2017-03-20 16:56:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "ቅዱስ ዮሴፍ ትላልቅ ነገሮችን ማለም እና ሕልማችንን እውን ማድረግ ያስተምረናል" ማለታቸው ተገለጸ።


በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 11/2009 ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማሪያም እጮኛ የነበረው ቅዱስ ዮሴፍ አመታዊ ክብረ በዓል ተከብሩዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ቅዱስ ዮሴፍ ወጣቶች “ሕልም የማለም ችሎታ እና ማንኛውንም ዓይነት አስቸጋሪ ነገሮችን የመጋፈጥ ችሎታ እንዲኖራቸው በአጠቃላይ ሕልማቸውን እውን ማድረግ ስጋቶችን ሁሉ በትዕግስት ማለፍ እንደ ሚገባቸው ያስተምራል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በቅዱስ ዮሴፍ ሕይወትና ተግባር ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስ ዮሴፍ የደካሞች እና እግዚኣብሔር በሕልሙ ተገልጾ የነገረውን ቃል በደራ የጠበቀ ሰው እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስ ዮሴፍ የእግዚኣብሔር መልአክ በሕልሙ ተገልጾ ማሪያም ያረገዘችው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ሆነ በማስረዳት ዮሴፍ ማሪያምን እንዲንከባከባት የሰጠውን የአደራ ቃል በተግባር ላይ አውሎታል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ ዮሴፍ ዝምተኛ እና ታዛዥ ሰው እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸዋል። ቅዱስ ዮሴፍ ይህንን በጣም ከባድ የሆነ ኃላፊነት ምንም ሳያንገራግር ተቀብሎ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም ሁኔታ እግዚኣብሔር የሰጠውን ኃላፊነት በዝምታ ተቀብሎ በታላቅ ብርታት እግዚኣብሔር ወደ ሚፈልገው ግብ ማድረሱንም ጭምረው ገልጸዋል።

ቅዱስ ዮሴፍ ብዙ ነገሮችን ሊነግረን የሚችል ሰው ነበር፣ ነገር ግን ምንም ለመናገር ስላልፈለገ በዝምታ መቆየትን መርጦ እንደ ነበረ በመግልጸ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የኢየሱስ በበረት መወለድ፣ ሕጻኑን ኢየሱስንና እናቱን ማሪያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሸሹን፣ በሕይወቱ የገጠሙትን ውጣ ውረዶችን ሁሉ ሳይቀር ሊነግረን ይችል ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ምንም ሳይናገር እነዚህን ነገሮች በልቡ በመያዝ በታላቅ ፍቅር የተሰጠውን ተልዕኮ ገግብ ማድረስ ችሎ ነበር ብለዋል።

ቅዱስ ዮሴፍ በሕልሙ ያየውን ነገር ሁሉ እስከ መጨረሻ ጠብቆ ለመቆየት ችሎ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው ሁል ጊዜ ትልቅ እና መልካም የሆኑ ነገሮችን የምናልም ከሆነ፣ ወደ እግዚኣብሔር ሕልም እንጠጋለን እግዚኣብሔር ለእኛ ወደ ምያልምልን ሥፍራም እንደርሳልን ብለዋል። ቅዱስ ዮሴፍ ሕልምን እውን ማድረግ እንዳስተማረን ሁሉ በዛሬ ዘመን የሚገኙ ወጣቶችም ምንም እንኳን በሕይወታቸው ብዙ ውጣ ውረድ ቢገጥማቸውም ሕልማቸውን እውን እስኪያደርጉ ድረስ ጠንክረው መሥራት እንደ ሚጠበቅባቸው ቅዱስ ዮሴፍ ያስተምራል ያሉት ቁዱስነታቸው ምዕመናን ሁሉ ለተሰጣቸው ኃላፊነት ታማኝ እንዲሆኑና የመልካምነትን ባሕሪ መላበስ አስፈላጊ እንደ ሆነም ያስተምረናል ካሉ ቡኃላ ልክ ቅዱስ ዮሴፍ መልካም፣ በጥቂት ቃላት ብቻ የየተገደበ ዝምተኛ ሰው እንደ ነበረ በዝምታ ሌሎችን በተለይም ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሁሉ ይንከባከብ እንደ ነበረ ሁሉ እኛም የእርሱ ዓይነት ባሕሪን ተላብሰን መልካም የሚባሉ ነገሮችን ማከናወን ይገባናል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.