2017-04-14 14:26:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የጸሎተ ሐሙስ መስዋዕተ ቅዳሴን አሳረጉ


እንደ ምታወቀው የያዝነው የ2009 ዓ.ም ዓብይ ጾም በመገባደድ ላይ ይገኛል። እነሆ በአሁኑ ወቅት በሕማማት ሣማንት የመጨረሻዎች ቀናት ውስጥ እንገኛለን። በዚህ ሳምንት መገባደጃ ላይ ለክርስትና እምነታችን መሠረት የጣሉና የደኅንነታችን ምንጭ የሆኑ ሦስት ታላላቅ ተግባራት ይከናወናሉ። በትላንትናው እለት በጸሎተ ሐሙስ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ከመቀበሉ በፊት “እኔ ለእናንተ እንዳደረኩት እናንተም እንዲሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ስጥቻችኃለው” (ዩሐንስ 13፡15) በማለት የትህትናና የአገልግሎት ምልክት የሆነውን የእግር ማጠብ ስነ-ስርዓት የፈጸመበት፣ እንዲሁም “ሥጋዬን የሚበላና ደሜንም የሚጠጣ የዘልዓለም ሕይወት ያገኛል” በማለት ቅዱስ ቁርባንን ለእኛ የሕይወት መብል እንዲሆን የመሠረተበት፣ በተጨማሪም “ይህንን ለእኔ መታሰቢያ አድርጉ” በማለት እርሱ የጀመረውን የጽድቅ መንገድ ቅዱሳን ሐዋሪያቱ ያስቀጥሉ ዘንድ የክህነት ስላጣንን ለሐዋሪያቱ ያስረከበበት ቀን ተከብሮ አልፏል።

የዚህን መረጃ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ይህ የጸሎተ ሐሙስ ቀን በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 5/2009 ዓ.ም. በሮም ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙ ካህናት፣ ገዳማዊያን/ዊያት፣ ምዕመናን፣ እንዲሁም  መላው የእግዚኣብሔር ሕዝብ እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በተገኙበት በቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በድምቀት ተከብሮ አልፉዋል።

የእለቱ ስርዓተ ዓምልኮ አንድ ክፍል የነበረው የእግር ማጠብ ስነ-ስርዓት የተከናወነው በቅዱስ ጴጥሮ ባዚሊካ ሳይሆን ቅዱስነታቸው የመስዋዕተ ቅዳሴን በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ካሳረጉ ቡኃላ በሮም አውራጃ ውስጥ በሚገኘው ወደ አንድ  ማረሚያ ቤት በመሄድ የሕግ ታራሚዎችን እግር አጥበዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተካሄደው መስዋዕተ ቅዳሴ ለምስጢረ ቀንዲል፣ ለምስጢረ መሮን እና ለምስጢረ ጥምቀት አገልግሎት የሚውሉ የወይራ ዘይት ብሩኬም በቅዱስነታቸው መሪነት ተካሂዱዋል።  በእለቱም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ቃል እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድኾች ወንጌልን እድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፣ ለታሰሩ መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨነቁትን ነፃ እንዳወጣ፣ የተወደደችሁንም የጌታ ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል” (ሉቃስ 418) በመንፈስ ቅዱስ የተቀባው ኢየሱስ ለድኾች መልካም ዜናን አምጥቱአል።  በምሕረት ዘይት ኃጢአታቸው የተሰረዬላቸው ኃጢአተኛ የነበሩ ሰዎች ወደ ደስተኛነት ቀይሮ እና እነርሱም በተራቸው ሌሎችን ይቀቡ ዘንድ በቅድሚያ መንፈሳዊ ፀጋቸውን በተልዕኮ ዘይት በመቀባት እንዲሄዱ  በወንጌል ደስታ የተሞላ ዜና አመጣልን።

