2017-04-03 16:52:00

አራተኛ ስብከት ዘዓቢይ ጾም፥ አባ ካንታላመሳ፤ የክርስቶስ ሞት የፍቅር ዋስትና ነው


የካፑቺን ንኡሳን አኃው ማኅበር አባል ሰባኬ ቤተ ጳጳስ አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና መላ የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጳጳሳዊ አቢያተ ምክር እንዲሁም ቅዱሳን ማኅበራት ሊቀ መናብርትንና ኅየንተዎችን ያሳተፈው በሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው እመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት የዓቢይ ጾም አራተኛ ስብከት ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ ገለጡ።

አባ ካንታላመሳ ያቀረቡት የዓቢይ ጾም አራተኛው ስብከት በክርስቶስ ምስጢረ ትንሣሴ ላይ ያማከለ ሆኖ የክርስቶስ ትንሣኤ ዘመዓለማዊ ሕይወት እንዴት ይሆን በሚለው ጥያቄ በማሰላሰል የሚታሰብ መሆን እንደሌለበት አሳስበው የስብከታቸውን አንኳር መንፈስ ቅዱስ ወደ የክርስቶስ የትንሣሴ ምስጢር የሚያቀርበንና የሚያስገባን ነው የሚል መሆኑ የገለጡት የቫቲካን ርዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ አያይዘው፥

“ትንሣኤ እንደ ታሪካዊ ክዋኔ (በታሪክ የተፈጸመ እውነት)፤ ሐዋርያት በሚያሳዝነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ፊት፤ የኢየሱስ ጉዳይ እንደ ተደመደመ በመቀበል የእምነት ሞት፡ እምነት የሞተበት ሁነት በማድረግ ያስቡታል። የሚያስገርመው ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ እንዲህ መሆኑ ይቀርና ስለ ክርስቶስ ሲታሰሩ ሲሰቃዩ ስለ እርሱም ሲሰዉ ማየቱ ነው። ምክንያቱም የሞተው ኢየሱስ ተነሥቷል ተገልጦላቸዋል አይተውታልምና። ትንሣኤ ልዩ ቀልብ ታሪካዊ ክዋኔ ነው። ልክ እንደ አንድ ባህርና መሬት የሚለያይ ምልክትም ነው። እንዲህ ሲባልም የኢየሱስ ትንሣኤ በታሪካ ውስጥም ነው ከታሪክ ውጭም ነው ለማለት ሲሆን፡ ይኽ ደግሞ ትንሣኤ በቀጥታ ከግዜና ከቦታ ጋር አጣምሮ በሰብአዊ ቃላት ልትመሰክረው አዳጋች  ያደርገዋል። በዚህ ምክንያትም ከሞት የተነሣው ኢየሱስ እንጂ ከሞት ሢነሳ ያየው ማንም እንደሌለ እንረዳለን።”

ትንሣኤ በታሪክ ሁነት ተደግፈህና ታሪካዊነቱን ልትተርክ ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ። የመጀመሪያው ይላሉ አባ ካንታላመሳ፥

“ያልተጠበቀ ሊገለጥ የማይቻል ወደ የሰማዕትነት የሚያደርስ ጽኑና ቆራጥ የሐዋርያት እምነት፡ ማለትም ሐዋርያት በራሳቸው ያስተላለፉት እርሱም ከትንሣሴ በፊት ስለ ነበረው ኢየሱስ ሳይሆን ከትንሣኤ በኋላ ህያው ስለ ሆነው ኢየሱስ ያላቸው ተመክሮ እንዲኖር የሚያደርገው እምነት የክርስቶስ ትንሣኤ ነው፡ ስለዚህ በኢየሱስ ሕይወት የተረጋግጠው ትንሣኤ የእግዚአብሔር እሺታ ነው። በዚህ በምንኖርበት ዘመን ብዙ የሚያሳዝን ፍጻሜዎች እንሰማለን። ይኽ ደግሞ ብዙ ሰዎች ቅን ብለው ለሚያስቡት ነገር ግን ለተሳሳተ ዓላማ እራሳቸውን ይሰዋሉ። የእነርሱ ሞት የሚመሰክረው ነገር ቢኖር የሞቱለት ዓላም ብቻ ነው። የኢየሱስ ሞት ግን እርሱ ላለው እውነት ዋስትና ሳይሆን የፍቅር ተመክሮ ነው። ይኽ ደግሞ እውነት ነው ምክንያቱም ገዛ እራሱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት ይልቅ የሚበልጥ ፍቅር የለምና።”

“የክርስቶስ ትንሣኤ” ይላሉ ሰባኬ ቤተ ጳጳስ፥ የሚመለከተንና የእኛ ከሞት የመነሣት ተስፋ መሠረት ስለ ሆነ ለእኛ ሚሥጢር ነው። በአንድ በኵል የእግዚአብሔር ከኃሌ ኩሉነቱን እርግጠኛነቱን የሚከውን ሲሆን በሌላው ረገድ ደግሞ የዚያ ብቃት አልቦና ኢፍትሓዊ የሆነውን የምድራዊውን ካሳ የሚያነጽር መሆን ተንትነው፥

