2017-03-30 11:13:00

በኢየሱስ ማመን ማለት ሕይወታችንን እንዳለች ተቀብለን፣ በደስታ ወደ ፊት መጉዋዝ ማለት ነው።


“በኢየሱስ ማመን ማለት ሕይወታችንን እንዳለች ተቀብለን፣ ሳናጉረመርም፣ ክፉ የሆነ ኃጥያት በምያመጣብን ቁዘማ ሳንበገር በደስታ ወደ ፊት መጉዋዝ ማለት ነው” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 19/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በእለቱ ከዩሐንስ 1:1-16 በተነበበውና “በኢየሩሳለም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተዛታ የሚባል አንድ የምጭ ኩሬ ነበረ፣ በዚያም አምስት ባለቀስት መተላለፊያዎች ነበሩ። በዙ በሽተኞች፣ ዕውሮች፣ አንካሶች፣ ሽባዎች በመተላለፊያዎቹ ተኝተው ነበር። የጌታ መልአክ ወደ ኩሬው ወርዶ ውሃውን ያናውጠው ነበር። ከውሃው መናወጥ ቡኃላ በመጀመሪያ ወደ ኩሬው የሚገባ ካደረበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር”፣ በሚለው የወንጌል ቃል ላይ ዙሪያ መሰረቱን ባደረገው ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ኢየሱስ እዚያ ይገኝ የነበረ አንድ ሰውን “መዳን ትፈልጋለህን”? ብሎ ጠይቆት እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

ኢየሱስ ሁሌም እኛን “መዳን ትፈልጋለህን? ደስተኛ መሆን ትፈልጋለህን? ሕይወትህን ማሻሻል ትፈልጋለህን? በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ትፈልጋለህን? ብሎ የምያቀርብልን ጥያቄ እንዴት አስደሳች ጥያቄ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በዚያ ስፍራ የነበሩ ብዙ በሽተኞች፣ ዕውሮች፣ አንካሶች፣ ሽባዎች ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ “መዳን ትፈልጋላችሁን?” ብሎ ብጠይቃቸው ኖሮ ሁሉም በአንድነት “አዎን!!” ብለው ይመልሱ ነበር” ካሉ ቡኃላ ኢየሱስ ግን ይህን ጥያቄ አቅርቦ የነበረው አንድ ባዕድ ለነበረ ሰው እንደ ነበረ ገልጸው ይህም በሽተኛ ሰው “ጌታ ሆይ! ውሃው በተንቀሳቀሰ ጊዜ እኔን ወስዶ ወደ ኩሬው የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፣ እኔ ልሄድ ስል ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል” ብሎ መልሶለት ነበር ብለዋል። “ጌታ ሆይ ተመልከት! የእኔ ሕይወት መጥፎ እና ፍትሀዊ ሕይወት አይደለም የተሰጠኝ። እነዚህ በሽተኞች ሁሉ ለአለፉት 38 ዓመታት እኔን ቀድመው በመሄድ ወደ ውሃው በመግባት ከበሽታቸው ይፈወሱ ነበር እኔ ግን ይሄው 38 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እንዳለው አለው” በማለት  ማጉረምረም በሚመስል መልኩ ነበር ለኢየሱስ የመለሰው ብለዋል።

“ከዚህ ሰው ባሕሪ መረዳት የምንችለው ከማጉረምረሙ ባሻገር ‘ላለፉት 38 አመታት ውሃው በሚናወጥበት ወቅት ሌሎች ከእኔ ቀድመው ወደ ውሃም ይወርዳሉ’ በማለት ችግሩን በሌሎች ሰዎች ላይ ለማላከክ ፈልጎ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው ከራሱ ግድዬለሽነትና የማጉረምረም ባሕሪ የመነጨ መጥፎ ሊባል የሚችል ኃጥያት ነው ብለዋል።

“ይህ ሰው በጣም እንዲታመም ያደረገው ሽባነቱ ሳይሆን ግዴለሽነቱ ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ሰው መኖር ይፈልግ ነበር ታዲያ ለምድነው እርሱ ሕይወቱን ማስቀጠል ያልፈለገው? ለምንድነው እርሱ በሕይወቱ አንድ ነገር መፈጸም ያዳገተው? ምናልባትም የደስታን ጣዕም ረስቶት ሊሆን ይችላል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ሰው ደስታ የሚባለውን ነገር ፈጽሞ አያውቀውም፣ ፈጽሞ ረስቶታል፣ ይህም መጥፎ በሽታ ነው ‘አይ በቃ እንዲ ነው የለመድኩት፣ እንዲህ መኖር ይሻለኛል፣ ሕይወት ጣዕሙ ተፍቶብኛል’፣ የሚለውን የዛን ሰው ጎምዛዛ የሆነ ልብ ማየት ይቻላል” ብለዋል።

