2017-04-26 17:16:00

የሃይማኖት ነጻነት ለኤውሮጳ አቢይ ተግዳሮት ነው


የመላ ኤውሮጳ ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረትና ኤውሮጳዊ ሕዝባዊ የፖለቲካ ሰልፍ በጋራ ያነቃቁት የሃይማኖት ነጻነት ለኤውሮጳ ዓቢይ ተግዳሮት መሆኑ በጥልቀት የሚያስገነዝብ፥ “የይማኖትና የቅብልት (እምነት) ነጻነት መከላከልና እንዲከበር ማድረግ ከሚለው ከኤውሮጳው የውሳኔ ሰነድ፡ ከዚህ በኋላስ ምን?” በሚል ርእስ ሥር ያነቃቁት ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. በራሰልስ ባለው በኤውሮጳ ኅብረት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ መካሄዱ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዚህ የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ዋነኛው ዓለማ የኤውሮጳው ኅብረት ከ 2013 ዓ.ም. ወዲህ በሃይማኖትና በቅብልት አመለካከትና እምነት ነጻነት ዙሪያ መርህ ይሆናል በማለት ባሰፈራቸውና ስምምነት በተደረገባቸው የውሳኔ ነጥቦች በአሁኑ ሰዓት በሃይማኖት ነጻነት ዙሪያ ዛሬ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ተጋርጦዎች የተነተነና የዚያ የውሳኔው ሰነድ ውጤት የገመገመና ይኽ የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነት ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት ገልጦ፥ በዚህ በተካሄደው ጉባኤ ኤውሮጳዊ ሕዝባዊ የፖለቲካ ሰልፍ የውይይትና ከተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይትና እንቅስቃሴ የሚንከባከብ ድርገት ምክትል ሊቀ መንበር ግዮርግይ ሆልቨንዪ፥ የሃይማኖት ነጻነት በወቅታዊው ሁነት ተጋርጦው ምን ይመስላል በሚል  እንዲሁም የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ክቡር ኣባ ኦሊቪየር ፖኵይሎን፥ የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ ከሚመለከተው ስምምነት ማዶ በሚል በመቀጠልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተአምኖ ነጻነት የሚንከባከበው ቢሮ ተጠሪ አህመድ ሻሂድ፥ አዳዲስ ተጋርጦዎች በተሰኙት ርእሶች ባስደመጡት ንግግር ተጀምሮ ዓውደ ውይይቱም የኤውሮጳ ሕዝባዊ የፖለቲካ ሰልፍ የሰብአዊ መብትና ክብር ተነክባካቢ ቢሮ ተጠሪ መርሰደስ ግራሲያ ፐረዝ፥ የ2013 ዓ.ም. የሃይማኖት ነጻነት ሰነድ ወቅታዊ ተጋርጦዎችን ግምት በመስጠና በማካተት እንዴት ወቅታዊ ማድረግ በሚል ርእስ ስር ባስደመጡት ንግግር ቀጥሎ መዋሉንም አስታውቋል።

የተካሄደው ጉባኤ የሃይማኖትና የተአምኖ ነጻነት ጉዳይ ለኤውሮጳ ኅብረት ተጠሪ ዣን ፊገል፥ የሃይማኖትና የተአምኖተ ነጻነት ሁኔታ ከኤውሮጳ አገሮች ውጭና በዚሁ ዙሪያ የኤውሮጳ ኅብረት ሚና በሚል ርእሰ ጉዳይ ንግግር ሲያሰሙ የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ የሕግና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ ኾሴ ባዛን በበኩላቸውም የ2013 ዓ.ም. የኅብረቱ የሃይማኖት ነጻነት ውሳኔ ገቢራዊና ብቃት እንዲኖረው ለማድረግ በሚል ነጥብ ዙሪያ ማስተግባሪያ ይሆናሉ የሚሉዋቸው ሓሳብ አዘል ንግግር ማስደመጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት ካጠናቀረው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.