ካህን ልክ እንደ ኢየሱስ ይህንን መልእክት በመላው ማንነቱ ያስተላልፋል። ከተቻለ አጠር ባለ መልኩ በሚሰብክበት ወቅት ይህንን ስብከት በደስታ በማድረግ እርሱን በጸሎቱ ወቅት ልቡን እንደ ነካው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩም የእግዚኣብሔር ቃል የሕዝቡን ልብ እንዲነካው ያደርጋል። እንደ ማንኛውም ዓይነት ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር ካህን  ሰዎችን ደስተኛ ሊያደርግ የሚችለው መልእክቱን በሁለንተናው ስያስተላልፍ ብቻ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው ደስታ የሚገኘው እና ለሌሎችም ልናካፍለው የምንችለው ትናንሽ በሚባሉ ነገሮች አማክይነት ነው። አንድ ትንሽ እርምጃ ወደ ፊት በመራመድ ስልካችንን አንስተን ከአንድ ሰው ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ በምንይዝበት ወቅት እና በትዕግስት ለሌሎች ሰዎች ጊዜያችንን በምንሰዋባቸው ወቅቶች ሁሉ፣ በባድማ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ቢሆን በዚህ መልኩ እኛ የአምላክ ምሕረት ተትረፍርፎ እንዲፈስ ማድረግ እንችላለን።

መልካም ዜናየሚለው ሐረግ በተዘዋዋሪቅዱስ ወንጌልእንደ ማለት ይቆጠራል። እነዚህ ቃላት ወደ አንድ በጣም አስፈላጊ ወደ ሆነ ነገር ያመለክታሉ፣ ይህም በቅዱስ ወንጌል የሚገኝ ደስታ ነው። ቅዱስ ወንጌል መልካም ዜና የሆነበትም ምክንያት ሕልውናው ወይም ደግሞ ማንነቱ የደስታ መልእክት ስለሆነ ነው።

መልካም ዜና በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የምናነበው ውድ የሆነ እንቁ ነው። ይህም አንድ ግዑዝ የሆነ ነገር ሳይሆን ተልእኮ ነው። ይህምአስደሳች እና አጽናኝ የሆነ የወንጌላዊነት ደስታልምድ ላለው ማንኛውም ሰው ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው። ይህ መልካም ዜና የሚወለደው በቅዕባ ቅዱስ አማክይነት ነው። ኢየሱስ የመጀመሪያውንታላቅ የሆነውን የክህነት ቅዕባ ቅዱስንየተቀበለው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በማሪያም ማሕጸን ውስጥ በነበረበት ወቅት ነበር። የዚህም መልካም ዜና ብስራት ቅድስት ድንግል ማሪያምን የምስጋና መዝሙር እንድትዘምር አነሳስቱአታል። እጮኛዋ የነበረውን የዮሴፍን ልብ ደግሞ በሚያስፈራ ዝምታ ውስጥ ከቶታል፣  በእናቱ በኤልሳቤጥ ማሕጸን ውስጥ የነበረውን ዩሐንስን ደግሞ በደስታ እዲቧርቅ አድርጎታል።

በዛሬው ወንጌል ደግሞ (ሉቃስ 4 16-21) ኢየሱስ ወደ ናዝሬት በተመለሰበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ወርዶበደስታ ዘይት ሲቀባውእናያለን። በእዛች ትንሽዬ ከተማ የምትገኘውን ቤተ መቅደስ የደስታ የመንፈስ ቅባት ስያድሳት እንሰማለን።

መልካም ዜና! በአንድ ቃል ሲጠቃለል ወንጌል ይባላል። ቃሉ ራሱ በሚነገርበት ወቅት ደስታን እና ምሕረትን በማምጣት እውነት ይሆናል። ድርድር የማያስፈልገው እውነት፣ ምንም ቅድመ ሁኔታ ያልተቀመጠበት እና ለኃጢአተኞች ሁሉ የሚሰጥ ምሕረት፣ ግላዊ የሆነና ለሁሉም ክፍት የሆነ ደስታ እነዚህን ሦስት የወንጌል ፀጋዎችን በፍጹም መነጣጠል የለብንም።  

የመልካም ዜናው እውነት በመጽሐፍ መልኩ ታትሞ ምቹ በሆነ መንገድ በመቅረቡ ምክንያት በሰዎች ሕይወት ውስጥ ተጨባጭ የሆነ ቅርጽ የሌለው ተደርጎ ተቆጥሮ የሚወሰድ ውስብስብ ነገር አይደለም።

