2017-03-17 16:34:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በካርፒ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሂዳሉ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ኤሚሊያ ሮማኛ ክፍለ ሃገር ሞደና አውራጃ በሚገኘው በካርፒ ሰበካ ሐዋርያዊ ግብኝት እንደሚያካሂዱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ያሰራጨው ዜና አስታወቀ። ከተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለውም፥ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ስምንት ሰዓት ከሩብ አገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፕተር ማረፊያ ተነስተው ልክ ዘጠኝ ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ካርፒ በሚገኘው ዶራንዶ ፐትሪ ስፖርት ሜዳ እንደሚደርሱም ይጠበቃል።

ልክ ከጠዋቱ አስር ሰዓት ተኩል በከተማይቱ በሚገኘው በሰማዕታት አደባባይ ደርሰው በካርፒ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ካቪና የእንኳን ደሃን መጡ መልእክት ተደምጦ እንዳበቃም በኤሚሊያ ሮማኛ ብፁዓን ጳጳሳት ታጅበው ከክፍለ ሃገሩ የተወጣጡ ምእመናን ያሳተፈ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁም እኩለ ቀን ላይ ጸሎተ መልአከ እግዚኣብሔር ይደግማሉ። እንደ መርሐ ግብሩ መሠረትም በከተማይቱ አዲስ የተገነቡትን የቅድስት አጋታ፡ የኖቪ ቅዱስ አንጦንዮስ ቤተ ሱባኤና የከተማይቱን ካቴድራል ሦስት መሰረተ እምን ይባርካሉ፡ ቀጥለውም ልክ አንድ ሰዓት ተኩል ካርፒ በሚገኘው ጳጳሳዊ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጻ በሚገኘው ማእድ ቤት ከመላ የኤሚሊያ ሮማኛ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ምሳ ከተቋደሱ በኋላ ከሰዓት በኋላ ልክ ሦስት ሰዓት ላይ በዚያ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ውስጥ ባለው ቤተ ጸሎት በካርፒ ከሚገኙት ካህናት ደናግል የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ተገናኝተው ቃለ ምዕዳን ይለግሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከካህናቱ ደናግል ገዳማውያንና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ተሰናብተው ለግል ጸሎት ወደ ካርፒ ካቴድራል ይሄዳሉ። ጸሎትና አስተንትኖ አከናውነው እንዳበቁም እ.ኤ.አ. በክልሉ በ 2012 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሳቢያ በከባድ የመፍረስ አደጋ ወዳጋጠመው ዳግም ታድሶ እስኪገነባ ድረስ ከመንፈሳዊ አገልግሎት ውጭ ሆኖ በመታደስ ላይ ሚገኘው ሚራንዶላ ወዳለው ካቴድራሉ ፊት ባለው አደባባይ ተገኝተው እዛው በብዙ ሺሕ የሚገመት ሕዝብ በተገኘበት በርእደ መሬቱ ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ለማሰብ የፍትሐት ጸሎት መርተው ቃለ ምዕዳን እንደሚለግሱ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ እንዲህ ባለ ሁነት ቅዱስነታቸው የካርፒ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ልክ አምስት ሰዓት ተኩል በሄሊኮፕተር ተሳፈረው ከምሽቱ ዘጠኝ ሰዓት ተኩሉ አገረ ቫቲካን ይገባሉ ተብለው እንድሚጠበቁም አስታውቋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የዚያ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለሚታደለው የካርፒ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ካቪና በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስ አባታችን ያንን እ.ኤ.አ. ግንቦት ወር 2012 ዓ.ም. በርእደ መሬት አደጋ እጅግ ለተጠቃው በዚያኑ ወቅት መንፈሳዊና ሰብኣዊ ድጋፋቸው ላቀረቡለት ክልል ሕዝብ ሊጎበኙ በመፍቀዳቸው የመላ ክፍለ ሃገር ኢሚሊያ ሮማኛ ሕዝብ እጅግ ደስ መሰኘቱንና የዚያ ክልል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እምነት እምነቷን ለማጽትና ቃለ ምዕዳን ለመቀበል መታደሏ ለሁሉም አቢይ የሐሴት ምክንያት መሆኑ ገልጠዋል።

ካርፒን እንደ ሚጎበኙ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ እንዳስታወቀ የካርፒ ሰበካም ሆን የክልሉ ህዝብ ያልጠበቀው በመሆኑ በእውነት በሁሉም ልብ ውስጥ ደስታን ፈጥሯል ብለው በዚህ አጋጣሚም ያ ክልል ቅዱስታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መጎብኘቱንም አስታውሰው፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸሰኮ በዚያ ክልል የዛሬ 5 ዓመት በፊት ተከስቶ የነበርው ርእደ መሬት ያስከተለው ጉዳት ብሎም የዳግመ ግንባታው ሂደት እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ካርፒን ሊገበኙ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው እንደሚጠናቀቅና በዚህ አጋጣሚ አስታውሰው፡ ያንን በርእደ መሬት የተጎዳው ሕዝብ ለመርዳት በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማሕበር ቅርንጫ አማካኝነት ብዙ ሥራ ተከናውኗል አሁንም እየቀጠለ ነው። ከመላ ጎደል ዳግመ ግንባታው ተጠናቋል ለማለት ይቻላል የኤኮኖሚው ዘርፉም የሥራ እድሉም እየተሻሻለ ነው ብለዋል። በመጨረሻም በሳቸው የሚመራው ሰበካ በችግር ውስጥ የሚገኙትን ቤተሰቦች ባለ ትዳሮች ወጣቶች በተለይ ደግሞ በችግር ላይ ወድቀው የሚገኙትን ሁሉ መንፈሳዊ ሰብኣዊና ግብር ገባዊ ድጋፍ በማቅረብ ላይ ይገኛል ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠናቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.