Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስና የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 11/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ - ANSA

20/04/2017 10:48

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በትላንትናው እለት በሚያዝያ 11/2009 ዓ.ም. ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ከ15፡1-5 ላይ በተጠቀሰው የክርስቶስ ከሙታን መነሳት በሚያወሳው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያተኮረ እንደ ነበረም ታውቁዋል። ክቡራን እና ክቡራት ታዳሚዎቻችን ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት ያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህሮቼ እንድምን ዋላችሁ!

ዛሬ እዚህ የተገናኘነው ባከበርነው እና በስርዓተ አምልኮአችን እያከበርነው በምንገኘው በበዓለ ትንሣኤው ብርሃን ተሞልተን ነው። ስለዚህም የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርእስት ጀምረነው የነበረውን ትምህርተ ክርስቶስ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ቅዱስ ሐዋሪያ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው የመጀመሪያ መልእክቱ ምዕራፍ 151-5 ላይ ተመስርቼ ተስፋችን ስለሆነው እና ከሙታን ስለተነሣው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልነግራችሁ ወዳለሁ።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በቆሮንጦስ ማኅበረሰብ ውስጥ የነበረውን ጥርጣሬ እና ውይይት መሃል የነበረውን ችግር ለመፍታት ይፈልጋል። በዚህም መልእክት ውስጥ በቀዳሚነት ተጠቅሶ የምናገኘው የኢየሱስን ከሙታን መነሣት ሲሆን ምን አልባትም ይህ አርእስት በጣም አስፈላጊ እና ዋነኛው በመሆኑ ሊሆን ይችላል፣ እንዲያውም ቀሪዎቹ ነገሮች ሁሉ በዚህ ቅድመ ሐሳብ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

ጳውሎስ ለክርስቲያኖቹ እንደ አንድ ጥበበኛ የሆነ ሰው በመሆን ያቀረበላቸው አስተንትኖ ሳይሆን ነገር ግን በማይታበል ሁኔታ ተጨባጭ በሆነ ነገር ላይ ተመስርቶ ቀለል ባለ ሁኔታ በአንድ አንድ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ጣልቃ በመግባት በማያወላዳ መልኩ አስተንትኖውን ይጀምራል። ክርስትናችን የተወለደውም ከዚሁ ነው። ይህም አንድ ርዕዮተ ዓለም አይደለም፣ ይህም አንድ የፍልስፍና ስርዓትም አይደለም፣ ነገር ግን በመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የተመሰከረ ከአንድ አጋጣሚ የተጀምረ የእምነት ጉዞ ነው። ክርስቶስ ስለኃጢአታችን ሲል ሞቶ ተቀበረ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ እንዲሁም ለጴጥሮስ እና ለዐሣራ ሁለቱም ታዬ በማለት ጳውሎስ በዚህ መልኩ አጠቃሎታል። ሞቶ ተቀብሮ ከሙታን ተነስቱዋል መነሳቱም ለሌሎች ተገልጹዋል ስለዚህ ኢየሱስ በሕይወት አለ ማለት ነው። ይህም እውነት ነው። ይህም የክርስትና መልእክት ዋነኛው ፍሬ ነው።

በተለይም ሐዋሪያው ጳውሎስ የመጨረሻውን የፋሲካ ሚስጢር የሆነውን የኢየሱስ ከሙታን መነሣት ጠንከር ባለ ሁኔታ እንደ ገለጸ ሁሉ እኛም ይህንን የእምነታችን  ማእከል የሆነውን አጋጣም ማብሰር ይኖርብናል። ሞቶ ነበር ነገር ግን ተነስቱዋል። እምነታችንም የተወለደው በትንሣኤው ነው። ኢየሱስ ተሰቅሎ መሞቱ ከእምነት ጋር የተያያዘ ነገር ሳይሆን ነገር ግን እውነተኛ ታሪክ ነው። በአንጻሩ ግን ከሙታን መነሳቱ ግን እምነት ነው። እምነታችንም የተወለደው በፋሲካ ቀን ጎህ ሲቀድ ነው። ጳውሎስ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሳ ቡኃላ የተገለጸላችውን ሰዎች ይነግረናል። በዚህም ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ ቡኃላ የተገለጸላቸውን ሰዎች በመዘርዘር በመጀመሪያም ለጴጥሮስ፣ ለዐስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት፣ ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ተከታዮቹም እና ለያዕቆብ እንደ ተገለጸ በመተንተን በመጨረሻም እንደ ጭንጋፍ ለሆንኩኝ ለእኔ ታየኝ በማለት ለእኛ አንድ ትንሽ የማጠቃለያ ሐሳብ ይሰጠናል።

