2017-04-26 17:12:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ለዓለም ሰላም አጅግ አስፈላጊነት ያለው ቅድመ ሁነት ነው


“የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ለዓለም ሰላም አንድ አስፈላጊ ቅድመ ሁነት ነው፡ ከዚህ ባሻገር የጋራው ውይይቱ ለክርስትናው ሃይማኖትም ሆነ ለሁሉም ሌሎች ሃይማኖቶች ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው” ፡ ይኽንን ያሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ቪላ ቦርገዘ ተብሎ በሚጠራው መናፈሻ የኢጣሊያው የምድር ቀን ማኅበር ካቶሊካዊው የአፍቅሮተ ዘቤት እንቅስቃሴና የኢጣሊያ የተፈጥሮና የአካባቢ ጉዳይ ሚኒ. ዓለም አቀፍ የምድር ቀን ምክንያት የምድር ጎጆ በሚል ስያሜ ያነቃቃውን መርሃ ግብር በይፋ ለመክፈት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይኽ ዓለም አቀፍ የምድር ቀን ዋና ዓላማው ዜጎች የምህዳር ባህል በጥልቀት እንዲያስተውሉና ከዚህ ጋር በተያያዘ ሂደት የተፈጥሮ ያካባቢ በጠቅላላ ፍጥረናን ተፈጥሮን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉት የጋራ ቤታችን ጤንነት በመንከባከብ ረገድ እንዲተጉ የሚያደግ ዘመቻ ሲሆን በተለይ የነገው ትውልድ በዚህ ባህል ታንጾ ካሁን ካለው ትውልድ በላይ ምህዳርን በመንከባከቡ ረገድ ትጉ እንዲሆን ለማድረግ መሆኑ ማብራሪያው የሰጠው ሲር የዜና አገልግሎ አክሎ፥ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ባስደመጡት ስብከት፥

“የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ለዓለም ሰላም መሠረት እንደመሆኑ መጠን ምህዳር መንከባከብም ከዚህ ባልተናነሰ ደረጃ የላቀ እሴት ነው፡ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ብዙ ጉዳዮች ነክ ነው፡ ለዓለም መረጋጋት ሰላምና የተፈጥሮና ፍጥረት እንክብካቤ መረጋገጥ በሚደረገ ጥረት ሁሉ ሃይማኖቶች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው፡ በቅርቡ ቤተ ክርስቲያን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አክብራለች ይህ የእምነት ማእከል የሆነው የክርስቶስ ከሙታን መነሣት ኅዳሴና ትንሣሴ በሁሉም መስክል እዲከወን መሠረት መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች።  ከጥቂት ቀናት በኋላ በትክክል እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 28 ቀን እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን በግብጽ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሂዳሉ በዚህ ጉብኝት ወቅትም በአል አዝሃር አቢይ መንበረ ጥበብ ሰላምን ርእሰ ጉዳይ ያደረገ ባዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ ይሳተፋሉ። ስለዚህ ይኽ ዓውደ ጉባኤ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ለዓለም ሰላም ግንባታ ዓቢይ አስተዋጽኦ እንዳለው የሚመሰክር ሁነት ነው”

እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎ ይጠቁማል።

ሁሉም እንደሚያውቀው የጋራ ውይይት ግኑኝነት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስልትና በመደጋገም በሁሉም መስክ በቤተ ክርስቲያንም ከቤተ ክርስቲያን ውጭም እንዲኖር ያሳስባሉ። ይክ እሳቸው የሚከተሉት ስልት መሆኑም ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ገልጠው በውይይት እውነትን ለመፈለግና ውድማማችነትን ለመኖር እያንዳንዱ ለሚያደገው ጥረት ድጋፍ ነው ብለው ስብከታቸውን፥ “በሁለት ስበት ውስጥ እንገኛለን አንደኛው የመልካምነት ስበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የክፋትነት ስበት ነው። ክርስቶስ ሞትን አሸነፎ ከተነሣ ወዲህ ከዚያ የጥላቻና የክፋት ስበት በላይ የፍቅርን የመልካም ስበት እጅግ ኃያል መሆኑ ተረጋግጦልናል። የክርስቶስ ትንሣኤ የሕይወት ስበት ከሞት ስበት እጅግ ብርቱ መሆኑ አረጋግጦልናል” በማለት እንዳጠቃለሉ ሲር የዜና አገልግሎት ዘግቧል።








All the contents on this site are copyrighted ©.