2017-04-18 08:02:00

2009 ዓ.ም. የፋሲካ በዓል ዋዜማ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በድምቀት ተከበረ።


በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በከፍተኛ ድምቀት ማክበራቸው ይታወቃል። የእዚህ በዓል አንድ ክፍል በሆነ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም. ቅዳሜ ምሽት የትንሣኤ ዋዜማ መስዋዕተ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ካህናት፣ ደናግላን፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት እንዲሁም ተለያዩ ሀገራት ልዑካን፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ አልፉል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

የዚህን ስብከት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ሰንበት ካለፈ በኋላ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጎሕ ሲቀድ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ ሄዱ (ማቴዎስ 281) ይህንን መንገድ እንዴት እንደ ተጓዙ መገመት እንችላለን፣ በጥርጣሬ እና ግራ በተጋባ ስሜት፣ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ለማመን የሚከብድ ነገር ነው በመለት ወደ ቀብር ስፍራ እንደ ሚጓዙ ሰዎች ዓይነት ጉዞ ነው ያደረጉት። የፊታቸውንም ገጽታ የገረጣ እና በእንባ የራሰ እንደ ነበር መገመት እንችላለን። እውነት ፍቅር ሞቱዋል ወይ? የሚል ጥያቄም ነበራቸው።

ጌታቸው በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የመጨረሻውን እስትንፋሱን ሲተነፍስ እንደ ነበሩ፣ የአርማቲያ ሀገር ሰው የነበረው ዮሴፍ በመቃብር ውስጥ ኢየሱስን ስያስቀምጠው ልክ እንደ ደቀ መዛሙርቱ ሴቶችም በእዚያው ተገኝተዋል። እነዚህ ሁለት ሴቶች ከእርሱ አልሸሹም፣ በጽናት ቁመውም ነበር፣ ሕይወትን እንደ አመጣጡ ተጋፍጠውትም ነበር፣ አድሎ ወይም የፍትህ መጓደል ምን ዓይነት መራር ነገር እንደ ሆነም አውቀውታል። በመቃብሩ ፊት ለፊት በሐዘን ተውጠው እናገኛቸዋልን፣ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጉዳይ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ብለው መቀበል አዳግቶዋቸዋል።

እኛ ይህንን ትዕይንት ለማሰብ በምንሞክርበት ወቅት የእነዛን ሴቶች የተለያዩ የፊት ገጽታዎችን በምናባችን በማሰብ፣ በአድሎ ምክንያት ከፍተኛ ሸክም እና አስከፊ ነገር ውስጥ የገቡትን የእናቶቻችን እና የአያቶቻችንን ፊት እንዲሁም የሕፃናት እና የታዳጊ ወጣቶችን ፊት መገመት እንችላለን። የእነዚህ ሴቶች የፊት ገጽታ ላይ በየከተማችን መንግዶች ላይ የሚገኙ በአስከፊ በሆነ ድኽነት የሚሰቃዩ፣ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የተበዘበዙ ወይም መጠቀሚያ የሆኑ ሰዎችን ፊት ያንጸባርቃሉ። በተጨማሪም ሀገራቸውን፣ ቤተሰቦቻችውን እና ቤታቸውን ጥለው ተሰደው በመምጣታቸው ብቻ ለንቀት የተዳረጉ ሰዎችን ፊትም ማየት እንችላለን። እጆቻቸው የተጨማደዱ እና የተተለተሉ በመሆናቸው ምክንያቱ ብቻ መገለላቸው እና ብቸኛ መሆናቸውን ፊታቸው ላይ ማንበብ እንችላለን። የእነርሱ ፊት የልጆቻቸው ሕይወት በከፍተኛ ሙስና ምክንያት መብቱን ሲገፈፍ እና ሕልማቸው ሲያጨልም  እንደ ሚያለቅሱ የሴቶች እና የእናቶች ፊት  ነጸብራቅ ነው። በየቀኑ በሚፈጸመው የራስ ወዳድነት ተግባር እነዚህን ሰዎች ይሰቅላል ከዚያም የሕዝቡን ተስፋ ይቀብራል። የእነ እዚያ ሁለት ሴቶች ፊት በየከተማችን መንገዶች ላይ የሚራመዱ ሰባዊ መብታቸው የተሰቀለባቸው ሰዎች ፊት ነጸብራቅ ነው።

