2017-03-08 17:08:00

ቫቲካን፥ በዓለም አቀፍ የሴቶ ቀን ዋዜማ የሴቶች ምክር ቤት ቅዋሜ በቫቲካን


እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት በሥሩ የሚተዳደር በዚህ በባህል ምክር ቤት ውስጥ ለሴቶች ተገቢ ሥፍራ እንዲሰጣቸውና ድምጻቸውም ተሰሚነት መስጠት በሚል ዓላማ ያቋቋመው ቋሚ የሴቶች መማክርት ማኅበር ይኸው እ.ኤ.አ. መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዋዜማ በይፋ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አድራሽ መተዋወቁ የተሰጠው ጋዜጣው መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ አስታወቁ።

የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በ 37 በዚህ የሴቶች መማክርት ማኅበር አባላት ተሸኝተው የመሩት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ መሆናቸው የገለጡት ማሶቲ በማያያዝም የዚህ የሴቶች መማክርት ማኅበር አስተባባሪ ሮማ በሚገኘው ሉምሳ መንበረ ጥበብ የዓለም አቀፍ የሥነ ግኑኝነት ምርምር ዘርፈ ጥናት አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ኮንስወሎ ኮራዲ መሆናቸውንም ጠቁመው፡ ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም፥ በዚህ ምክር ቤት ውስጥ እስካሁን ድረስ የሴቶች መማክርት ማኅበር ያልነበረው ብቻ ሳይሆን እግዚኣብሔር በአምሳይውና በአርአያው ሰውን ፈጠረ፡ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው፡ ስለዚህ ማኅበሩ ይኸንን ምሉእ እንዲሆን ወንድና ሴቶች አድርጎ ፈጠራቸው የሚልውን እውነት መግለጫ መሆን አለበት በሚል እማኔ የተቋቋመ ማኅበር መሆኑ አብራተው፡ የዚህ የሴቶች መማክርት ማኅበር በመመሥረቱም ምክንያት በማኅበሩ ውስጥ የሚሰጠው ምክር እና የምክር ቤቱ እይታም ምሉእ እንዲሆን እድርጎታል። ይኽ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚያከውናቸው ተግባሮች ተባእታዊ እይታ ላይ የተመሰረተ ብቻ ሳይሆን አንስት እይታ ያለውና ህኖ ሁለቱን እይታዎች የሚስተናገድበ ይሆናል። በሌላውም ረገድ የቤተ ክርስቲያን ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ ቋንቋ ያለውን ውበቱና ጥልቀቱን እጅግ ያስውበዋል ጠሊቅ ያደርገዋል እንዳሉ ገልጧል።

የዚህ የሴቶች መማክርት ማኅበር አባላት እንዲሆኑም የተመረጡት በፖለቲካዊ መድረክ የተጠመዱት ከያንያን ጋዜጠኞች የመናብርተ ጥበብ መምህራን የመንፈሳዊ ማሕበር አባላ ደናግል ያካተተ ሲሆን። ከቫቲካን ራዲዮም ውስጥ ጋዜጠኛሮበርታ ጂሶቲና እንዲሁም ከቫቲካን አቢያተ መዘክር የዘመናዊ የስነ ቅብና ስነ ንድፍ ቅርስ ጉዳይ ኃላፊ ሚኮል ፎርቲ በአባልነት እንደሚገኙበትና በጠቅላላ አባላቱ ከተለያየ የባህል መድረክ ከተለያዩ አገሮችና ሃማኖቶች ጭምር የተወጣጡ መሆናቸውና ከእነዚህም ውስጥ የቲዮሎጊያ ሊቅ የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሻሃራዛድ ሁሻማንድም እንደሚገኙበት ማሶቲ ይጠቁማሉ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የዚሁ በባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሥር ለሚታቀፈው የሴቶች መማክርት ማኅበር አቀነባባሪ ኮንስወሎ ጆራዲ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ወንዶች ከሴቶች የተለዩ እንደ መሆናቸው መጠን ሴቶችም ከወዶች ለየት ያሉ ናቸው የሁለቱም ጾታዎች እኩለት ሲባል የእያንዳንዳቸውን ወንድና ሴቶች አድርጎ ፈጠራቸው በሚለው የእግዚኣብሔ ይሁን ባይነት ሥልጣን ዘንድ ያለው አንዱን ጾታ ከሌላው ጾታ ለየት የሚያደርገው ልዩ የገዛ እራሱ መሆናዊ ባህርይ መሰረዝ ወይም መሆናዊው መለያቸው ማደላደል ማለት ሳይሆን በሰብአዊ መብትና ክብር ላይ ያተኰረ በመብትና ክብር ያለ መበላለጥ ከፍና ዝቅ የማለት ደረጃዊ የአቀማመጥ ልዩነት የለም ማለት ነው እንዳሉ ማሶቲ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.