ጳውሎስ ይህንን ቃል የተጠቀመው ድራምዊ ከሚመስለው የግል የሕይወት ታሪኩ ላይ ተመርኩዞ ነው። የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አልንበረም። በእብሪት የተሞላ የቤተ ክርስቲያን አሳዳጅ ነበር እንጂ። በደማስቆ መንገድ ላይ ከኢየሱስ ጋር ከመገናኘቱ በፊት ጳውሎስ ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ መስሎትም ነበር። ለምድነው አሳዳጅ የነበረው ሐዋሪያ ሊሆን የቻለው? ምክንያቱ ክርስቶስ በሕይወት እንዳለ እና ከሙታን መነሳቱን በመረዳቱ የተነሳ ነው።   

ልክ እንደ ሌሎቹ ሐዋሪያት እምነት፣ ልክ እንደ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ልክ እንደ እኛ እምነት ይህም የጳውሎስ የእመነቱ መሰረት ነው። ይህ የክርስትና ሥር መሰረት መሆኑን ማሰብ እንዴት ደስ ይላል። እኛ እግዚኣብሔርን ለማግኘት የምናደርገው ፍለጋ ሳይሆን፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ እግዚኣብሔር እኛን ለማግኘት የሚያደርገው ፍለጋ ነው። ክርስትና ፀጋ እና ክስተት ነው፣ ስለሆነም ይህንን ድንቅ የሆነ ነገር መቀበል የሚችል ልብ ያስፈልጋል። የተዘጋ እና በምክንያት ብቻ የሚያምን ልብ ይህንን ድንቅ ነገር ማስተናገድ አይችልም፣ ክርስትና ምን መሆኑንም መረዳት አይችልም። ምክንያቱም ክርስትና ፀጋ ነው፣ ፀጋ ደግሞ መረዳት ይጠይቃል፣ በግንኙነቱም መገረም መቻልን ይጠይቃል።

ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን፣ ነገር ግን ኃጢአያተኛነታችን እንዲሁ ለይስሙላ በወረቀት ላይ ብቻ ሰፍሮ የሚቀር ከሆነ ቅዱስ ወንጌላችን እንደ ሚነግረን በፋሲካ እለት ጎህ ሲቀድ ወደ ኢየሱስ የመቃብሩ ስፍራ ሄደው የመቃብሩ ክዳን የነበረው ድንጋይ ተንከባሎ እንዳገኙት ሁሉ እግዚኣብሔር ለእኛም ያልጠበቅነውን ፍሬ እንደ ሚሰጠን ማመን ይገባናል። እያንዳዳችን በውስጣችን ይነስም ይብዛም የቀብር ሥፍራ ይገኛል። ወደ እዚያ በመሄድ እግዚኣብሔር ከሞት የመነሳት ብቃት እንዳለው ማየት ይጠበቅብናል። በዚያም ሁሉም የስቃይ፣ የሽንፈት፣ የጨለማ ቦታ አድርገው በሚቆጥሩበት ስፍራ ደስታ እና ሕይወት የሚገኝበት ሥፍራ ይሆናል። እግዚኣብሔር በጣም ደረቅ ከሚባሉ ድንጋዮች መኃል ውብ የሆነ አበባን ያበቅላል።

ክርስቲያን መሆን ማለት ስር መሰረቱን በሞት ላይ ማድረግ ማለት ሳይሆን፣ ጠላታችንን ድል የነሳው የእግዚኣብሔር ፍቅር ከእኛ ጋር መሆኑን ማወቅ ማለት ነው። ሐዋሪያው ጳውሎስሞት ሆይ ድል መንሻህ የት ነው? ሞት ሆይ ሰውን የምትጎዳበት ኃይልህ የት ነው?”ይለናል። በዚህ የፋሲካ ሰሞን ይህንን ድምጽ በልባችን እናስተጋባ።

 

20/04/2017 10:48