የእናንተን እና የእኔን ፊት ጨምሮ የእነዚያ ሴቶች ፊት የብዙኃን ሰዎች ፊት ነጸብራቅም ነው። ልክ እንደ እነሱ እኛም ወደ ፊት እንድንራመድ የሚሰማን ስሜት እና እውነታው በዚህ መልኩ ሊጠናቀቅ ስለ ሚችል ራሳችንን ማግለል እንችላለን። እርግጥ ነው እኛ በውስጣችን የእግዚኣብሔርን ቃል ኪዳን እና የእግዚአብሔርን ታማኝነት በእርግጠኛነት እንሸከማለን። ነገር ግን ለራሳችን እና ለሌሎች ታማኝ ያልሆንባቸውን ብዙ አጋጣሚዎችን፣ ያደረግነውን ጥረት እና ጥረት አድርገን የተሸነፍንባቸውን ነገሮች ሁሉ ያካተተ ጠባሳ በፊታችን ላይ ይታያል። በልባችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ከእዚህ የተለየ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሳናስበው ተስፋ በመቁረጥ በመቃብር ውስጥ መኖርን እንለማመዳለን። ከእዚህም በከፋ መልኩ ይህ ነገር የሕይወት አንዱ ሕግ እንደ ሆነ አድርገን ራሳችንን እናሳምናለን፣ የማምለጫ መንገዶችን በመዘየድ ሕሊናችንን አደንዝዘን አምላክ በአደራ የሰጠን ተስፋ እንቀብራለን። ስለዚህም በአንድ በኩል ለእግዚኣብሔር ያለን ፍላጎት እና በሌላ በኩል ደግሞ ከጨለማ መላቀቅ  አቅቶን በእነዚህ ሁለት ነገሮች ውስጥ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተን ልክ እነዚህ ሁለት ማሪያሞች እንዳደጉት ዓይነት ጉዞ እኛም በዚህ መንገድ ላይ ብዙን ጊዜ እንጓዛለን። ጌታ ብቻ ሳይሆን የሞተው ተስፋችንም ከእርሱ ጋር ሞቶዋል።

እነሆ በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሰተ እነዚህም ሴቶች ልክ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር በእግራቸው ሥር ሆነ መሬቱን እንዳንቀጠቀጠው ዓይነት ስሜት ስለተሰማቸው በድንገት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገቡ።  በተጨማሪም አንድ ሰው ወደ እነርሱ መጥቶእናንተስ አትፍሩካላቸው ቡኃላእርሱ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቱዋልበማለት ጨምሮ ነገራቸው። ይህም መልእክት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ዛሬ እዚህ ቅዱስ የሆነ ምሽት ላይ በመድረስወንድሞች እና እህቶች በፍጹም አትፍሩ እርሱ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቱዋልይለናል። በመስቀል ላይ የጠፋው ሕይወት ዛሬ እንደ ገና እንደ አዲስ ይነቃል። የኢየሱስ የልብ ምት እንደ ስጦታ ተሰጥቶናል አዲስ አድማስም ከፍቶልናል። የጌታ የልብ ምት ተሰጥቶናል እኛም በአንጻሩም ይህንን የልብ ምት ወደ አንድ ለዋጭ ወደ ሆነ ኃይል እና አዲስ ስብእና እድንፈጥር እንዲረዳን ልንጠቀምበት ይገባል። ክርስቶስ በትንሣኤው የመቃብሩን ክዳን የነበረውን ድንጋይ ከፍቶታል፣ እኛንም ቆልፎ ከያዘን ስጋት፣ ደኅንነትን ከመግዛት ፍላጎት እና እኛ ሥልጣናችንን የሌሎችን ሰባዊ መብትን ለመግፈፍ ከመጠቀም ፍላጎቶቻችንም ነፃ ያወጣናል።

