Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ወጣቶች

ቅዱስ አባታችን፥ ኅብረተሰባችን በጋለ ስሜት ያስተማሪነት ጥሪያቸውን የሚወጡ መምህራ ያስፈልገዋል

ቅዱስ አባታችን፥ ኅብረተሰባችን በጋለ ስሜት ያስተማሪነት ጥሪያቸውን የሚወጡ መምህራ ያስፈልገዋል - ANSA

21/04/2017 16:58

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ዝክረ ሁለት መቶኛ ዓመተ ምሥረታው በማክበር ላይ ለሚገኘው በቅዱስ ማርቸሊኖ ካምፓኛት ለተመሥረተው በቅርቡ በላቲን አመሪካ አገረ ኮሎምቢያ የማኅበሩ ጠቅላይ ጉባኤ ለሚያካሂደው የማሪያኒስት ወንድሞች ማኅበር ይድረስ ለጠቅላይ አለቃ ለወንድም ኤሚሊ ቱሩ“በእያንዳንዱ ሕፃን ተማሪ ውስጥ ያለው እምቅ ኃይል ጎልቶ እንዲወጣ ለማድረግ እንዲቻል አስተማሪዎች በፍቅር ሊያስተምሩ ይገባል” የሚል ምእንዳን ያማከለ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀረው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ማስተማር፥ “የደግነት የመልካምነትና የእግዚአብሔር ምኅረት መግለጫ ነው”  ያሉት ቅዱስ አባታችን፥ ወጣት ትውልድ ማስተማር እጅግ አስፈላጊና የላቀ ክብር ያለው ተልእኮ መሆኑ በማብራራት ይኽ ደግሞ የማሪያኒስት ወንድሞች ማኅበር መንፈሳዊ መርሆ መሆኑ አስታውሰው፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝ የማኅበሩ መሥራች ቅዱስ ማርቸሊኖ ካምፓኛት፥ “ሕፃናትን ማስተማር ማለት ለም መሬት  መኮስኮስ ማለት ነው” ሲል የተናገረውን ቃል ጠቅሰው አክለው “ማስተማር ብዙ መስዋዕትነት ጽናትና ቀጣይ ትጋት የሚጠይቅ ጥሪ ሲሆን። ልብን የሚያካትት የልብ ጥያቄ በመሆኑ ደግሞ የላቀ ክብር ያለው አገልግሎት ነው”  እንዳሉ ጂሶቲ ያመለክታሉ።

ማስተማር የእግዚአብሔር ፍቅርና ዱካ የሚታይበት አገልግሎት ነው

“ገዳማዊ ወይንም የመንፈሳዊ ማኅበር አባል በማስተማር አገልግሎት የሚሰማራው በቅድሚያ ገዛ እራሱን መኮስኮስ ይኖርበታል፡ በተመሳሳይ መልኩም በማሰተማር የሚኮሰኩስ ቅርጽ የሚሰጥበት ዘርፍ ነው ስለዚህ የሚኮሰኮሰውና ቅርጽ የሚሰጠው አካል ቅዱስ ነው። በዚያ በሚታነጸው ሰው ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅርና አሻራ አለና”  ያሉት ቅዱስነታቸው ከዚሁ ጋር በማያያዝም ይኽ ማኅበር የተመሠረተበት መንፈሳዊ መርሆ በወቅታዊው ሁነት ማዕቅፍ ስር በማገናዘብ ወቅቱ የሚጠይቀው የአገልግሎት ግብና ፍጹም ፍቅር የተካነው አገልግሎት መመስረቅ ይኖርበታል እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው ለማኅበሩ አባላት፥ “በታደሰ መንፈስ ተስፋን ሰንቃችሁ ወደ መጻኢ ተጓዙ” በማለት የማበረታቻ ቃል ለግሰው፥ “ወቅታዊው ኅብረተሰብ በዓላማና በመሠረታዊ ደንብ የጸኑ የበለጠ ዓለም ለሁሉ ሰው ዘር ለማረጋገጥ በሚያስችል የሕንጸት ዘርፍ የሚጠመዱ በቃልና በሕይወት እምነታቸውን የሚመሰክሩ አስተማሪዎች ይሻል”  እንዳሉ አስታውቋል።

ገዳማዊ ሕይወት የሚኖር አስተማሪ የቅድስት ድንግል ማርያም አብነት የሚከተል ነው

“በማርያም ሁሉም ለኢየሱስ፡ ለማርያም ሁሉም ለኢየሱስ፡ ዝግጁነት ለጋስነት ትህትና የተሰኙትን የማርያም ቅዱስ ምናባዊ መንፈስ አብነት በማድረግ ገዳማዊ ካህን ወንድም አስተማሪ መሆን ያስፈልጋል፡ እንዲህ ስትሆኑ ወጣቱ ተማሪ በእናንተ ውስጥ ያለው የሕይወት አግባብ በማስተዋል ለመማር ለማወቅ ያለው ጉጉት በመከተል ጥልቅ የሆነው ምጡቅ እውቀትን ለመቅሰም አነሆኝ ይላል” በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

21/04/2017 16:58