2017-03-24 15:19:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "የደነደነ ልብ ካለን፣ እምነተ ቢስ ካቶሊኮች ነን ማለት ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


“የእግዚኣብሔርን ድምጽ በየጊዜው ማዳመጥ የደነደነ ልብ እንዳይኖረን ያደርጋል” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 14/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

የዚህ ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!!

 

ከእግዚኣብሔር በምንርቅባቸው ወቅቶች ሁሉ እና የእርሱን ቃል ላለምስማት ጆሮዎቻችንን በምንደፍንበት ወቅቶች ሁሉ ታማኝ ያልሆንን ወይም ደግሞ “አምላክ ዬለሽ ካቶሊኮች” እንሆናለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት በሚያቆምበት ጊዜ ሁል ቀዝቃዛ ይሆናል በመጨረሻም ራሱን ከአምላክ ያርቃል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር መሰረት በእለቱ በተነበበውና ከትንቢተ ኤርሚያስ 7፡23-28 በተወሰደው የእግዚኣብሔርን ድምጽ ማዳመጥ ያስፈልጋል በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ እንደ ገለጹት “የእግዚኣብሔርን ድምጽ ማዳመጥ በምናቆምባቸው ወቅቶች ሁሉ ከእግዚኣብሔር መራቅ እንጀምራለን፣ ጀርባችንንም ለእርሱ ላይ ማዞር እንጀምራለን፣ የእግዚኣብሔርን ድምጽ ማዳመጥ ትተን ሌሎች ድምጾችን ማዳመጥ እንጀምራለን ብለዋል።

ቀስ በቀስም ከእነዚህ የዓለማችን የጣኦት ድምጾች ጋር እየተለማመድን በምንመጣባቸው ወቅቶች ሁሉ  በተቃራኒው ደግሞ ለእግዚኣብሔር ድምጽ ጆሮዎቻችንን እንደፍናለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ዛሬ እዚህ የምንገኝ ሁላችን ለአንድ አፍታ ቆም ብለን ልባችንን ብንመረምር፣ ምን ያህል ጊዜ ጆሮዎቻችንን ለእግዚኣብሔር ድምጽ መድፈናችንን መረዳት እንችላለን” ብለዋል።

አንድ እዝብ፣ ወይም አንድ ማኅበረሰብ፣ ወይም ደግሞ አንድ የክርስቲያን ማሕበር፣ አንድ ቁምስና፣ አንድ ሀገረ ስብከት ጆሮዎቹን የእግዚኣብሔር ድምጽ ላለመስማት ድፍን በማድረግ በተቃራኒው ደግሞ ጆሮዎቹን ለጣኦቶች፣ ለዓለምና በዓለም ውስጥ ለሚገኙ ድምጾች ሁሉ ወይም ደግሞ ከማኅበረሰቡ ለሚወጡ ድምጾች ሁሉ ጆሮዎቹን  በሚከፍትበት ወቅቶች ሁሉ ከእግዚኣብሔር ይርቃል ብለዋል።

በእዚህም ሁኔታ ከእግዚኣብሔር በምንርቅበት ወቅቶች ሁሉ ልባችን መደንደን ይጀምራል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔርን ድምጽ ማዳመጥ ችላ እያልን በምንሄድባቸው ወቅቶች ሁሉ ልባችንም በዛው ልክ እየደነደነ ይሄዳል፣ ራሱን  በራሱ እየዘጋ ይሄዳል” ብለዋል።

“በእዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ መግባት ጥሩ ነገር አይደለም” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በምናደርገብት ወቅት ሁሉ “ልባችን በየቀኑ ይበልጡኑ  ከእግዚኣብሔር መራቅ ይጀምራል” ካሉ ቡኃላ “የእግዚኣብሔርን ድምጽ አለመስማት እና ልባችንን ማደንደን የሚሉት ሁለት ቃላት ራሳችንን በራሳችን ዝግ በማድረግ ታማኝነት እንድናጣ ያደርገናል” ብለዋል። ዛሬ የተነበበልን የመጀመሪያው ምንባብ (ከትንቢተ ኤርሚያስ 7፡23-28) ጌታ ሆይ በዚህን ጊዜ “ታማኝነት ጠፍቱዋል” ይለናል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ታማኝነት ካጣን ታማኝ ያልሆንን፣ አረማዊያን፣ ከእዚህም ዘለል ሲል “እግዚኣብሔር የለሽ ካቶሊኮች እንሆናለን” ካሉ ቡኃላ ምክንያቱም በማጣቀሻነት ሊወሰድ የሚገባውን የሕያው የእግዚኣብሔር ፍቅር በውስጣችን ባለመኖሩ የተነሳ ነው ለእዚህም ነው እንግዲህ የእግዚኣብሔርን ድምጽ አለማዳመጥ እና ጀርባችንን ለእርሱ መስጠት ልባችንን እንዲደነድን ያደርገዋል፣ ይህም ታማኝነትን ወደ ሚያሳጣ ጎዳና ይመራናል የምላችሁም በዚሁ ምክንያት ነው” ብለዋል።

ታዲያ ይህንን “ጉድለታችንን እንዴት ነው መሙላት የምንችለው”? ብለው ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እግዚኣብሔር የት እንዳለ በማናውቅበት እና እግዚኣብሔር በሌለበት ሥፍራ ግራ በተጋባ መልኩ እርሱን ለማግኘት በምንሞክረበት ወቅት ሁሉ እግዚአብሔርን እና ሰይጣንን በማቀላቀል ግራ እንጋባለን” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ሐሳባቸውን ለማጠናከር በማሰብ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል 11: 14-23 ላይ በተወሰደው ምንባብ ላይ በመመርኮዝ “ኢየሱስ ተአምራትን በመስራት የሕዝቡን ደኅንነት ባረጋገጠበት ወቅት ሕዝቡ በጣም ደስተኛ ነበር” አንድ አንዶቹ ግን አጋንትን የሚያሰውጣው የአጋንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል አማክይነት ነው” ይሉ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

“የእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እግዚኣብሔርን እንደ መሳደብ ይቆጠራል፣ ይህም ስድብ የእግዚኣብሔርን ድምጽ ባለመስማት ተጉዘን የመጨረሻ ደረጃ ላይ በምንደርስበት ወቅትና ልባችንም በጣም በሚደነድንበት ወቅት የምንለው ስድብ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ግራ እንድንጋባ እና ታማኝነታችንን እንድንረሳ በማድረግ ይሄው በመጨረሻው ደግሞ እግዚኣብሔርን የመሳደብ ደረጃ ላይ ያደርሰናል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “ከኢየሱስ ጋር የነበራችሁን የመጀመሪያ ግንኙነት የዘነጋችሁ እና እርሱ ያደረገላቸውን ድንቅ ነገር ለመረዳት የታከታችሁ ሰዎች ሁሉ ወየውላችሁ!” ያሉት ቅዱስነታቸው “ዛሬ እየአንዳንዳችን ‘የእግዚኣብሔርን ድምጽ ለመስማት እስቲ አንደ ቆም እንበል፣ መጽሐፍ ቅዱሳችንን በእጃችን በመያዝ ለእኔ እየተናገረኝ ነውን?’ ልቤ ደንድኑዋልን? ከእግዚኣብሔር ርቄ ነበርን? ለጌታ የነበረኝን ታማኝነት አጥቻለሁኝን፣ የምኖረውስ ጣዎት በስጦታነት ለሚያቀርብልኝ ዓለማዊ ነገሮች ራሴን አስገዝቼ ነውን? ከጌታ ጋር በመጀመሪያ በተገናኘውበት ወቅት የነበረኝን ደስታ አጥቻለሁኝን? በማለት ራሳችንን በመጠየቅ በዛሬው ቀን የእግዚኣብሔርን ድምጽ ለመስማት የምንጠባበቅበት እለት ሊሆን ይገባል ብለዋል። ልክ ዛሬ ከመዝሙረ ዳዊት በተወሰደው ምንባብ “ዛሬ የእግዚኣብሔርን ድምጽ ስሙ፣ ልባችሁን አታደንድኑ” ብለን እንደ ጸለይነው ይህንን የማዳመጥ ፀጋ ከእግዚኣብሔር እንጠይቅ ምክንያቱም ልባችንን እንዳይደነድን እርሱ ሊረዳን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.