2017-03-09 08:21:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሮም የቅድስት መንበር የአስተዳደር አካልት ጋር በመሆን ለ6 ቀናት ያህል የሚቆይ ሱባሄ ማድረግ ጀመሩ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም ከሚገኙ የቅድስት መንበር የአስተዳደር አካላት ጋር በጋራ በመሆን በየካቲት 22/2009 ዓ.ም የተጀመረውን ዐብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ከሮም ከተማ 218 ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኘው ዲቪኒ ማየስትሮ ዲ አሪቻ ተብሎ በሚጠራው የስቡሄ ስፍራ ከየካቲት 26/2009 እስከ መጋቢት 1/2009 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሱባሄ የፍራንችስካዊያን ካህን በሆኑ በአባ ጁሊዮ ማኬሊን መሪነት በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮና የሥራ ባልደረቦቻችውን ባሳተፈው በየካቲት 28/2009 ዓ.ም. ምሽት ላይ ክቡር አባ ጁሊዮ ማኬሊን ያደረጉት አስተንትኖ  ከማቴዎስ ወንጌል (26:36-46) በተወሰደው እና ኢየሱስ በጌተ ሰማኒ ያደረገውን ጸሎት፣ ከእዚያም ቡኋላ በጠላቶቹ መያዙን በሚያወሳው ታሪክ ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ አስተንትኖ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ኢየሱስ በደብረዘይትና በገሊላ በሚገኘው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ያደርገውን ጸሎት በማውሳት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ክቡር አባ ጁሊዮ ማኬሊን በእነዚህ ሁለት ስፋራዎች የተፈጸመው ተግባሮች በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ የሚመሳሰል ነገር እንዳላቸው ጠቁመው በመጀመሪያ አጋጣሚ ማለትም በደብረ ዘይት ተራራ ሐዋሪያው ጴጥሮስ እና የተቀሩት ሐዋሪያት ኢየሱስ “ነብይ በኢየስሩሳሌም ሊሞት ይገባዋል” ብሎ በነገራቸው ወቅት በፍጹም አልተረዱትም ነበር በለዋል።

በሁለተኛው ገጠመኝ ማለትም በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ደግሞ ኢየሱስ “ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ብሎ መናገሩን በማስታወስ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ክቡር አባ ጁሊዮ ማኬሊን በደብረ ታቦር ተራራ እግዚኣብሔር አባት ልጁን ኢየሱስን ያጽናናበት ድምጽ ይሰማ ነበር፣ ነገር ግን በጌተ ስማኒ ኢየሱስ መከራውን የመቀበል ያለመቀብል ትግል ላይ ነበረ እንጂ ምንም ዓይነት ድምጽ አልሰማም ነበር ብለዋል።

በጌተ ሰማኒ ኢየሱስ የእግዚኣብሔር መልካም ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ነው የጸለየው፣ ይህም የእግዚኣብሔር መልካም ፈቃድ ልጁ እንዲድን ነው እንጅ እንዲሞት አልነበረም በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ክቡር አባ ጁሊዮ ማኬሊን ኢየሱስ ወደ እዚህ ምድር የተላከው ሕዝቦቹን ከሞት እንዲታደጋቸው በእምነት እና በፍቅር እንዲያድጉ ሊረዳቸው ነበር የመጣው ብለዋል።

 ይህንንም ምልአት ባለው መልኩ ለመፈጸም ራሱን እስከ መስቀል ሞት አሳልፎ መስጠቱን በመግለጽ አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ክቡር አባ ጁሊዮ ማኬሊን ኢየሱስም ሐዋሪያቱ እርሱ በጌተ ሰማኒ ፈጽሞ የነበረውን ገድል በሕይወታቸው ይተገብሩ ዘንድና ሕዝቡም እግዚኣብሔርን በሙሉ ልባቸው እና ነብሳቸው ሕይወታቸውን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ እንዲደርሱ ለማስተማር ፈልጎ የፈጸመው ገድል ነው ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.