2017-03-27 17:00:00

የዓቢይ ጾም ሦስተኛ ስብከት፥ ሞት ለአማኝ ወደ አዲስ ሕይወት መወለድ ነው


የካፑቺን ንኡሳን አኃው ማኅበር አባል ሰባኬ ቤተ ጳጳስ አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና መላ የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጳጳሳዊ አቢያተ ምክር እንዲሁም ቅዱሳን ማኅበራት ሊቀ መናብርትንና ኅየንተዎችን ያሳተፈው በሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው እመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት የዓቢይ ጾም ሦስተኛ ስብከት ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ ገለጡ።

አባ ካንታላመሳ ያቀረቡት የዓቢይ ጾም ሦስተኛው ስብከት፥ መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ሞት ውስጥ ያለውን የፋሲካ ምስጢር የሚያበራ ነው የሚል ሃሳብ ያማከለ ሆኖ ከዚህ ጋር በማያያዝም የነፍስ ወከፍ ሰው ሕይወትና ሞት ምን ትርጉም እንዳለው የሚያስረዳ አስተንትኖ ማቅረባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አያይዘው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣሴ  ውስጥ ያለው ምስጢረ ፋሲካ ለዚያ የሕይወትና ሞት፡ የሕይወት ፍጻሜ ምንድር ነው ለሚለው ጥያቄ ብቸኛ መልስ ነው፡ ከዚህ ዓይነት ጥልቅ ግንዛቤ በመነሳትም አባ ካንታላመሳ፥ ኢየሱስ ገዛ እራሱን ለመስዋዕት ሲሰጥና በስቃዩም ሁሉ ኃይል እንዲኖረው የመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነትን ተቀበለ፡ ኢየሱስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ ተቀበለ በሚሞትበት ወቅትም ኢየሱስ በተራው መንፈስ ቅዱስን አደለ። ስለዚህ ይኽ ምስጢር ለእያንዳንዳችን ያለው ትርጉም በመለየት በማስተዋል ልናከብረው ይገባናል ብለው ኢየሱስ ሲሞት የፈጸመው አዲስ ክውንት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ በማንሳት፥

ኢየሱስ በሚሞትበት ወቅት የፈጸመው ወሳኝ ተግባር፥ ‘… ስለ ሁሉ ሞተ’ (2ቆሮ. 5,15)፤ ይኽ የዚህ ሰው ሞት (የኢየሱስ) በሰው ልጅ ሞት ላይ ያመጣው ወሳኝ ለውጥ ምንድን ነው? ምንድን ነው የከሰተው? አልአዛር በኋላ እንደ ማንኛውም ሰው የራሱን ሞት የሚሞተው ኢየሱስ ክሞት ሲያስነሳው ሲቀበር በገባበት በር ነበር የወጣው። ኢየሱስ ዳግም እንዳይሞት ከሞት ሢነሳ ሲቀበር የገባበት በር ከፍቶ ሳይሆን የመቃብሩን መክበቢያ ግንብ በርግዶ በማፍረስ ነው የተነሣው። ኢየሱስ ከሞት ወደ ትንሣሴ ይሸጋገራል። ቅዱስ አጐስጢኖስ ‘በስቃይ ኢየሱስ ሰው ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገረ። በዚህ መንገድ፡ እኛ በእርሱ ትንሣኤ ለምናምን ከሞት ወደ ሕይወት የሚያሸጋግረውን ተስፋ አበራልን’ ሲል እንደተናገረው ነው።”

