2017-04-28 17:49:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ክፍት ብርቱና ከሕዝብ ጋር በሕዝብ መካከል ይሁን


“ተልእኮ የካቶሊክ ተግባሮች ካሉት ኃላፊነቶች ውስጥ አንዱ ተብሎ የሚጠቀስ ሳይሆን ዋናውና መሠረታዊ ኃላፊነት ነው”  የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ የተማከለ ቃለ ምዕዳን ለዚያ እ.ኤ.አ. በ 1867 ዓ.ም. በኢጣሊያ ለተቋቋመው ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያናዊ ማኅበር ለሆነው የካቶሊክ ተግባር ማኅበር በአገረ ቫቲካን እያካሄደው ባለው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ መዝጊያ ቀን የተሳተፉትን ተቀብለው መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታውቋል።

“የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ዓይነተኛው የመለያ ኃይሉ ተልእኮው ካልሆነ ለመኖሩም ምክንያት እንደማይኖረው ነው፡ የሚያስፈልገው በቁምስናዎች በሰበካዎች በአገርም በመንደርም በቤተሰብም በየሥራና በትምህርት በዘመቻ እንቅስቃሴዎች በጠቅላላ በዚያ የኑሮ ሥፍራ ሁሉ በሚገለጥበት ጉዳይ ከህዝብ ጋርና ለህዝብ መሆን ይጠበቅበታል። ስለዚህ በዚህ ተልእኰ ለሁሉም ከሁሉም ጋር በመሆን በመወያየት በመወሰን የባህል ግንባታ ያከናውናል”  

ያሉት ቅዱ አባታችን የካቶሊክ ተግባር ማኅበር ዓራቱ አዕማዳት እነርሱም፥

“ ጸሎት ሕንጸት መስዋዕትነት (ገድል)ና ሐዋርያዊ ተልእኰ” የተሰኙ መሆናቸው አስታውሰው፥ በአነዚህ ዓራቱ አዕማዳት ጸንቶ ሐዋርያዊ ልኡክነት በወቅታዊው ዓለም የሚከውን ነው፡ አለ ጸሎት ተጋድሎውም ሆነ ሕንጸቱ ውጤት አልባ ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ጸላያን ሁኑ ወቅታዊውን ተጋርጦ ለመግጠም የሚያስችላችሁ በዚያ ከኢየሱስ ጋር በምታጸኑት ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ለዚህ ብቁ የሚያደርጋችሁ ወቅታዊ ሕንጸት ማግኘት ይኖባችኋል፥ ልባችሁን በሰዎች ስቃይና ሐዘንና ደስታ ላይ አኑራችሁ ዘወትር ጸልዩ። እንዲህ በማድረግ የሕዝቡ ችግር ተመልካች ሳትሆኑ የሕዝቡ ሁኔታን ተካፋይ ትሆናላችሁ። ተጋድሎ ከሁሉም በላይ ንጹሓን ሆናችሁ እንዲሰማችሁ ሳይሆን ለሌሎች መልካምን ነገር ለማድረግ የሚያነቃቃችሁ ይሁን። የምታቀርቡት አስፍሆተ ወንጌል፡ ሌላው እምነት ለማስካድ የሚቀርብ እንዳሆንም መስተዋል አለበት ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን አስፍሆተ ወንጌል በቃልና በሕይወት በምትሰጠው ምስክርነት በመማርክ ነው፡ ስለዚህ የካቶሊካዊት ተግባር ተልእኮ የሆነውን አስፍሆተ ወንጌል መወቀት ማለትም ወቅታዊነት በማረግ ወንጌላዊ ተልእኮ በቀመራዊ ተግባር ሳይሆን በቃልና በሕይወት በሁሉም ሥፍራ ለሁሉም በማንኛውም ሁነትና ወቅት በዚያ በከተሞቻችን በሕልውናም ጥጋ ጥግ በሆነው ሁነት ለሚገኘው  ሁሉ ማቅረብ ነው፡ በሕዝቡ በሰዎች ሁነት በቁምስናዎ በሰበካዎች  ስግዋን ሁኑ ማለትም በሕዝቡ ሁነት ውስጥ በመውረድ በመካከል መገኘት ይኖርባችኋላ።

እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታውቋል።

“አደራችሁ ልክ እንደ እነዛ ኵላዊነትን ለማንም ካለ መታዘዝ አለ ተጠያቂነት እንደሚኖሩ ስሜታችውን የሚማርከውን በመሻትና ደስ የሚያሰኛቸውን ፍለጋ ለሚጠመዱ አለ መሰረተ መንደርደሪያ እንደሚኖሩ አትሁኑ፡ ኩላዊነታችሁ መሰረት አለው። ስለ ተልእኰ በተመለከተ በእንከን የለሽ ሥራ ለመርካት በሚል ፍላጐት ዙሪያ ስታጠነጥኑና ስታብላሉ ጊዚያችሁን ስታጠፉ ያጠናችሁትና የቀመራችሁት ሁሉ ጊዜ ያልፍበትና ተመልሳችሁ ትንትና ውስጥ ትገባላችሁ። ስለዚህ ምልከታውን የሚሰጣችሁ ተጨባጩ ሁነት ይሁን አደራ”

ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አክለው፥ “ዝግጁ በሆነው ልባችን በመጸለይ ጸሎትን እንደምንማር ሁሉ ወንጌላዊነትን ወንጌልን በማስፋፋት ነው የምንማረው” ስለዚህ

“ካቶሊካዊት ተግባር በፖለቲካም በድርጅቶችም በሙያዊ ዘርፍ ሁሉ ህልው መሆን ይኖርበታል። ህልውነቱም እንከን የሌለው ወጋኛ ክርስቲያን ሆኖ በመገኘት ሳይሆን በማገልገል ነው፡ በተለይ ደግሞ በማረሚያ ቤቶች በሕክምና ቤቶች በጎዳናዎች በድኾች መኖሪያ ክልል በፋብሪካዎች ሁሉ ወንጌላዊነትን በማገልገል ህልው ማድረግ ያስፈልጋል። ፈሪሳዊ አስመሳይነትን አታነቃቁ መስተዳድራዊ ተከትሎነትን ሳይሆን የምሕረት አቀንቃኝ ሁኑ፡ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ቤተ ክርስቲያን ከር.ሊ.ጳጳሳት በላይ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስያን እትሁኑ፡ በሮቻችሁን ክፈቱ፡ ሁሉንም አስተግናዱ አትወግኑ፡ በቤተ ክርስትያን ካልታሰረ ምሥጢረ ተክሊል የተወለደም ይሁን ሁሉን የማኅበሩ አባል ሊሆን አይችልም የሚል ቅድመ ፍርድ አይኑራችሁ አትፍረዱ። ምስረቃው የተዛባባቸው በድንግዝግዝ ዓለም ያሉትን የቆሰሉትን ወጣቶች ለሁሉም ክፍት ሁኑ”

ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው፥ “ብርቱዎች ሁኑ፡ በእያንዳንዱ እርምጃ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ከሌሎች ለመነገርና ምልከታው እንዲሰጣችሁ የምትጠባበቁ ከሆናችሁ ለቤተ ክርስቲያን ታማኞ አይደላችሁም ማለት ነው” ብለው የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታውቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.