2017-03-28 10:48:00

“የዓብይ ጾም ወቅት ከሚያጎድፈን እና ያልተገባን ከሚያደርጉን ነገሮች የምንርቅበት ወቅት ነው”


“የዓብይ ጾም ወቅት ከሚያጎድፈን እና ያልተገባን ከሚያደርጉን ነገሮች የምንርቅበት ወቅት ነው”

የምሕራባዊያን አብያተ ክርስቲያንት በየካቲት 22/2009 ዓ.ም. ሐይማኖታዊ በሆነ መንገድ የአምድ በግንባር ላይ የመቀባት ስነ-ስርዓት በማከናወን የ40 ቀን ዓብይ ጾምን በይፋ መጀመራቸው ይታወቃል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ በሚገኘው በቅድስት ሳቢና ቤተ ክርስቲያን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ  ዓብይ ጾምን በይፋ አስጀምረዋል። በእለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት “የዓብይ ጾም ወቅት ከሚያጎድፈን እና ያልተገባን እንድንሆን በማድረግ የእግዚኣብሔር ልጆች የመሆን መብታችንን የሚንፍጉን ነገሮች ሁሉ በምሕረት ድል እንድናደርግ የሚረዳን ወቅት ነው” የዓብይ ጾም ወቅት ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ያሰሙትን ስብከት በእለቱ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመናዋል።

“አሁንም ቢሆን በጾም፣ በለቅሶና በሐዘን በፍጹም ልባችሁ ተመለሱ ይላል እግዚኣብሔር፣ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ” (ት.ኢዩኤል 2:12)። ነቢዩ ኢዩኤል ይህንን ጥሪ ለሕዝቡ በእግዚኣብሔር ሥም ያቀርባል።  “ሕዝቡን ሰብስቡ ጉባሄውን ቀድሱ፣ ሽማግሌዎችን በአንድነት አቅርቡ፣ ሕጻናትን ሰብስቡ፣ ጡት የሚያጠቡትን አታስቀሩ፣ ሙሽራው እልፍኙን ይተው፣ ሙሽሪትም የጫጉላ ቤቷን ትተው” (ት. ኢዩኤል 2:16) በማለት ማንም ሰው ከእዚህ ጥሪ ውጭ ሊሆን እንደ ማይገባ ያሳስበናል። ሁሉም ምዕመናን ጌታቸውን እንዲያመልኩ “ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚኣብሔር ተመለሱ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ ቁጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገስ ነውና” (ት.ኢዩኤል 2:13) በማለት ጥሪ ያደርጋል።

እኛም ይህንን ጥሪ ተቀብለን በምሕረት ወደ ተሞልተን የአምላክ ልብ ልንመለስ ያስፈልጋል። አሁን ባለንበት የጸጋ ወቅት ወደ እግዚኣብሔር ምሕረት ዐይናችንን ልንመልስ ያስፈልጋል። የዓብይ ጾም ወቅት ከሚያጎድፈን እና ያልተገባን እንድንሆን በማድረግ የእግዚኣብሔር ልጆች የመሆን መብታችንን የሚንፍጉን ነገሮች ሁሉ በምሕረት ድል እንድናደርግ የሚረዳን ወቅት ነው። ዓብይ ጾም ከባርነት ወደ ነፃነት፣ ከመከራ ወደ ደስታ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ጉዞ የሚደረግበት ወቅት ነው። በግንባራችን ላይ የተቀባነው አመድ ሥር መሰረታችንን በማስታወስ ከፈር መሠራታችንን እና ወደ አፈር እንደ ምንመለስ ያስታውሰናል። እርግጥ ነው በእግዚኣብሔር የፍቅር እጆች ውስጥ አፈር ነን፣ እስትንፋሱንም በእያንዳንዳችን ላይ እፍ በማለት የሕይወት መንፈስ ሰጠን፣ አሁንም እየሰጠን ይገኛል። ሸፋፍኖ ከያዘን የራስ ወዳድነት መንፈስ፣ በራስ ወዳድነትና በምን አገባኝ ስሜት እንድንጓዝ ሸፋፍኖ ከያዘን መንፈስ፣ የርኅራኄ መንፈሳችንን ሸፋፍኖ ከያዘን መንፈስ፣ አድማሳችንን ከሚያጠበው እና የልብ ምታችንን ከሚያደክመው ከእንዚህ እና ከመንኛውም ዓይነት ለየት ካለ መንፈስ  የሚታደገንን የሕይወት እስትፋሱን በቀጣይነት ሊሰጠን ዝግጁ ነው። የእግዚኣብሔር የሕይወት እስትንፋስ እምነታችን እንዲቀበር ከሚያደርጉት ለጋሾች እንዳንሆንና እምነታችንን ከሚያደመዝዙ ማነኛውም ዓይነት መንፈሶች እኛን ይታደገናል ያድነናልም። የዓብይ ጾምን ወቅት መለማመድ ወይም መኖር ማለት አምልካ ባለ ማቋረጥ የሚለግሰን እስትንፋሱን በመቀበል የጨቀዬ ታሪካችንን ፍሬአማ በሆነ መልኩ እንዲነጻ ማድረግ ማለት ነው።

