2017-03-24 16:57:00

ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ፥ ሚላኖ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ለማስተናገድ ትጓጓለች


ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚላኖ ከተማ የአንድ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን። የቅዱስነታቸውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለምትታደለው ሚላኖ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ “ምንም’ኳ ተስማሚ ልማትና እርስ በእርሱ የሚሟላ ልማት ነው ብሎ ለመናገር ባደፈርም ሚላኖ በተለያየ ዘርፍ እርሱም የሥራ ዕድል በመፍጠሩ ረገድ፤ በባህል ጉዳይ፤ በግብረ ሠናይና ማኅበራዊ ወዳጅነት ባካተተ የልማት ዘርፍ እድገት እያረጋገጠች ትገኛለች” ብለው ከዚህ ጋር በማያያዝ ይኽች ኅብረዊት ከተማ ዕለታዊ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ኅብረአዊነት መለያዋን ግምት የሰጠና ኅብረአዊነትን የሚመሰክር ነው። ይኽም ሆን ተብሎ ሳይሆን በከተማይቱ ያለው ተጨባጩ ሁነት እንዲኖር የሚያደርገው ዕድል መሆኑ በማለት ገልጠዋል።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን በሚላኖ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያንን እሳቸው እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. “Evangelii Gaudium-ወንጌላዊ ሐሴት” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ፈለግ ያደረገ እንደሚሆን ከዚህ የሐዋርያዊ ጉብኝት መርሐ ግብር ለመረዳ ይቻላል። በከተማይቱ ጥጋዊ ክልል የሚኖረው በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ የሚተዳደረውን በመድኽነት የሚገኘውን ነዋሪ ሕዝብ ዘንድ በመሄድ በድኽነት ለሚሰቃዩት ኢየሱስ ምንኛ ቅርብ መሆኑ ይምሰክራሉ። ጉብኝታቸውን ከተናቁት በድኽነት ሥር የሚገኙትን እስረኞችና ህሙማን ጋር በመገናኘት የሚጀምሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት በመሆኑ የኢየሱስ አብነት የሚኖር ጉብኝት ነው፡ ስለዚህ የሕይወት ባህል ላይ ያተኰረ ከዚያ ካልአ ኢየሱስ ከሆኑትን ድኾች ጋር መገናኘትና የድኾችን አካል መንካት የሚል ኢየሱሳዊ መንፈስ ያማከለ ጉብኝት ነው ብሏል።

በወንጌላዊ ሐሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን ተመልክቶ እንደሚገኝም የኤኮኖሚው ዓለም፡ ባለ ሃብቶች በጠቅላላ ባለ ግብኣታውያን ሁሉ ብቻ የሚበለጽጉበት የሚያድጉበት ሳይሆን ሁሉም ዜጋ ለማሳደግ የሚያግዝ እቅድ አስፈላጊ ነው በማለት ያስቀመጡት ሃሳብ አስታውሰው ስለዚህ ቅዱስ አባታችን በዚህ በሚያካሂዱት ጉብኝት ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመገናኘት ይሻሉ ከሁሉም ጋር ለመገናኘት ባይችሉም በሐዋያዊ ጉብኝት ወቀት የሚለግስቱ ቃለ ምዕዳን ለሁሉ መደቦች የሚመለከት መልእክት እንደሚኖር እርግጠኛ ነኝ ብለው ስለዚህ ጉብኝቱ ሁሉንም የሚያጠቃልል መሆኑ ገልጠዋል።

በሁሉም ማኅበራዊ መስክ ቃለ ወንጌል ለማገናኘት የሚያስችል የሕይወት ስልት መኖር ያለው አስፈላጊነት ቅዱስ አባታችን በቃልና በሕይወት የሚሰጡት ምስክርነት ነው። ስለዚህ ይኽች የኢጣሊ የኤኮኖሚና የቁጠባ ማእከል ተብላ የሚነገርላት ከተማ የጊዜ እጥረት የሚታይባት ተብሎም ይነገርላታል ቢሆንም የጊዜ ማጠር መፈውስ የሚቻለው ሰብአዊነት ያማከለ ሕይወት በመኖር ነው። ሰብአዊነት ያማከለ ሲባል ሃብት ማካበት ከሚለው አስተሳሰብ ተላቆ ወደ ተካፍሎ መኖር መሸጋገር ይጠይቃል ነው። ስለዚህ ይኽ ለከማይቱ የአስፍሆተ ወንጌል ጎዳና ነው በማለት ያካሂዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.