የመልካም ዜናው ምሕረት ኃጢአተኞችን ከስቃያቸው ውስጥ ለማውጣት እጁን የማይዘረጋና በለውጥ ጎዳና ላይ እንዲራመዱ የማያደርጋቸው የሐሰት ትዕይንት ፈጽሞ ሊሆን አይችልም።

ፈጽሞ ግላዊ በሆነ መልኩ ደስታን የሚገልጽ ከመሆኑ የተነሳ ይህ መልእክት ፊቱን ያጠቈረ ወይም ግዴለሽ መሆን ፈጽሞ አይችልም። ይህምከትናንሾቹ አንዱ እንኳን መጥፋት የለበትም የሚለው የአባታችን ደስታ ነው ድኾች መልካም ዜና ሲበሰርላቸውና ትንንሽ የተበላቱም በፊናቸው የተቀበሉትን መልካም ዜና ለማብሰር መውጣት መቻላቸው በራሱ ኢየሱስን ደስ የሚያሰኘው ጉዳይ ነው።

በወንጌል የሚገኝ ደስታ በጣም ልዩ የሆነ ደስታ ነው። በጥቅሉደስታየምልበት ምክንያት እንደ የወቅቱ፣ እንደ እየግለሰቡ እና እንደ እየባሕሉ መንፈስ ቅዱስ ለመገለጽ ፍቃደኛ በሆነበት መንገድ ላይ ተመስርተን ስንመለከተው ደስታ በጣም ብዙ እና የተለያየ ዓይነት መልክ ያለው በመሆኑ የተነሳ ነው። ወድ ካህናት ወንድሞቼ መልካም ዜና ሳይጎመዝዝ በአንጻሩም በደንብ በርክቶ መልካ ጣዕምሙን ይዞ እንዲቆይ የሚያደርገውን የአዲስ አቁማዳ ገጽታ ወይም አምድ የሆኑትን ሦስት ነገሮች ላካፍላችሁ እወዳለሁኝ።

በቃና ዘገሊላ ሰርግ ወቅት (ዩሐንስ 26) የነበሩትን በድንጋይ የተሰሩ ጋኖች እንደ መጀመሪያው የመልካም ዜና አምድ አድርገን ልንወስደው እንችላለን።  በአንድ በኩል እነዚህ ከድንጋይ የተሠሩ ጋኖች እመቤታችን ድንግል ማሪያም ራስዋ ፍጹም መሆኑዋን ያንጸባርቃሉ። ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚነግረን አገልጋዮቹ እነዚህን ጋኖችእስከ አንገታቸው ድረስ” (ዩሐንስ 27) ውሃ ሞሉዋቸው። እኔ እንደ ማስበው ምን አልባት ከእነዚህ አገልጋዮች አንዱ ማሪያምን እየተመለከተውሃው በቂ ነው ወይ?’ በሚላት ጊዜ እርሷም አንድ ጠብታ እንዲጨምር የነገረችው ይመስለኛል። ማሪያም ቀጣይነት ባለው ደስታ የምትሞላን አዲስ አቁማዳ ናት። እርሷእኔ የአብ የእጁ ሥራ ውጤት ነኝ በማለት የውዳሴ መዝሙር ዘምራለች እርሷ ንጹሕ በሆነው ማሕጸኗ ውስጥ የሕይወት ቃል የሆነውን ከጸነሰች ቡኃላ ዘመዷ የሆነችውን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት እና ለመርዳት ሄደች። እርሷቀጣይነት ያለው ምልአትየፍርሃት ፈተናዎችን፣ እስከ አንገታችን ድረስ በፀጋ እንዳንሞላ ወደ ኋላ ከሚጎትቱን ፈተናዎች፣ ልባችንን አደንድኖ ጠፍሮ ይዞን ሌሎችን በደስታ እንዳንሞላ ከሚያደርገን ፈተናዎች ውስጥ እንዳንገባ ይረዳናል።በወንጌል የሚገኝ ደስታ ልባችንን በመሙላት ኢየሱስን ለሚገናኙ ሰዎች ሁሉ ነብስ እንዲዘሩ ያደርጋቸዋል