የእግዚኣብሔር እስትንፋስ ሁል ጊዜ እኛ ለመረዳት ከሚያዳግተን እና ምንም እንኳን እኛን እንደ ሚጎዱን እያወቅን ነገር ግን ጤናማ ነገር እንደ ሆነ አርገን የምንተገብራቸውን ተግባሮች ውስጥ ታፍነን እንድንኖር ከሚያደርጉን መነፈሶች ሁሉ ነፃ ያወጣናል። የሚጎዱን ነገር ግን እኛ ከእነዚህ ነገሮች ጋር በመለማመዳችን የተነሳ እንደ ጤናማ አድርገን የምንቆጥራቸውን ተግባሮች፣ በጭላንጭል ውስጥ ያሉትን መንፈሶች፣ የጭንቀት መንፈሶችን ሳይቀር እንድናሸንፍ ይረዳናል ዓብይ ጾም።

የዓብይ ጾም ወቅት እምብዬው የምንልበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት መንፈሳዊ ሕይወታችንን አፍኖ በመያዝ ሕይወታችንን በምን አገባኝ መንፈስ በመመረዝ የሌሎች ሰዎች ሕይወት እኔን በፍጹም አይመለከተኝም እንድንል የሚያባብሉን መንፈሶች በመቃወም እንዚህን ክፉ መንፈሶች እንብዬው አታስፈልገኝም በማለት ይምንቃወምበት ወቅት ነው የዓብይ ጾም ወቅት። የዓብይ ጾም ወቅት ሕይወታችንን የሚመርጹ ነገሮችን ሁሉ እብዬው በማለት ከሕይወታችን እነዚህን መርዛማ ነገሮችን የምናስወግድበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት ትርጉም የለሽ የሆኑ ባዶ ቃላትን፣ ሰዎችን መፈረጅ፣ በሰዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ ሂስ እንድናደርግ የሚገፋፉንን ስሜቶች እንብዬው አታስፈልግኝም የምንልበት ወቅት ነው የዓብይ ጾም ወቅት። የዓብይ ጾም ወቅት የክርስቶስ መከራ ተካፋይ የሆኑ ወንድም እና እህቶችን በማግለል እግዚብሔርን ብቻ እንድንፈልግ የሚያደርገንን አፍኖ የያዘንን መንፈስ እንብዬው አታስፈልገኝም የምንልበት ወቅት ነው። በአጠቃላይ የዓብይ ጾም ወቅት  እምነታችንን ሊቀንሱ የሚችሉትን መንፈሶች፣ ክፉ ባሕሎችን አግላይ የሆኑ ባሕሪያትን ሁሉ እንብዬው አታስፈልጉኝም የምንልበት ወቅት ነው የዓብይ ጾም ወቅት።

የዓብይ ጾም ወቅት የማስታወሻ ጊዜ ነው። በእዚህ የዓብይ ጾም ወቅት የምናሰላስልበትና ራሳችንን እግዚኣብሔር በሩን ቢዘጋብን ምን ልንሆን እንችላለን ብለን ራሳችንን የምንጠይቅበት ወቅት ነው። ይቅርታን መለገስ የማይሰለቸውና ሁልጊዜ አዲስ ሰዎች እንድንሆን እድል ከሚሰጠን ከእግዚኣብሔር ምሕረት ወጭ ብሆን ምን ልሆን እችላለሁ ብለን ራሳችንን የምንጠይቅበት ወቅት ነው የዓብይ ጾም ወቅት። የዓብይ ጾም ወቅት በጣም ብዙ ሰዎች ሕይወታችንን ደግፈው፣ እጃቸውን ዘርግተው እንዲሁም ተጨባጭ በሆነ መልኩ እኛን በመርዳት ተስፋ ሳንቆርት ወደ ፊት እንድንጓዝ እና አዲስ ሕይወት እንድንኖር ያስቻሉንን ሰዎች ሁሉየማስታወሻ ጊዜ ነው የጾም ወቅት።

የዓብይ ጾም ወቅት እንደ ገና በአዲስ መልኩ መተንፈስ የምንጀምርበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት ልባችንን በመክፈት ውስጣችንን ከክፉ ነገር አጽድቶ መልካም ሰዎች እንድንሆን ለሚያደርግን መንፈስ ልባችንን የምንከፍትበት ወቅት ነው።

የዓብይ ጾም ወቅት በክፉ ነገሮች ፊት ቆመን ልብሳችንን የምንቀድበት ወቅት ሳይሆን መልካም ነገሮችን እንድናከናውን የሚረዳንን ልባችን የምንከፍትበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት እንድንገለልና ሽባ እንድንሆን የሚያደርጉንን ነገሮች ሁሉ አውልቀን የምንጥልበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት ርኅራኄን የምናሳይበት ወቅት ነው። የዓብይ ጾም ወቅት በመጽሐፈ መዝሙር በምዕራፍ 51: 12, 15 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ከአዳኝነትህ የሚመነጨን ደስታ መልሰህ ስጠኝ እንድታዘዝህም ፈቃደኛ አድርገኝ፣ በእኔም አመሰግንሃለሁ” የምንልበት ወቅት ሊሆን ይገባል።

ክቡራን እና ክቡራት ታዳሚዎቻችን ቀደም ሲል ስትከታተሉት የነበራችሁት የ40 ቀን ዓብይ ጾም በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከተማ በሚገኘው በቅድስት ሳቢና ቤተ ክርስቲያን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ነበር። አብራችሁን ሆናችሁ ዝግጅቶቻችንን ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን።

                                        

 








All the contents on this site are copyrighted ©.