Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ \ ስብከቶች

ቅዱስነታቸው "“በምንም ዓይነት ሁኔታ በቁሳቁሶች እና በስጋዊ ምቾቶች መመካት የለብንም” ማለትቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጉበት ወቅት።

17/03/2017 17:19

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 7/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ያሰሙት ስብከት በእለቱ በላቲን ስርዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ከሉቃስ ወንጌል 16: 19-31 ላይ በተወሰደው የድኻው የአልዓዛር እና የአብታሙ ሰው ምሳሌ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበር ለመረዳት ትችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌ ዛሬ በእዚህ ዘመን የምንኖር እኛንም ይመለከተናል ካሉ ቡኃላ ብዙን ጊዜ በየመንገዱ ወድቀው ለሚገኙና መጠለያ ለሌላቸው ሰዎች ተገቢውን እንክብካቤ እያደረግን ባለመሆናችን የተነሳ የሐብታሙን ሰው ባሕሪ በመላበስ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

“በምንም ዓይነት ሁኔታ በቁሳቁሶች እና በስጋዊ ምቾቶች መመካት የለብንም” ያሉት ቅዱስነታቸው በከንቱ ነገሮች፣ በኩራት እና በሀብት መመካት ከእግዚኣብሔር ያርቃል ብለዋል። ይህንንም ለማረጋገጥ ከተፈለገ በእግዚኣብሔር የሚታመኑ ሰዎች ሁሉ ፍሬያማ መሆናቸውን፣ በራሳቸው እና በሐብታቸው የሚመኩ ሰዎች ሁሉ ደግሞ የሚመኩት ራሳቸው በሚቆጣጠሩት ሐብትና ንብረት ላይ ብቻ በመሆኑ የተነሳ ከንቱ የሆነና እርካታ የማይሰጥ ኑሮ እየኖሩ መሆናቸውን ማይት ብቻ በቂ ነው ብለዋል።

ሰዎች በሐብት፣ ጊዜያዊ በሆኑ ነገሮች በአጠቃላይ በቁሳቁሶች በመመካት ራሳቸውን በእነዚህ ነገሮች ዙሪያ ብቻ አጥረውና ዘግተው በሚኖሩበት ወቅት ሁሉ የሕይወት አቅጣጫ ይጠፋባቸዋል፣ ውስን መሆናቸውንም ይዘነጉታል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም እውነታ በዛሬው ወንጌል (የሉቃስ ወንጌል 16: 19-31) ላይ ከተጠቀሰው በየምሽቱ የእራት ግብዣ ያዘጋጅ የነበረውን እና በደጁ ተኝቶ በድኽነት ሲሰቃይ የነበረውን ድኻ ሰው ችላ ካለው የሐብታሙ ሰው ምሳሌ መረዳት ይቻላል ብለዋል።

ይህ ሐብታም ሰው በደጁ ላይ አንድ ድኻ ሰው እንዳለ ያውቅ ነበር። ስሙንም በሚገባ ያውቅ ነበር፣ ነገር ግን ለዚህ ድኻ ሰው ምንም አይነት እንክብካቤ አላደረገም። ታዲያ ይህ ሰው ኃጢያተኛ ነውን? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አዎን ይህ ሐብታም ሰው ኃጢያተኛ ነው ተጸጽተው ወደ እርሱ የሚመለሱትን ሁሉ እግዚኣብሔር ይቅር ይላቸዋል ይህ ሐብታም ሰው የነበረው ልብ ግን በቀጥታ ወደ ሞት ጎዳና የሚያመራ ልብ ነበር የነበረው ብለዋል።

ይህ ሀብታም ሰው ኃጢያተኛ ብቻ ነው፣ ምግባረ ብልሹ የነበረ ሰው ጭምር ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም በደጁ የነበረውን ድኻውን አልዓዛር በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደ ነበረም ጥንቅቆ ያውቀ እርሱን ለመርዳት ግን ምንም ፈቃደኛ ስለነበረ ነው ብለዋል። ተስፋቸውን በራሳቸው ላይ ያደረጉ ሰዎች ወየውላቸው ምክንያቱም የደነደነ ልብ የያዙ ሰዎች ሁሉ መጨረሻቸው አሳዛኝ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ዓይነት ጎዳና ላይ የምንራመድ ሰዎች ከሆንን ልባችን እንዲፈውስ ማድረግ በጣም ሊከብደን ይችላል ብለዋል።

መጠለያ የሌላቸው ሕጻናት በየመንገዱ እየለመኑ ብናገኛቸው ልባችን ምን ዓይነት ስሜት ይሰማዋል? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የቤት ኪራይ መከፈል ባለመቻላቸው የተነሳ ለጎዳና ሕይወት የተጋለጡ ሰዎችን በምናይበት ወቅት ምን ዓይነት ስሜት ይሰማን ይሆን? ያሉት ቅዱስነታቸው ዝም ብለን የተወሰኑ ሳንቲሞችን ብቻ ሰጥተን ማለፍ ብቻ በቂ አይደለም ብለዋል።

እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉትን ነገሮች በምናይበት ወቅት ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሳንቲም ስጥተን ማለፍ ብቻ በቂ አይደለም ያሉት ቅዱስነታቸው ድኾችን ቀርቦ ማነጋገርና በእጃችንም ልንዳስሳቸው ይገባል ብለው የአልዓዛርን ቁስል የዳሰሰው ሐብታሙ ሰው ሳይሆን ውሾች እንደ ነበሩም ተቅሰው እኛም የተቸገሩ ሰዎችን ቀርበን በማናዋራቸው እና በምንዳስሳቸው ወቅቶች ሁሉ ልባችን ወደ እግዚኣብሔር ይቀርባል ካሉ ቡኋላ ኃጢያተኛ ሰው በኃጢያቱ ተጸጽቶ ሊመለስ ይችላል ልቡ የደነደነና ብልሹ የሆነ ሰው ግን ወደ እግዚኣብሔር መመለስ ያዳግተዋል፣ እግዚኣብሔር መልካሙን መንገድ ያሳየን ዘንድ መጸለይ ይገባል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

17/03/2017 17:19