የካህናት አለቆች እና የሐይማኖት መሪዎች ከሮማዊያን ጋር በግጭት ላይ በነበሩበት ወቅት ሁሉንም ነገር በስሌት እንወጣዋለን የሚል እምነት ነበራቸው፣ ለዚህም የመጨረሻ የሆነውን ቃል ተናገሩ፣ ቃላቸውንም በተግባር በፈጸሙበት ወቅት እግዚኣብሔር በድንገት በመምጣት አበሳጭ የሆኑ ሕግጋታቸውን በመሻር አዳዲስ የሆኑ አጋጣሚዎችን ፈጠረ። እግዚኣብሔር ሊፈጥር እና አዲስ የሆነ የአጋጣሚ ዘመን የሆነውን የምሕረት ዘመን ልሰጠን እና ልገናኘን በድጋሚ ይመጣል።  ይህም ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረ ቃል ኪዳን ነው። ይህም እግዚኣብሔር በእርሱ ለሚያምኑ ሕዝቦቹ በድንገት የሚሰጣቸው ስጦታ ነው። ዝግጁ የሆነ ሕይወት ከእንቅልፉ ይነቃ ዘንድ በውስጣችሁ የተደበቀ የትንሣኤ ዘር ስላለ ደስ ይበላችሁ!

በዚህ ምሽት እንድናውጀው የተጠራነው የኢየሱስን የልብ ምት ነው። ኢየሱስ በሕይወት አለ። የመቅደላዊት ማሪያምና የሌላኛዋን ማሪያም ሰላም የፈጠነ እንዲሆን ያደረገው ይህ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት መልካም ዜናውን ለማብሰር የተመለሱት። የሐዘን ቁርበታቸውን እና ሐዘንተኛ ገጽታቸውን አውልቀው እንዲጥሉ ያደረገውም ይሄው ራሱ ነው። ወደ ከተማ ተመልሰው ከሌሎች ጋር እንዲገናኙ ያነሳሳቸውም ይህ ነው።

እኛም እንደ ሁለቱ ሴቶች የኢሱስን መቃብር አይተናል፣ ስለዚህም ወደ ከተማ ከእነርሱ ጋር እንድትሄዱ ጠይቃችኃለሁ። እኛ ሁላችን አካሄዳችንን ተመልክተን የፊታችን ገጽታ መቀየር ይኖርብናል። ከእነርሱ ጋር ተመልሰን በመሄድ የቀብር ስፍራ የሕይወት መደምደሚያ የመጨረሻው ስፍራ አድርጎ ለሚቆጥሩ ሁሉ፣ ሞት ከእዚህ ምድር የመገላገያው ብቸኛ መንገድ በሚመስልበት ስፍራ ሁሉ መልካም ዜናውን ለማብሰር እንውጣ። ለማብሰር፣ ለመካፈል፣ እውነት ምን እንደ ሆነ ለመግለጥ ጌታ በሕይወት መኖሩን ለመግለጽ እንውጣ።  ተስፋቸው የተቀበረባቸው የሚመስሉ ፊቶች፣ ሕልማቸው ለተቀበረባቸው፣ መብታቸው ለተቀበረባቸው ሰዎች ሁሉ እርሱ ኑዋሪ እንደ ሆነ እና እነርሱንም እንደ ሚያስነሳ ማወጅ ይገባል። መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ ላይ እንድንጓዝ የማንፈቅድለት ከሆንን እኛ ክርስቲያኖች አይደለንም ማለት ነው።

ሰለዚህም እንሂድ! በዚህ ድንገተኛ በሆነ አዲስ ንጋት እና ኢየሱስ ብቻ ሊሰጠን ከሚችለው አዲስነትን ለመቀበል እራሳችንን ዝግጁ እናድርግ። የእርሱ ርኅራኄ እና ፍቅር እርምጃችንን እንዲመራው እንፍቀድለት። የእርሱ የልብ ምት የደከመውን የልባችንን ምት ያፋጥነው ዘንድ እንፍቀድለት።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.