Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዓርብ ስቅለት ከተካሄደው የመስቀል መንገድ በመቀጠሉት ያደረጉት አስተንትኖ

ቅዱስነታቸው በኮሌሴሆም የዓርብ ስቅለት የመስቀል መንገድ በታደሙበት ወቅት ። - AP

15/04/2017 14:21

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች።

እንደ ሚታወቀው በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 6/2009 ዓ.ም.  የዓርብ ስቅለት ተዘክሮ ማለፉ ያታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም በሚገኘው ኮሌሴዩም በሚባል አከባቢ በሚገኘው ሥፍራ ከተደተገው የመስቀል መንገድ በመቀጠል ያደረጉትን አስተንትኖ እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ክርስቶስ በራሱ ሕዝብ ተክዶ እና ተሽጦ ብቻውን ቀረ። ክርስስቶስ በአለቆች ተላልፎ ተሰጥቶ በኃጢያተኞች ተዳኘ። በክርስቶስ የተጎሳቆለ ሰውነቱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፉበት፣ በሀር የተሠራ ልብስም አለበሱት።  ክርስቶስ ሆይ ገርፈውህ በሚያሳቅቅ ሁኔታ በሚስማር ቸነከሩህ። ክርስቶስ ሆይ ልብህን በጦር ወጉህ። ሞተህ የተቀበርክ ክርስቶስ ሆይ! አንተ የሕይወት እና የሕልውናችን አምላክ ነህ።

ክርስቶስ አዳኛችን ሆይ በዚህም ዓመት በፈጸምነው አሳፋሪ ተግባራችን ምክንያት አንገታችንን ደፍተን እና በተስፋ በተሞላ ልብ በድጋሚ ወደ አንተ መጥተናል። ውድመት፣ ጥፋት እና ዝቅጠት እነዚህ የተለያዩ አሳፋሪ ምስሎች በሕይወታችን ውስጥ የተለመዱ ክስተቶች ሆነው ቀጥለዋል። በእየቀኑ የሚፈሰው የሴቶች፣ የሕጻናት፣ የስደተኞች ደም እና በቆዳቸው ቀለም የተነሣ የሚሰደዱ ሰዎች ወይም ደግሞ በዘር ልዩነት እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ሚና እና በእምነታቸው ምክንያት የሚገለሉ ሰዎች ጉዳይ በመመልከት ዝም በማለታችን አፍረናል።

እንደ ይሁዳ እና ጴጥሮስ ስለሸጥንህ፣ ስለካድንህ እና ለኃጢያታችን ብለህ ብቻህን እንድትሞት በማድረግ ከማኅበራዊ ኃላፊነታችን መሸሻችንም አሳፍርኖል።

በፍትህ ፊት ቆመን ዝም በማለታችን፣ እጃችን በስንፍናና በስግብግብነት በመታሰሩ፣ የእኛ ከፍ ያለ ድምጽ የዋለው የእኛን ጥቅም ብቻ ለማስከበር በመዋሉ እና ለሌሎች ድምጻችንን ማሰማት በመፍራታችን፣ እግሮቻችን በክፋት መንገድ ላይ ለመራመድ በመፍጠናቸው እና ሽባዎች በመሆናችን አፍረናል።

ብዙን ጊዜ እኛ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ገድማዊያን እና ገዳማዊያት በሠራነው አሳፋሪ ተግባር የተነሳ የአንተ የሰውነት ክፍል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን በመጉዳታችን እና  መሰረታችን የሆኑትን ፍቅር፣ ጉጉት እና ተደራሽ መሆን እንዳለብን ዘንግተን ልባችንን እና ታማኝነታችንን በማጉደላችን አፍረናል።

