2017-04-05 16:49:00

የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማሕበር መግለጫ


 ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልእክት ዘንድ እርሱም የለፈብቭራውያን ካህናት ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውህደት ላላቸው ካቶሊካውያን ምእመናን ምሥጢረ ንስሐ መስራት ይችላሉ በማለት ፍቃድ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ይኸንን በማስከተልም ቅዱስነታቸው የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ ወንድማዊ ማኅበርሰብ ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ለሆኑት ምሥጢረ ተክሊል ለመቀበል ለሚሹት ተገቢ የምሥጢረ ተክሊል ሐዋርያዊ ግብረ

ኖልዎ በብቃት ለተከታተሉት መሥራት ይችላሉ በማለት የሰጡት ፈቃድ ማእከል በማድረግ የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተና በዚህ ቅዱስ ማኅበር ጋር ጥብቅ ትሥሥር ያለው ጳጳሳዊ Ecclesia Dei-የእግዚኣብሔር ቤተ ክርስቲያን”  ተንከባካቢ ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ገርሃርድ ሉድዊግ ሚዩለርና በዚህ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳዊ ማኅበር ዋና ጸሓፊ በኢጣሊያ የባኞረጆ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጉይዶ ፖዛ ፊርማ የተኖረበት ይድረስ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከታቸው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በሚል በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስም ባስተላለፉት ማብራሪያ፥ በዚያ ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ውህዳት ባላቸው ብፁዓን ጳጳሳት ሐዋርያዊ እንክብካቤ ሥር በሚመሩት ሰበካዎችና ቅምስናዎች የሚታቀፉት ምእመናን በክልላቸው ከሰበካቸው የተወከለ አንድ ሕገ ቀኖናዊ ሕጋዊነት ለበስ የሆነ ካህን ሰበካውን ወክሎ በልኡክነት በተገኘበት የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ ወንድማዊ ማኅበረሰብ ካህናት አማካኝነት ካቶሊካውያን የሚቀበሉት ምሥጢረ ተክሊል የተፈቀደና ሕጋዊነት እንዳለውና ቃል ኪዳኑን ያሰሩትም ምእመናን የጋብቻ የምስክር ወረቀት በቀጥታ ለክልላቸው ሰበካ ወይንም ቆሞስ  በማቅረብ አለ ምንም ችግር የተሰራላቸው ምስጢረ ተክሊል ሕጋዊና ቅቡልነት በሰበካቸው እንደሚረጋገጥላቸው ነው ሲል፡ ነገር ግን  ሰበካውን ወክሎ ለመሳተፍ የሚችል ካህን ከሌለ ደግሞ በቀጥታ በለፈብሪያን ካህናት ምሥጢረ ተክሊል የተሰራላቸው ካቶሊክ ምእመናን በሰበካቸው ለሚገኘው መንበረ ጳጳስ የጋብቻውን ምስክር ወረቀት በማቅረብ ወይንም ማሰተላለፍ እንደሚጠበቅባቸው ተመልክቶ ይገኛል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም መግለጫው በትክክል ውሳኔው ግልጽ እንዲሆን ፥ ይኽ ቅዱስ አባታችን የሰጡት ልዩ ፈቃድ የቅዱስ ፒዮስ አስረኛ ወንድማዊ ማኅበረሰብ ከኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በመነጠሉና ይከንን ተከትሎም ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ውህደት የሌለው በመሆኑ ይኽ ቅዋሜው በሕገ ቀኖና መሠረት  ከሕግ ውጭ ነው የሚለው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ እንደተጠበቀ ነው የሚል ማብራሪያ ያካተተ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.