2017-04-14 16:21:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ለሕጽበተ እግር በፓሊያኖ ማረሚያ ቤት


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሕማማት ሳምንት ያንን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑ የሚያስታውሰን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመው የሕጽበተ እግር ስነ ሥርዓት ለመፈጸም በኢጣኢያ ፍሮሲኖኔ ክፍለ ሃገር ወደ ሚገኘው በብዛት ከባድ መዋቅራዊነት ባለው ሁነት በሚፈጸመው የተለያየ ከባድ ወንጀል ምክንያ ተከሰው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ተጸጽተው የሕግና ፍትህ ተባባሪ የሆኑት ነበር ወንጀል ቡድን አባላት የሚገኙበ የፓሊያኖ ወህኒ ቤት ጎብኝተው እዛው ለሚገኙት 70 እስረኞችና የወህኒ ቤት ጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት እንዲሁም ዋና አስተዳዳሪ በተገኙበት የሕጽበተ እግር ስነ ሥርዓት ፈጽመው ባሰሙት ስብከት፥

እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፡ በማገልገል ፍቅርን እንዘራለን

“በማገልገል ፍቅርን እንዝራ። ፍቅር የሚዘራው በማገልገል ነው። ኢየሱስ የጠራን እርሱ እንዳደረገው ላገልግሎት ነው። ስለዚህ እርሱ እንዳደረገው እናድርግ፡ ኢየሱስ በዓለም የነበሩት የእርሱ የሆኑትን እስከ ዘለዓለም አፈቀራቸው” ያሉት ቅዱስ አባታችን፥

ምንም’ኳ ኃጢኣተኞችም ብንሆንም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው

“ጌታችን ተክዶ ተላልፎ እንደሚሰጥ ያውቅ ነበር፡ በይሁዳ ተላልፎ እንደሚሰጥም ያውቅ ነበር፡ ተላልፎም ተሰጥቷዋል። ነገር ግን ለእኛ ያለው ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው። ለእያንዳንዳችን ሕይወቱን አሳልፎ ሰጠ፡ ዘለዓለማዊ ፍቅር። ቀላል ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም ሁላችን ኃጢኣተኞ ነንና ፍጹማን አይደለንም ውሱኖች ነን፡ ግድፈት አለብን ሌላም ሌላም። ሁላችን እናፈቅራለን ነገር ግን የአፈቃቀራችን ጉዳይ ከዚያ እስከ ዘለዓለም ከሚያፈቅረን ጌታ ለየት ያለ ነው። ምን ይመጣብኝ ይሆን ብሎ ሳያሰላስል የሚያፈቅር ፍቅር። ይኽ ጌታ ለእኛ ያለው ፍቅር ወሰን አልባ ነው፡ ጌታ ሆኖ እያለ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ።”

ኢየሱስ ወደ ዓለም የመጣው ሊያገለግል ነው ስለዚህ ር.ሊ.ጳ. ይኸንን ነው መተግበር ያለበት

ሕጽበተ እግር በዚያ ኢየሱስ በነበረበት ዘመን ከምሳና ከእራት በፊት በጠቅላላ ከማዕድ በፊት የሚፈጸም ልማድ ነበር ምክንያቱም ከነ አቧራህ እቤት አይገባምና። ስለዚህ እግር አጣቢዎች ተብለው የሚለዩ አገልጋዮች ነበር ሕጽበተ እግር የሚፈጽሙ። ይኸንን ልማድ እንዳለ ሆኖ ነገር ግን እግር የሚያጥበው አገልጋይ ሳይሆን ጌታው መሆን እንዳለበት ኢየሱስ ልማዱንና ባህሉን ቀየረ። ስምዖን ጴጥሮስ አይ አንተ እግሬን አታጥብም ያለበት ምክንያትም ወጉንና ባህሉን መሰረት በማድረግ ነበር። ኢየሱስ ግን ሊያገለግል እንጂ ሊገለገል እንዳልመጣ የሁሉም አገልጋይ ለመሆን ለእኛ ሕይወቱን ለመስጠት እስከ ዘለዓለም ሊያፈቅረን መምጣቱን ይገልጥላቸዋል።

“ዛሬ ወደ ወህኒ ቤቱ ስመጣ በመንገድ ያየኝ የነበረው ሕዝብ የቤተ ክርስቲያን መሪ ር.ሊ.ጳ. መጡ እያለ ሰላምታ ያቀርብልኝ ነበር። እትሳሳቱ የቤተ ክርስቲያን እራስና መሪ ኢየሱስ ነው። ስለዚህ እባካችሁ ይኸንን እናስተውል። … ቆሞሶች በዛሬይቱ ዕለት የምእመናን እግር ያጥባሉ። አዎ አገልጋይ መሆን በማገልገል ፍቅርን መዝራት።”

ሕጽበተ እግር በነበረ የሚፈጸም ባህላዊ ልማድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፍቅር ተጨባጭ ምልክት ነው

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እያንዳንዱ እስረኛ ይኸንን አገልግሎ አብነት በማድረግ እርስ በእርሱ መተጣጠብ ይሆርበታል። ምክንያቱም የፍቅር መግለጫ ተጨባጭ ምልክት ነውና። አንዳንዴ ደቀ መዛሙርት ቀዳሚውና የኋለኛው ማን ይሆን እየተባባሉ እርስ በእርሳቸው ይከራከሩ ነበር። ይኸንን ሹክቻ ያስተዋለው ኢየሱስ ግን የዓለም አመክንዮ ገልብጦ “የመጀመሪያ መሆን የሚፈልግ የመጨረሻ ይሁን። ትልቅ ለመሆን የሚፈልግ አነስ ይበል ትሁት ይሁን’”ይላል። “እግዚአብሔር ለእኛ እንዳደረገውና ለእኛ የሆነውን መሆን ይጠበቅብናል” ብሏል።

“እዚህ ያለነው ሁላችን እንዳችንም ሳይቀር ሚስኪን ነው። ጌታ ግን ታላቅና መልካም ነው። እንደ መሆናችን እንደ እኛነታችን የሚያፈቅረን አምላክ ነው። በዚህች ሰዓት እስቲ እግዚአብሔን ኢየሱስን እናስብ። ሕጽበተ እግር በነበረ ነበር የሚፈጸም ባህላዊ ልማድ ሳይሆን ያንን ኢየሱስ የፈጸመው ተጨባጭ የፍቅር መግለጫ ነው፡ ይኸን ከፈጸመ በኋላም የሕይወት ምግብና የሕይወት ውኃ ሆኖ ገዛ እራሱን ሰጠ። ስለዚህ ዛሬ እስቲ ስለዚህ ታላቅ ፍቅር እናስብ።”

ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከ70 በወህኒ ቤቱ ከሚገኙት እስረኞች ውስጥ ለተወጣጡ ሦስት ሴቶች አንድ የምስልምና እምነት ተከታይ የነበረው እ.ኤ.አ. ሰነ 2017 ዓ.ም. ሚሥጢረ ጥምቀት ተሰርቶለት የክርስትና እምነት የሚቀበለው አንድ አርጀንቲናዊ አንድ አልባኒያዊ አስር የጣሊያ ዜጋ የሚገኙበት በጠቅላላ ለ 12 እስረኞች ሕጽበተ እግር ፈጽመው እንዳበቁም ለሁም እስረኞችን አንድ በአንድ ሰላምታን አቅርበው ከወህኒ ቤቱ መስተዳድርና የጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባላት ጋር ተገናኝተው ሰላምታንንና የመልካም የህማማት ሳምንት ምኞት መግለጫ ተለዋውጠው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቅ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.