“የኢየሱስ ትንሣሴ ተከዋኒነቱ የሚገለጥበት አኳሃን ያንን እግዚአብሔር ‘በኮሬብ ተራራ ለሙሴ የአግዚአብሔር መልአክ በእሳት   ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል’ የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ መሆኑ የመገለጡ ሁነት የሚያመልክት ነው። የህያዋን አምላክ! በክርስቶስ ትንሣኤ የምታምን ከሆንክ በሙታን ትንሣኤ ታምናለህ ማለት ነው፡”

እንዳሉ አስታውቋል።

“በክርስቶስ ትንሣሴ አምናለሁ የሚለው የክርስትናው እምንት ያንን በሰው ልጅ ልብ ውስጥ በኑባሬ ላለው ከሞት የመነሣት ባህርያዊ ፍላጎት (መሞት ያለ መፈለግ የዘለዓለማዊነት ባህርያዊ ፍላጎት) መልስ ነው። ጳውሎስ እንደሚለውም ‘በእዚህ ድንኳን (ሥጋ) እስካለን ድረስ ከብዶን እንቃትታለን ምክንያቱም ሟች የሆነው በሕይወት እንዲዋጥ ሰማያዊውን መኖሪያችንን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንፈልግም (2ቆር. 5,4) ነው። ይኽ ደግሞ ያ እኛ የምንመኘው የሁለተናንችንና ምሉእነታችን ትንሣኤ ‘ሥጋችንና ነፍሳችንን’ የሚያጠቃልል ትንሣኤ ነው። ሟቹ ሰውነታችን ከሕይወት ጋር ተዋህዶ ኢሟችነትን እንዲለብስ የሚያረጋግጥ ነው።”

“ያ በእኛው ውስጥ ያደረው መንፈስ” ይላሉ አባ ካንታላመሳ፥ “ከዚያ ከመንፈስ ኢሟችነት በላይ በህልዉና በመጻኢው ሕይወታችን መካከል ያለው የሕይወት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው” ብዙውን ጊዜ ይኸንን ጉዳይ ለመግለጥ እንደ ምሳሌ የተፈጥሮ ባህርያትን ስንጠቀም፡ “አንድ ዛፍ የሚያድግ ዘር ነው፥ ያ ዘር በክረምት ወቅት ይሞታል በጸደይ ወራት ደግሞ ያብባል (ይነሣል)” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ አያይዘው፥

“ያ መጠቅ ከነገር በላይ የሆነው ማዶ የሚኖረው ሁኔታችን ልናውቀው የማይቻለን ሚሥጢር ነው። እንዲህ ያደረገውም እግዚአብሔር ሚሥጢር አድርጎ ከእኛ ደብቆ ለማቆየት ብሎ ሳይሆን፡ ሊወክለው የሚችል መሠረታዊ መመዘኛ መሠረት በማድረግ ለመግለጡ ስለማይቻለን ነው፡ ሁሉ አገላለጣችን ከጊዜና ከቦታ ግር ጥምረት ያለው በመሆኑ ከጊዜና ከቦታ ውጭ የሆነ ተጠቃሽ ነገር በመጠቀም ለመግለጥ ችሎታው የለንም። በጊዜና በቦታ ነው ያለነው፡ ምክንያቱም ዘለዓለማዊነት በገዛ አራሱና ለገዛ እራሱ አካል አይደለም። እንዲሁም እስከ ወሰን አልቦነት የሚራዘም ጊዜ ማለትም አይደለም። ዘለዓለማዊነት ወሰን አልቦ ማለት አይደለም። ዘለዓለማዊነት የእግዚአብሔር መሆናዊ አገባብ ነው፡ (የእግዚአብሔር መሆን) ወይንም ደግሞ የእግዚአብሔር ህላዌ አግባብ ነው፡ ዘለዓለማዊነት እግዚአብሔር ማለት ነው። ወደ ዘለዓለማዊነት መግባት ማለት ደግሞ በጸጋ የእግዚአብሔር ህላዌ (የእግዚአብሔር የመሆን አግባብ) ተካፋይ መሆን ማለት ነው።”

በማለት ገልጠው፥ “እጅግ አስፈላጊነት ያለው ጉዳይ፤ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዴት ይሆን ብለን ማሰላሰል ሳይሆን ወደ ዘለዓለማዊነት የሚያደርሱንን ከገሮች መፈጸም ነው። ዕለታዊና አሁናዊው ሕይወታችን ወደ ዘለዓለማዊው ሕይወት የሚሸኝ እርምጃ ይሁን” በማለት አባ ካንታላመሳ ያቀረቡት የአቢይ ጾም አራተኛውን ስብከት ማጠቃለላቸው አስታውቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.