ሁለተኛው የመልካም ዜናው አምድ ደግሞ አንዲት የሰማሪያ ሀገር ሴት በእኩለ ቀን ጸሐይ ከእንጨት የተሠራ ማንጠልጠያ ያለው የዋሃ መቅጃ ይዛ ውሃ ልትቀዳ የሄደችውን ሴት ይመስላል (ዩሐንስ 45-30) ይህም ወሳኝ የሆነና ተጨባጭ ሁኔታዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ለእኛ ይነግረናል። የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆነው ጌታ ውሃ ከጉድጓድ አውጥቶ ጥሙን ማርካት የሚያስችለው ሁኔታ ላይ አልነበረም። ስለዚህም ሳምራዊቷ ሴት በያዘችው የውሃ መቅጃ የጌታን የውሃ ጥም መቁረጥ ችላለች። በተጨማሪም ተጨባጭ በሆነ መልኩ ኃጢአቱዋን በመናዘዙዋም ጥሙን ቆርጣለች። መንፈስ ቅዱስ የዚህችን ሳምራዊት ሴት ነብስ በምሕረቱ በማናወጥ፣  በእዛች ትንሽ ከተማ የምኖሩት ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር እንዲኖር እስከ መለመን ድረስ እንዲደርሱ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞሉ አድርጎዋቸዋል።

በተጨማሪም ጌታተጨባጭ በሆነ መንገድ አካታች የሆነበእዛች ሳማሪውት ሴት ሕይወት ውስጥ የምናየው አዲስ አቁማዳ ደግሞ እማሆይ ትሬዛ ናቸው። ወደ እርሱ እንድትቀርብ በመጥራትውሃ አጠጭኝአላት።ልጄ ሆይ ነይ! ድኾች ወደ ሚገኙበት ቦታ ውሰጅኝ፣ ስለ ማያውቁኝ ወደ እዛ ብቻዬን መሄድ አልችልም። አያውቁኝም ለእዛም ነው የማይወዱኝ። ወደ እነርሱ ውሰጅኝአላት። እማሆይ ትሬዛ ለፈገግታቸው ምስጋና ይግባውና ተጨባጭ  በሆነ መልኩ አንድ ድኻ ሰው በመርዳትና ቁስሉን በመንካት መልካሙን ዜና ለሁሉም አበሰረች።

በሦስተኛ ደረጃ የምናገኘው የመልካም ዜና መገለጫ አምድ ጥልቀቱ ሊለካ የማይችለው ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ እንዲቀርቡ ያደረገው የተወጋው የኢየሱስ ልብ፣ የዋህነቱ፣ ትህትናውና ድህነቱ ነው። ከእርሱ የምንማረው ነገር ቢኖር ደስታን ለድኾች ማብሰር የምንችለው በክብር፣ በትህትና እና የዋህ በሆነ መንገድ ስንቀርባቸው ብቻ መሆኑን ነው። ወንጌላዊነት በትዕቢት ሊተገበር በፍጹም አይችልም። የእውነተኛነት አቋማችን ግትር ሊሆንም አይገባም። መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረን እና የምያውጀውየእውነትን አካታችነትነው። መንፈስ ቅዱስ በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ በምንገባበት ወቅት ለጠላቶቻችን ምን ማለት እንደሚገባን እና በዚያም ወቅት እያንዳንዱን እርምጃችንን ብሩህ በማድረግ ወደ ፊት እንድንጓዝ ይረዳናል። ይህ የዋህነት እና አካታችነት ለድኾች ደስታን ይሰጣል፣ ኃጢአተኛውን ያነቃዋል፣ ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸው  ሁሉ እፎይታን እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።

ውድ ካህናት በእነዚህን ሦስት አቁማዳዎች ላይ በምናሰላስልበት ወቅት እና ከእነርሱ በምንጠጣበት ወቅት እመቤታችን በመላው ሕይወቱዋ ያንጸባረቀችውንተጨባጭ የሆነ አካታችነትንበሳምርዊቷ ሴት ታሪክ፣ በቃላት ሊገለጽ በማይችለው በመንፈስ ቅዱስ ትሕትናና ከተወጋው ከኢየሱስ ልብ በሚመነጨው  መልካም ዜናቀጣይነት ባለው መልኩ ምልአትውስጥ ሆነን እንዲያገኘን መጸለይ ይገባናል።   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.