ይኸንን ያሉት አባ ካንታላመሳ ሞት ምንም ማለት መሆኑ ሲያስረዱ፥

“በዘመናት ተፈላሳፍያን ገጣሚዎች ደራሲያን የተለያዩ ሃይማኖቶች ፥ ሞት የሕይወት መቋረጥ ወይንም ስለ እዳ የሚከፈል ዋጋ፡ አሊያም ሃሳባዊ ወይንም የሌለ ችግር፡ ተመልሰን የምንሄድበት ለመፈጠራችን ምክንያት እንደሆነ ይኽ ደግሞ ባዶነት ተብሎ የሚገልጡትና በሌላው ረገድ ደግሞ ተኪዎችን በመፍጠር (በመውለድ) የሚቀረፍ ችግር ነው። ሌሎች ደግሞ ሞት ለዳግመ ሥጋዌ በር (ዳግም ሥጋ ለብሶ ወደ መፈጠር የሚያሸጋግር) ብለው ይገልጡታል። በክርስቶስ ግን ወደ ማያልፈው (አዲስ ሕይወት) ሕይወት መሸጋገሪያ ሆነ። የዚህ ሞት ጥልቅ ትርጉም በፍቅር ላይ የጸና መሆኑ ያስገነዝበናል። ይኽ የፍቅር ምሥጢር በማትጠብቀው ሁነት የሚከወን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የሞት ምሥጢር በዚያ ኢየሱስ ሞቶ ሞትን አሸነፈ በሚለው ላይ ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ሊያሰርጽ በመምጣቱ ላይ ጭምር ነው። የሰው ልጅ ገዛ እራሱን ከእግዚአብሔር አራቀ ለእግዚአብሔር ጀርባውን ስጠ። ኢየሱስ በትስብእቱ (ሥጋን ለብሶ-በመወለድ) በዚያ ተሸማቆ በነበረው ጥልቅ ሰብአዊ ውስጥ ፍቅር እንዲሰርጽ ያደርጋል። ስለዚህ ሁሉም የሰው ልጅ ፍጥረት ቢያስተውለውም ባያስተውለውም በውስጡ ሰርጾ ካለው ከሚጠባበቀው ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር ነው የሚገናኘው።”

ዛሬም ቢሆን ወደ መቃብር መሄድ መሞት አልቀረም መሞት ያለ ነው። ሆኖም የሰው ልጅ በክርስቶስ ትንሣሴ ላይ ተንጠላጥሎ ከሞት ለመውጣት ለመነሣስት እድል እንደተሰጠው አባ ካንታላመሳ ገልጠው አንድ አማኝ ሊያደርገው የሚገባው ጉዳይ በኢየሱስ ትንሣኤ ማመን ነው። ክርስቲያን እንደ ሌሎች ነገር ግን ከሌሎች የተለየ ነው ሲባል። ሟች መሆኑ የሚያወቅ ነገር ግን በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ተንጠላጥሎ ከሞት እንደሚነሳ በሞት ፊት ፍርሃት ሃዘን ያለው ነገር ግን በክርስቶስ ትንሣሴ ላይ ተንጠላጥሎ ከሞት ወደ አዲስ ሕይወት እንደሚሸጋገር የሚያምን መሆኑ ማለት ነው፡ ስለዚህ ለአንድ አማኝ መሞት ማለት ዳግም መወለድ ማለት፡ ነው እንደ ምስጢረ ጥምቀት ነው። ከክርስቶስ ጋር መሞት ከክርስቶስ ጋርም መነሣት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታውቋል።

የክርስትናው እምነት መንገዱን የሚያቀናው የሚስፋፋው ሌላውን የሚማርከው በሞት ዘንድ ያለው ፍርሃት፡ የሞት አስፈሪነት በመጠቀም ሳይሆን ፍርሃትን በማስወገድ ነው። የእራሳችን ሞት የኢየሱስ ስቃይና ሞት (አስተውለን) በመገንዘብ ስናስብና ስናተነትን ውጤት ይኖረዋል። በተለይ በዚህ በአሁኑ የዓቢይ ጾም ወቅት ይኸንን ለማሰብ ይመቻል ያሉት አባ ካንታላመሳ ይኽ አይነቱ አስተንትኖ የሚያነቃቃ እንጂ ጭንቀት የሚፈጥር አይደለም። ምክንያቱም በመጨረሻም ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው፥ “ያፈቅረኛል አፍቅሮኛል ገዛ እራሱን ስለ እኔ አሳልፎ ሰጥቷል” ብለን በግብታዊነት ለማወጅ እንድንችል ያደርገናልና በማለት ያቀረቡትን ሦስተኛው የዓቢይ ጾም ስብከት ማጠቃለላቸው ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.