2017-04-07 17:00:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በአርጀንቲና በጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ለተጎዱት ሁሉ መንፈሳዊ ቅርብታቸውን አረጋገጡ


በአርጀንቲና ከባለፈው ረቡዕ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ በመጣል ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ መንፈሳዊ ቅርበታቸውን በማረጋገጥ ለተጎዳው ሕዝብ እርዳታ በማቅረቡ ሂደት ሁሉም በተለይ ደግሞ የተለያዩ ሃይማኖቶች የወንድማዊ ትብብር ጥሪ በተግባር እንዲመሰክሩ አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍለ መግለጫ ይጠቁማል።

ተከስቶ ባለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ በአርጀንቲና ደቡባዊ ክልል በሚገኘው የኮሞዶሮ ኢቫዳቪያ አካባቢ እጅግ የተጠቃ መሆኑ ሲነገር ከሰባት ሺሕ በላይ የሚገመቱ ሰዎች በመኖርያ ቤት መደርመስ ምክንያት ለሞት አደጋ እንዳይጋለጡ አቢያተ መኖርያቸውን ለቀው እንዲወጥ መደረጋቸው ለማወቅ ሲቻል። አካሁን ድረስ ሁለት ሺሕ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው ካካባቢው የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

ቅዱስ አባታችን ይድረስ ለሳንታ ፈ ደ ላ ቨራ ክሩዝ ርእሰ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ለብፁዕ አቡነ ኾሰ ማሪያ አራንሰዶ ባስተላለፉት መልእክት፥ ሃይለኛው ዝናብ ያደረሰው ጉዳት እጅግ እንዳሳዘናቸውና ለሁሉም ለተጎዱት ቤትን ንብረታቸውን ላጡት ሁሉ መንፈሳዊና ሰብአዊ ቅርበታቸውንም ማረጋገጣቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስነታቸው ያረጋገጡት ቅርበት በሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኾሰ ማሪያ አራንሰዶ በኩል ለተጎዳው ሕዝብ እንዲደርስም አደራ እንዳሉና ለብዙ ዓመት ጥረህ ግረህ የያፈራኸውን በላብህ ውጤት የገነባኸው ንብረት የቤተሰብ መዘክር ሁሉ ባንድ አፍታ ሲወድም ማየቱ በእውነቱ በጣም የሚያሳዝ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉንም በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸውና ሁሉም የተጎዳውን ሕዝብ ለመርዳት በግብረ ሠናት የተጠመዱትን ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ምእመናንና ቁምስናዎችን እንዲሁም የአገሪቱ መንግሥት የክልሉ የመንግሥት ተጠሪዎችንም በማበረታታት ሁሉም ለተጎዳው ሕዝብ ቅርብ እንዲሆን አደራ እንዳሉም ይጠቁማል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.