ኢየሱስ ይህንን ሰው አላወገዘውም ነበር። ነገር ግን “ተነስ! አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ባለው ጊዜ ይህ ሽባ የነበረ ሰው ወዲያውኑ ከበሽታው ተፈውሶ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  “ያ ሽባ ሰው የተፈወሰበት በሰንበት ቀን ነበር፣ ፈሪሳዊያን እና የሕግ አዋቂዎችም ይህንን ከበሽታው የተፈወሰውን ሰው በሰንበት ቀን አልጋህን መሸከም አልተፈቀደልህም፣ ማነው እርሱ በዚህ በሰንበት ቀን የፈወሰህ?” ብለው ጠይቀውት እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “ይህንን ጥያቄ በጠየቁት ጊዜ ይህ ሰው ‘ሕግን ይቃረናል፣ ይህ ሰው በፍጹም የእግዚኣብሔር ሰው አይደለም’” ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ሰው ከበሽታው የፈወሰውን ኢየሱስን ‘አመስግንሃለው’ እንኳን አላለውም ነበር፣ ያዳነው ማን እንደ ነበረ እንኳን ስሙን አልጠየቀም ነበር” ብለው “ከዚያ ከያዘው ግዴለሽነቱ ጋር ነበር ተነስቶ የሄደው፣ እስካሁንም ይህ ሰው በሕይወት የቆየው የሚተነፍሰው ኦክስጂን በነጻ የሚገኝ በመሆኑ ነው፣ ሌሎች ከእኔ የተሻለ ‘ደስተኞች ናቸው’ በማለት ሐዘን ውስጥ ገብቶ ነበር፣ ይህም ደስታውን እንዲረሳ አድርጎት ነበር” ብለዋል።

“ግድየለሽነት ሽባ ሊያደርገን የሚችል በሽታ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በትክክል እንዳንራመድ ያግደናል” ካሉ ቡኃላ “ዛሬም ቢሆን ጌታ እያንዳንዳችንን ይመለከታል፣ ሁላችንም ኃጢያት ሠርተናል፣ ሁላችንም ኃጥያተኞች ነን፣ ይህንን ኃጥያታችን ተመልክቶ ‘ተነስ/ተነሽ!’ ይለናል” ብለዋል።

“ዛሬ ጌታ እያንዳንዳችንን እንዲህ ይለናል ‘ ተነስ/ሽ! ሕይወትህ መልካም ወይም መጥፎ ይሁን አይሁን እንዳለች ውሰዳትና ወደ ፊት ሂድ፣ አትፍራ፣ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ!” ይለናል ያሉት ቅዱስነታቸው “ምንም እንኳን ሕይወትህ ምሳሌ ለመሆን የሚችል ባይሆንም ወደ ፊት ሂድ! ከፉ የሚባል ሕይወት ቢኖርህም ወደ ፊት ሂድ፣ ምክንያቱም የአንተ ሕይወት የአንተ ደስታ ናትና” ብለዋል።

“መዳን ትፈልጋለህን?” በማለት ጌታ ዛሬ በቀዳሚነት ጥያቄ ያቀርብልናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “አዎን ጌታ ሆይ! ብለን ስንመልስ “ተነስ/ሽ” ይለናል ብለዋል። በመስዋዕተ ቅዳሴያአችን መግቢያ ላይ “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፣ እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ ወደ ውሆች ኑ፣ ኑ ያለ ገንዘብ ያለ ዋጋ፣ በደስታም ጥማችሁን አርኩ (ኢሳያስ 55:1)” ይል እንደ ነበር ያስታወሱት ቅዱስነታቸው እኛ ለጌታ “ጌታ ሆይ መዳን እፈልጋለሁኝ፣ አዎን ጌታ ሆይ እንድነሳ አግዘኝ” በምንልበት ወቅት ሁሉ በደኅንነት የሚገኘውን ደስታ ምን እንደ ሆነ እንገነዘባለን ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.