2017-04-24 15:59:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "መንፈስ ቅዱስ ግትሮች እንዳንሆን እና እንዳናወላዳ ይረዳናል" ይረዳናል ማለታቸው ተገለጸ።


“የእኛ እምነት ምናባዊ ያለሆነ፣ በመግባባት የሚያምን ተጨባጭ የሆነ ነገር መሆኑን በፍጹም መርሳት የለብንም”። ቀደም ሲል ያነበባችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 16/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙትስ ስብከት የተወሰደ ነው።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያሰሙት ስብከት መአከሉን አድርጎ የነበረው መንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ ወንጌልን ግትር ባለሆነ መልኩ እንድናውጅ ነፃነቱን ይሰጠናል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ጨምሮ ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ከዩሐንስ ወንጌል 3፡ 1-8 ተወስዶ በተነበበው የወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው ኒቆዲሞስ የተባለ የአይሁድ አለቃ የነበረ ሰው በሌሊት ኢየሱስን ሊገኛኘው መውጣቱን በሚያወሳው የመወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው እንደ ገለጹት ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ በፍቅር እና በትዕግስ “በድጋሚ በመንፈስ ቅዱስ መወለድ ያስፈልጋል” ብሎ እንደ ነበረ ጠቅሰው ይህም ከአንድ አስተሳሰብ ወደ ሌላ አስተሳሰብ መሻገር እንደ ሚያስፈልግ ያሳያል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን አስተሳሰባቸውን በሚገባ ለማጽናት በማሰብ በወቅቱ ከሐዋሪያት ሥራ 4፡23-31 ላይ በተነበበው እና ሐዋሪያው ጴጥሮስ እና ዩሐንስ ከሙታን በተነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንድ ሽባ ሰው በመፈወሳቸው የተነሳ ተከሰው እንደ ነበር በሚያወሳው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ተመስርተው የነበረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሐዋሪያው ጴጥሮስ በአይሁድ አለቆች ሽነጎ ፊት ቆሞ “ያየነውን እና የሰማነውን ከመናገር በፍጹም ወደ ሁዋላ አንልም” ብሎ እንደ ነበረም አስታውሰው በዚህም መልክ መልካም ተግባራችውን ማከናወን ቀጥለው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“ይህም የእምነታችንን ተጨባጭነት ያሳያል፣ ሐዋሪያው ጴጥሮስ እና ዩሐንስ የነበራቸውን ጥንካሬ እና ግልጽነትም ያሳያል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ግልጽነት የመነጨው ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑን አስምረው ይህም “የለምንም ማወላዳት በግልጽ፣በድፍረት፣ በእውነት ማናገር” ማለት እንደ ሆነ ገልጸው ይህም እምነታችን ተጨባጭ መሆኑን የሚያስይ የመጀመሪያ ምልክት ነው ብለዋል።

“ቃል አሳብ ሆነ ሳይሆን የሚለን ቃል ሥጋ ሆነ ነው የሚለው! አንድ አንድ ጊዜ እምነታችን ተጨባጭ ነገር መሆኑን እንዘነጋለን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ብዙን ጊዜ ጸሎተ ሐይማኖታችንን በምንደግምበት ወቅት “ሰማይንን እና ምድርን በፈጠረ በእግዚኣብሔር አብ አምናለው ከቅድስት ድንግል ማሪያም ሥጋን ለብሶ ተወለደ፣ ሞተ. . .” ወዘተ የሚሉት ነገሮች ሁሉ ምናባዊ ሳይሆኑ ነገር ግን ተጨባጭ የሆኑ ነገሮች ናቸው ብለዋል።

“ይህንን ምስጢር በጥልቀት መረዳት እንድንችል እና ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚያደርገን፣ በእምነት ቅባት የሚቀባንን፣ እምነታችን ተጨባጭ ነገር መሆኑን እንድንረዳ የሚረዳንን መንፈስ ቅዱስን ጌታ ይልክልን ዘንድ ልንጠይቀው የገባል ብለዋል።

“ንፋስ ወደ ፈለገበት ይነፍሳል፣ ድምጹንም እንሰማለን፣ ነገር ግን ከወደ የት እንደ መጣ እና ወደ የት እንደ ሚንፍስ ግን አናውቅም፣ ከመንፈስ የተወለደ ሰውም እንዲሁ ነው፣ ድምጽ ይሰማል፣ ድምጹን ይከተላል፣ ወደ የት እንደ ሚያደርሰው ባያውቅም የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ተከትሎ ይሄዳል” ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም እምነታችን ተጨባጭ መሆኑን ለመረዳት ከመንፈስ ቅዱስ መወለድ አስፈላጊ እንደ ሆነ ጌታ ራሱ ስላስተማረን ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት ጌታ ይህንን የፋሲካ መንፈስ ይሰጠን ዘንድ እን የለምንም ማወላዳት መንፈስ ቅዱስ በሚያሳየን ጎዳና ላይ መራመድ እንድንችል በነጻነትም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ መምጣቱን መመስከር እንድንችል ይረዳን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.