2017-04-28 17:55:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ክርስቲያን የአንድ አስተሳሰብ ምስክር ሳይሆን የተአዝዞ ምስክር ነው


“ክርስትያን መሆን ማህበራዊ ክብር ሁኔታ ወይንም ሥልጣን ሳይሆን ልክ እንደ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር መገዛትንና ለእርሱ ታዛዥ የመሆን ምስክርነት ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. እንደ ወትሮው ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መስዋዕተ ቅዳሴ ኣሳርገው ባሰሙት ስብከት መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ ገለጡ።

የዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ታዛዥ መሆን እንድንችል የሚያበቃውም መንፈስ ቅዱስ ነው በመሆኑም ጸጋውን እንዲሰጠን ልንለምነው እንደሚገባን ያስገነዘብት ቅዱስነታቸው፥ በላቲን ሥርዓት የዕለቱን ምንባብ የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 5, 27-33 እና የዮውሓንስ ወንጌል ምዕ. 3, 31-36  ባለው ላይ ተንተርሰው፥ 

ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሒር ልንታዘዝ ይገባል ያለው በመልአኩ አማካኝነት ከወህኒ ቤት ነጻ ከወጡ በኋላ ጴጥሮስና ደቀመዛሙርት በሊቀ ካህናቱ ፊት ነበር፡ በኢየሱስ ስም ማስተማር ተከልክሎ ነበር። እንዲህ መወሰኑም ሊቀ ካህናቱ ሊያስታውሳቸው ወደደ። ነገር ግን ደቀ መዛሙርት በሚሰጡት ትምህርት ኢየሩሳሌም እንድትጥለቀለቅ አደረጉ። ይኽንን በዕለቱ ከግብረ ሐዋርያት የተወሰደውን ምንባብ መሠረት በማድረግ ከገለጡ በኋላ ጉዳዩ ከዚያች ከመጀመሪያው ዘመን ከነበረቸው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጋር በማጣመር በደቀ መዛሙርት ትምህርት አማካኝነት ብዙዎች ይለወጡና ተአምራትንም ይፈጽሙ ነበር። ከሕዝብ በኩል ህያው እምነት ነበር እነዚያ ብልጦች ነን ባዮችንም ልክ እንደ ሐናኒያና ሰጲራ የመሳሰሉት እምነት ለገዛ እራሳቸው የሥልጣን መወጣጫ ለመጠቀም በሚሹትም ዘንድም እምነት ነበር፡ የዚህ ዓይነቱ ሁለት ዓይነት እምነትን የመኖሩ ጉዳይ በዚያ ዘመን ብቻ ሳይሆን አሁንም እንዳለ ይታያል። ያንን በሽተኞችን ወደ ደቀ መዛሙርት ፊት ለፈውስ ያመጡ የነበሩትን መንፈሳዊ ንገደት ይፈጽም የነበረውን አማኙን ሕዝብ ያልተማረ መሃይም ብሎ የሚያንቋሽሽ ብዙ ነበር። አማኙን ሕዝብ የሚያንቋሽሽ መቼም ቢሆን ይሳሳታል። ጴጥሮስ ፈርቶ በዕለተ ሓሙስ ሰሙነ ሕማማት ወቅት ኢየሱስን ካደ አሁን ግን በኃይል ተሞልቶ አለ ምንም ፍርሐት በሁሉም ፊት ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ልንታዘዝ ይገባል ሲል ደፍሮ ይናገራል። ይኽ የጴጥሮስ መልስ “ክርስትያን እንደ ኢየሱስ በደብረ ዘይት ሁለመናውን ተሟጦ ለአባቱ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን ሲል እንደታዘዘው ሁሉ የፍጹም ተአዝዞ ምስክር መሆኑ ማለት እንደሆነም ያረጋግጥልናል።”

“ነገር ግን የተአዝዞ መስካሪ ለመሆን የመንፍስ ቅዱስ ጸጋ ያስፈልጋል” በማለት ያስረዱት ቅዱስ አባታችን፥ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው የተአዝዞ መስካሪያን እንድንሆን የሚያበቃን፡ “እኔ ወደ እዚያ የሃይማኖት መምህር ነው የምሄደው፡ ያንን መንፈሳዊ መጽሓፍ ነው የማነበው ሊባል ይቻላል። ይኽ ሁሉ መልካም ተግባር ነው ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው የሰውን ልብ ሊለውጥና የተአዝዞ መስካሪ ለመሆን የሚያበቃው” ይኸንን የመንፈስ ቅዱስ ተግባርን ነው ልንለምን የሚገባን፥ “አብ ወልድ ኢየሱስ የተአዝዞ ምስክር እንድሆን ማለትም ክርስቲያን እንድሆን በእኔ በእኛ ላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ፍቀዱ” በማለት እንጸልይ። የተአዝዞ ምስክር መሆን በዕለቱ በተነበበው አንደኛው ምንባብ ዘንድ ጴጥሮስ እንደሚያወሳው ሊገልድሉትም እሰሚቃጣቸው ድረስ፥ “የተአዝዞ ምስክርነት ስደት መከራ መገፋትንም እንደምያስከትል ነው” ኢየሱስ ብፅዕ የሚያስብሉ ተግባራት ሲዘረዝር፥

“እናንተ የምትሳደዱ የምትዘለፉ ብፅዓንናችሁ በማለት እንዳስቀመጠው ነው፡ መስቀል ከክርስትናው ሕይወት ማግለል አይቻልም። የአንድ ክርስቲያን ሕይወት  “ክርስትያን መሆን ማህበራዊ ክብር ሁኔታ ወይንም ሥልጣን ሳይሆን የእንድ መልካም የሚያደርገኝ የሚያሻሽለኝ የመንፈሳዊ ሕይወት ሁነት መኖር ማለት ነው። ነገር ግን ይኽ ለብቻው በቂ አይደለም። የአንድ ክርስቲያን ሕይወት ልክ እንደ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር መገዛትንና ለእርሱ ታዛዥ መሆን ምስክርነትና ሕይወቱ ለዘለፋ ለስደት ለስም ማጥፋት ለመሳሰሉት አደጋዎ የተጋለጠ ነው” እንዳሉ ዲኒኒ አስታውቋል።

እንደ ኢየሱስ የተአዝዞ መስካሪ ለመሆን፥ መጸለይና ብዙ የዓለም ይሆኑት ነገሮች በልባቸው አምቀው የያዙ ሐጢአተኞች መሆናችንን ማወቅ ይገባናል ስለዚህ እግዚአብሔር፥ “የተአዝዞ መስካሪያን የሚያደርግ ስደትና መከራ ሲያጋጥም ስንታማ ስንዘለፍ ስማችን ሲጠፋ ሁሉ ላለ መፍራት ጸጋውን እንዲሰጠን እንዲሰጠን እንለምነው። ምክንያቱ በዳኛው ፊት ስንቀርብ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሆኖ መልስ ይሰጣል ሲል ጌታችን እንደተናገረው ነውና” በማለት ያደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዲኒኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.