2017-04-24 17:10:00

ወንጌል በዓለም ሁሉ ይስፋፋ ዘንድ የተቀበልነው ወንጌላዊ ተልእኮ እናድስ


ቅዱስ አባኣታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በፓላንድ የግናይዝኖ ዎቸክ ፖላክ ሊቀ ጳጳስ በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሜ የሚል ስያሜ የተሰጠበት ዝክረ ስድስ መቶኛው ዓመት ምክንያት ለሰበካው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. “ወንጌል በዓለም ሁሉ ይስፋፋ ዘንድ የተቀበልነው ወንጌላዊ ተልእኮ ዳግም እንዳስ”  የሚል ሃሳብ ያማከለ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመ ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት የዛሬ ስድስት መቶ ዓመት በፊት በኮንስታንዝ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በተካሄበት ወቅት የግናይዝኖ ዎቸክ ፖላክ የቀዳሜነት ስያሜ ሰበካው ለገዛ እራሱና በመላይቱ ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በፖሎኒያ ቀዳሚነቱን እውቅ አግኝቶ በሰበካው ሊቀ ጳጳስ ሆነው በመተካካት ለሚሰየሙት ሁሉ ቀዳሚነቱ በተዋረድ የሚተላለፍ ስሜት ሆኖ እንዲቀጥል መደረጉንም ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይኽ ስያሜ በዚያ በድሮው የፒያስት ሥርወ መንግሥት የክርስትና እምነት አናሥር በመሆን ወጌላዊ ተልእኮ በይፋ የተጀመረበትና ብሎም ቅዱስ አዳልበርቶ የደም ሰማዕትነት የተቀበለበት ጽኑና ጥልቅ እምነት አሃዱ ያለበት ጊዜ እንደነበርም አብራርተው ይኸው በዚያች ምድር የሰማዕት አዳልበርቶ ቅዱስ አጽም እንደሚገኝና እ.ኤ.አ. በ 1000 ዓ.ም. የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲልቨስትሮ ዳግማዊ ልኡካን ወደ ክልሉ ተልከው ከነበረው የኦቶነ ሦስተኛና ከልዑል ቦለስላዖ ጋር መገናኘት ወዲህ ግናይዝኖ ሜጥሮፖሊታና ለክልሉ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቀዳሜ እንዲሆን መደረጉንም ታሪኽ ጠቀስ የሆነውን ምዕራፍ ዋቢ በማድረግ እ.ኤ.አ. በ 1417 ዓ.ም. የመላ ፖላንድ ቀዳሜ ለመሆን መብቃቱንም አስታውሰው፡ ይኽ ታሪካዊ ሁነትም በፖላንድ በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ማእከል ሆኖ ይዘከራል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ በቀጣይ ዘመናትም ይላሉ ቅዱስነታቸው በመእክታቸው፥ “የግናይዝኖ ሰበካ አገረ ፖላንድ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን የክርስትና እምነትና መንፈሳዊነት ማጣቀሻ ሆኖ የሕዝቡ የነጻነት ማእከልና ለመንፈሳዊ እድገቱንም ጭምር አቢይ ታሪካዊ የባህልና የክርስትና እምነት ቅርስ ነው” እንዳሉ ያመለክታል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት፥ “የግናይዝኖ ሰበካ በጠቅላላ የአገሪቱ ሕዝብ ወደ ተስፈኛ መጻኢ በማተኰር ሰማዕት ቅዱስ አዳልበርቶ የሰጠው በዚያ ክልል ለአስፍሆተ ወንጌል ህያው ምንጭ የሆነው ጥልቅ መንፈሳዊ አስተንፍሶ ለመጪው ትልውድ በቃልና በሕይወት ምስክርነት ይቀጥልም ዘንድ ለጌታ ኃይልህን ስጠን እንበል”  በማለት ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.