በጣም ብዙ አሳፋሪ ነገሮች ፈጽመናል። ነገር ግን ልባችን በተስፋ ወደ አንተ በመቃተት እንደ ፈጸምነው ተግባር እንደ ማትዳኘን ተስፋ በማድረግ በአንተ ምህረት እንታመናለን። የእኛ የክህደት ተግባር የአንተን ፍቅር ጥልቀት አይክድም። በእኛ ልብ ድንዳኔ ምክንያት እናት እና አባት የሆነው የአንተ ልብ በፍጹም አይረሳንም።

የእኛ ስሞች የአንተ ልብ ውስጥ እና የአንተ የዓይን ብሌን ውስጥ እንደ ሚገኙም እርግጠኛ የሆነ ተስፋ አለን።  የአንተ መስቀል የደነደነ ልባችንን ቀይሮ ማለም፣ ይቅርታን ማድረግ እና መውደድ ወደ ሚችል ሥጋ ልብ እንደ ሚቀይረው፣ ይህንን ጨለማ የሆነ የመስቀል ምሽት በትንሣኤው ብርሃን እንደ ሚሞላው ተስፋ እንደርጋለን።

የአንተ እውነት በእኛ እውነት ላይ መሠረቱን እንዳላደረግም ተስፋ እንደርጋለን። በአንተ መስቀል ተስፋ ያደረጉ ወንድ እና ሴት ምዕመናን ተስፋ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፣ የቆሰለው ሰባዊነትህ እንደ እርሾ በመሆን ለሕይወታችን ጣዕም በመስጠት አዲስ የብርሃን አድማስ ይከፍትልናል።

የአንተ ቤተ ክርስቲያን አንተ በሕያዋንና በሙታን ላይ ልትፈርድ ዳግም በምትመለስበት ጊዜ በድል ትመለስ ዘንድ  መንገድ በማዘጋጀት የሰው ዘር ሁሉ ወደ አንተ ይመለስ ዘንድ በምድረ በዳ የሚጮህ ድምፅ ለመሆን ጥረት እንደ ምናደርግ ተስፋ እናደርጋለን።

ምንም እንኳን በጎነት ወይም መልካምነት ለጊዜው በግልጽ የተሸነፈ ቢመስልም መልካምነት አሸናፊ እንደሚሆን ተስፋ አለን!

የእግዚኣብሔር ልጅ የሆንክ፣ ኃጢያት ሳይኖርብህ ለእኛ ብለህ የተሰቃየህ ጌታ ኢየሱስ ሆይ! በአምላካዊ እና ንጉሣዊ ሰንደቅህ፣ በአንተ ሞት እና የክብር ምሥጢር ፊት፣ በመቃብርህ ፊት ለፊት ከነ ነውራችን እና ከነ ተስፋችን ተንበርክከን ደማችንን ከተወጋው ልብህ ውስጥ በሚመነጨው ውሃ እንድታጥበው፣ ኃጢያታችንን ይቅር እንድትለን እና በደላችንንም እንድትተውልን እንጠይቅአለን።

በነውጥ እና በጦርነት ምክንያት የተጎዱ ወንድሞችንም እንድታስታውስ እንጠይቃለን።

በራስ ወዳድነት እንድንታሰር ያደረገውን ሰንሰለት እንድትበጣጥስ፣ ሆን ብለን አይኖቻችንን ለጨፍንባቸው ጊዜያት ሁሉ እና ዓለማዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ በመቀመር ለኖርናባቸው ጊዜያት ሁሉ ይቅርታን እንጠይቅአለን።

ክርስቶስ ሆይ መቼም ቢሆን በመስቀልህ እንዳንፍር፣ እንድንበዘብዘው ሳይሆን እንድናከብረው እና እንድናመልከው አድርገን። ምክንያቱም አንተ በመስቀልህ  የእኛ ኃጢያትን አስፋሪ እንደ ሆነና የአንተ ፍቅር ታልቅ መሆኑን፣ ፍርዳችን ፍትሃዊ አለመሆኑን እና የአንተ ፍቅር ኃያል መሆኑን አሳይተህናል። አሜን።

 

15/04/2017 14:21