመካፈል መገኘታቸው ለቅዱስነታቸው ያላቸውን አክብሮ እና ፍቅር መግለጫ ተደርጎ ተወስዱዋል። ቅዱስነታቸው በስብከታቸው እንደ ገለጹት ለእግዚኣብሔር ደስ የምያሰኘው የጽንፈኝነት ዓይነት ፍቅር ብቻ ነው ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንንም የተናገሩት ከዚህ ቀደም በግብፅ የኮፕቲካ ካቶሊክ ፓትሪያርክ የሆኑት ፓትሪያርክ ሲድራክ ቅዱስነታቸው በዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ  ከእስልምናው ዓለም ጋር በቀጣይነት ውይይት ሊደረግ ይገባል የሚለውን ሐሳባቸው ለማጠናከር አስበው የተናገሩት እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውንን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማደመጥ ትችላላችሁ!

በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ ከ30 ሺ በላይ የካቶሊክ፣ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናን እንዲሁም የሙስሊም ምዕመናን ተወካዮች መካፈላቸውም የተጠቀሰ ሲሆን በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የተወሰደው ከሦስተኛው የፋሲካ እሁድ ሰንበት ምንባባት አንዱ ከሆነው ከሉቃስ 24፡13-35 የተወሰደው እና ሁሉት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ ከሞተ ቡኃላ በድጋሚ አይነሳም ብለው ተስፋ ቆርጠው ከኢየሩሳሌም ወደ ኤማውስ በመጓዝ ላይ በነበሩበት ወቅት ኢየሱስ እንደ ተገለጸላቸው በሚተርከው ታሪክ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው ሞት፣ ትህሣኤ እና ሕይወት በሚሉት ሦስት ቃላት ላይ ትኩረቱን ባዳረገው ስብከታቸው እንደ ገለጹት የእነዚ ሁለት ደቀ መዛሙርት ተሞክሮ የመነጨው ከስጋት፣ከኪሳራ ስሜት፣ የሕይወት ማጣቀሻ ከማጣት፣ ደስታንና መተማመንን ከማጣት፣ ከሙታን የተነሣውን ጌታ ለማየት ከነበራቸው ጉጉት እና በመጨረሻም እያንዳንዱ ሰው እግዚኣብሔርን ለማግኘት ከሚያደርገው ፍለጋ የመነጨ መሆኑንም ገልጸዋል።

“የመስቀሉን ጉዞ ተመክሮ በማለፍ እስከ ትንሣኤው እውነተኛነት ያለውን ጉዞ የማያልፍ  ሰው እራሱን በራሱ በማውገዝ ተስፋ እስከ መቁረጥ ይደርሳል” ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ በእርግጥ አምላክ ሁሉን ቻይ እና ኃያል  መሆኑን የምያንጸባርቀውን ግንዛቤያችን ውስን መሆኑን እስካልተረዳን እና ይህንንም አስተሳሰብ እስከ አልሰቀልነው ድረስ አምላክን በአግባቡ መገናኘት አንችልም ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን የተወለደችው በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ባለን እምነት ተመስርቶ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው እውነተኛ እምነት ደጋጎች፣ መሐሪዎች፣ ታማኝ እና ሰብዓዊነትን የተሞላን እንድንሆን ያደርጋል ካሉ ቡኃላ ይህም እውነተኛ እምነት የመወያየት ባሕልን፣ መከባበርን እና ወንድማማችነትን  ጠብቀን እንድንጓዝ ያደርገናል ብለዋል።

“እውነተኛ እምነት የሌሎችን ሰብአዊ መብቶችን እንድንጠብቅ ያደርጋል፣ በተመሳሳይም መልኩ ሌሎችም በዚሁ መልኩ የእኛን ሰብአዊ መብት እንድያከብሩ ማድርግም ይቻላል፣ በእርግጥ በእምነት ስናድግ እና በሕሊናችን ስንመራ፣ በተመሳሳይ መኩም በውስጣችን ያለው ትህትናም ያድጋል፣ ትንሽ መሆናችንንም እንረዳለን” ብለዋል።

እግዚኣብሔርን የሚያስደስተው  እምነት አሉ ቅዱስነታቸው በሕይወት ምስክርነት የታጀበ እምነት ነው ካሉ ቡኃላ ምክንያቱም “እርሱ ለአማኞች የፈቀደላቸው የጽንፈኛነት ዓይነት ፍቅር ብቻ ነው” ካሉ ቡኃላ ከዚህ ለየት ያለ ጽንፈኝነት እግዚኣብሔርን አያስደስተውም፣ ከእርሱም የመነጨ ሊሆን በፍጹም አይችልም ብለዋል።

“ለትንሳኤው ብርሃን ልባችሁን መክፈት አትፍሩ፣ ጥርጣሬያችሁን ሁሉ በማስወገድ በአዎናቲ አስተሳሰቦች እና ለሌሎች መልካምነትን ታሳዩ ዘንድ እንዲለውጣችሁ ፍቀዱለት፣ ወዳጆቻችሁም ይሁን ጠላቶቻችሁን ሁሉንም ከመውደድ አትታክቱ ምክንያቱ በሕይወት ምስክርነት በምናሳየው ፍቅር ብቻ ነው የእምነታችን ጥንካሬ እና ታላቅነት የሚገለጸው በዚሁ መልክ ብቻ ነው” ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጅቱን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.