2017-04-29 14:22:00

ር.ሊ. ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግብፅ በመካሄድ ላይ በነበረው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ያስተላለፉት መልእክት።


ከቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 20/2009 ዓ.ም. በግብፅ በሚገኘው በታላቁ የአል ዛዓር ማዕከል በመካሄድ ላይ በነበረው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ያደረጉትን ንግግር እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የዚህን መልእክት ሙሉ ይዘትን ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ

አል ዛዓር የጉባሄ መዐከል

ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም.

ሰላም ለእናንተ ይሁን

በግብፅ የማድረገውን ጉብኝት በመጀመር በዚህ ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ መአቀፍ ውስጥ ሆኜ እዚህ መገኘቴን እንደ ታላቅ ስጦታ እቆጥረዋለሁ። የታላቁን የአል ዛዓር ኢማም ይህንን ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ስላቀዱ እና ስላስተባበሩ እኔንም በዚህ ጉባሄ ላይ እድሳተፍ በትህትና ስለጋበዙኝ አመሰግናለሁ።

በዚህ ታላቅ ታሪክ ባላት ምድር፣ ከዘመናት በፊት የዓለም የስልጣኔ መጀመሪያ፣ እንዲሁም የቃልኪዳን ምድር ስለሆነችው ይቺ ምድር የተወሰኑ ነገሮችን ማለት እፈልጋለሁኝ።

ግብፅ በአባይ ወንንዝ ተፋሰስ የምትገኝ እና የሰው ልጅ ስልጣኔ የጀመረባት ጥንታዊ ሀገር ናት። ዐስርቱ ትዕዛዛት በድንጋይ ላይ ከመታተማቸው በፊት በሲና ተራራ ላይ የታወጁባት ሀገር ናት። በዚህ በዛሬው ውይይታችን እዚህ ለሚገኙ ግለሰቦች እና በሁሉም ዘመን ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ “አትግደል” የሚለው ትዕዛዝ በድጋሚ ያስተጋባል። ሕይወት ሰጭ የሆነው እግዚኣብሔር በፍጹም ሰውን ከመውደድ ታክቶ አያውቅም፣ ስለዚህም ማንኛውንም ዓይነት የነውጥ መንግዶችን ለማስወገድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ምድራዊ ቃል ኪዳንን ነው። ከሁሉም በላይ በተለይም ዛሬ እኛ ባለንበት ዘመን ሁሉም ሐይማኖቶች የተጠሩት ይህንን ታላቅ የሆነ ትምህርት ለማክበር እና ነውጥ የሚፈጥሩ ማንኛውንም ዓይነት ነገሮች እንድናስወግድ ነው። ነውጥ ማንኛውንም ሐይማኖት እንደ መካድ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።

እኛ የሐይማኖት መሪዎች የተጠራነው የሐይማኖት ጭንብልን ለብሰው ነውጥ የሚፈጽሙትን ሁሉ ለማጋለጥ ነው። ማንኛውንም የሰው መብቶችን እና ስብእናን የሚጥሱ የነውጥ ተግባሮችን የማውገዝ ግዴታ አለብን ምክንያቱም የሐይማኖቶች ሁሉ አባት የሆነው እግዚኣብሔር፣ ስሙ ቅዱስ ነው፣ የሰላም አምላክም ነው። በእግዚኣብሔር ስም ሊከናወን የሚገባው ተግባር የእርሱን ስም የሚያረክሰው ነውጥ ሳይሆን ሰላም ብቻ ነው። ነውጥ የእግዚኣብሔርን ስም ያጎድፋል፣ ያረክሳልም።

ሐይማኖቶች የተጠሩት ክፉ የተባሉ ነገሮችን ለማጋለጥ ብቻ ሳይሆን ከመቼው ጊዜ በላይ በተለይ ዛሬ ሰላምን የማስፋፋት ተልዕኮም አላቸው። እኛ እንደ ክርስቲያን “ሁሉም ሰዎች በእግዚኣብሔር ሀምሳል በመፈጠራቸው የተነሳ ሰዎችን ሁሉ እንደ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የማናስተናግዳቸው ከሆነ፣ ጸሎታችን በትክክለኛ እና በእውነተኛ መንፈስ ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ አንችልም።

ግጭቶችን ለማስወገድ እና ሰላምን ለመገናባት በቅድሚያ አክራሪነት ሥር መሰረቱን ያደርገበትን ድኽንነትን እና ብዝበዛን ብሎም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ማገድ እና ብጥብጥን ለሚፈጥሩ ሰዎች ሁሉ የሚቀርበውን የጦር መሳሪያ ማስቀረት ይኖርብናል። በተለይም የጦር መሳሪያ ምርት እንዲወገድ መስራት ይጠበቅብናል፣ ምክንያቱም የጦር መሳሪያ ዛሬ ወይም አንድ ቀን ጥቅም ላይ መዋሉ አይቀሬ ስለሆነ ነው። የየሀገራቱ መሪዎች፣ ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙሐን ሳይቀሩ ይህንን ከባድ የሆነ ተልዕኮ ለማሳካት መስራት ይኖርባቸዋል።

እዚህ የተሰበሰብን ሁላችን እንደየ ባሕላችን በያለንበት አከባቢ በታሪክም ቢሆን ሰላም ይሰፍን ዘንድ የበኩላችንን ተግባር እንድንፈጽም በእግዚኣብሔር ኃላፊነት ተሰቶናል። ሰላም በሀገራት እና በሰዎች መካከል ስምምነት እንዲመጣ ያደርጋል። ይህ የተወደደ የግብፅ ምድር ለራሱ ሕዝብ እና በመካከለኛ ምስራቅ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ አስተዋጾ እንደ ሚያደርግ ተስፋዬ ነው።

ሰላም ለእናንተ ይሁን።

             ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ

            28/04/2017 አል ዛዓር የእስልምና ማዕከል፣ ግብፅ ካይሮ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.