Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

ቅዱስ አባታችን፥ የድኾችን እሮሮ ማዳመጥ

ቅዱስ አባታችን፥ የድኾችን እረሮ ማዳመጥ - ANSA

27/02/2017 17:13

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 24 ቀን 2017 ዓም. በአገረ ቫቲካን ጳጳሳዊ የሥነ ምርምር ተቋም “ውኃ የማኘት መብት” በሚል ርእስ ዙሪያ እንዲወያ ባሰናዳው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው የወንድም እረሮ ማዳመጥ የተፈጥሮ የዚያች የምንኖርባት የሁሉም የጋራ ሃብት የሁሉም ቤት የሆነውን የመሬት አረሮ ማዳመጥም ማለት ነው የሚል ሃሳብ ያማከለ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸቺሊያ ሰፒያ ገለጡ።

ውኃ ባለበት ሥፍራ ሁሉ ሕይወት አለ። ውኃ ባለበት ቦታ ብቻ ነው እድገት ተቻይ የሚሆነው፡ በመሆኑም ይኸንን የሁሉም የጋራ ጸጋ የሆነውን ውኃ የመንከባከብ ኃላፊነት ማለት ለሁሉም ማዳረስ ማለት መሆኑ ቅዱስ ፍራቸስክ ዘአሲዚ ውኃ የጋራ ትሁና ንጹሕ ጸጋ ነው ከሚለው ጥልቅ አስተሳሰብ ጋር አጣምረው በማብራራት፡ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ማግኘት የሁሉም ሰው ዘር መብትና ክብር ነው፡ የሚጠጣ ውኃ የማግኘቱ መብት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ነው። ከዚህ መብት የሚነጠል የሚገለል ማንም መኖር የለበትም። ውኃ የጋራ ኃብት ነው፡ የምንኖርበት ዓለም ምኅዳር በጠቅላላ ለእኔ ባይነትና ስግብግ መንፈስ አማካኝንት እየተበዘበዘ የተፈጥሮ ኃብት የጥቂቱ ብቻ እየሆነ በሰዎች መካከል ተጠቃሚና ተመልካች የሚል መለያየትን እያስከተለ ተጠቃሚና ተመጽዋች በሚል አጥሮ አየለያየ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያጠቃልለው ንጹህ የመጠጥ ውኃ የማግኘት መብት በብዙ የዓለማችን ክልሎች ሲጣስ ይታያል ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘውም፥ የውኃ አጠቃቀምና የመጠጥ ውኃ ለሁሉም ለማዳረስ ውኃ በሕይውት ያለው ማእከልነት የሚያስተውል ፖለቲካ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። የውኃ ሃብት በተመለከተ የተባበሩት መግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. ያስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ያደረገ የውኃ ሃብት የማስተዳደር ሂደት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ንጹሕ የመጥ ውኃ ማግኘት ለሕይወት መሠረት ነው። በመሆኑም በተፋሰስና የተፈጥሮ ኃብት ላይ የሚከሰተው በደል የተፈጥሮ የውኃ ሃብት ብከላ ሰውን ለብዙ ችግር እያጋለጠ ነው፡ በዚህ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተገማመሰ በሚካሄዱ ተፈራረቅ ጦርነቶች አማካኝነት አየታየ ያለው ሦስተኛው የዓለም ጦርነት የውኃ ሃብት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሽቅድድም አንዱ ለዚህ ዓቢይ ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልጠው። ስለዚህ ወደዚህ አቢይ የዓለም ጦርነት ከመገባቱ በፊት ውኃ ለሰው ልጅ የተሰጠ ሰብአዊ ሃብት መሆኑ በሚገባ እውቅና አግኝቶ የሁሉም ንጹሕ ውሃ የማግኘት መብት ለማስከበር አሁንም ጊዜው አለን። በኋላ እንዳይቆጨን ከወዲሁ ልናስተውለው ይገባል እንዳሉ ሰፒያ አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንጹሕ ውኃ እጥረት በሚያስከትለው በሽታ ሳቢያ እንዲሁም በውኃ እጥረት ሳቢያ በየዕለቱ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሕጻናትና በጠቅላላ የሰው ልጅ ብዛት አስደግፎ የሰጠው ዘገባ በትልቅ ሃዘን ጠቅሰው አሁንም የብዙ ሰዎች ሕይወት ከሞት አደጋ ለማትረፍ ጊዜው አለ ስለዚህ የሰው ልጅ ንፁሕ የውኃ መጠጥ የማግኘት ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲጠበቅ ሁሉም በተለይ ደግሞ የመንግሥታትና የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አቢይ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። ይኽ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ከተከበረ ሁሉም የመጥጥ ውኃ እንዲያገኝ በግንባር ቀደም ከተንቀሳቀስን የብዙ ሰዎች ሕይወት ከሞት እናድናለን፡ የግኑኝነት ባህል በማስፋፋት እርስ በእራሳችን ልንተሳሰብ ይገባናል፡ እንዳሉ የገለጡት ልክት ጋዜጠኛ ሰፒያ አያይዘውም፥ በውኃ ዙሪያ የሚከሰተው ችግር የመጥጥ ውኃ እጥረት ለመቀረፍ ሁሉም ኃይሎች ማለት የሥነ ምርምር ሊቃውንት ባለ ኃብቶች መንግሥታት የፖለቲካ ኣካላት ለአዲስ ፍጥረት መረጋገጥ ተፈጥሮንና ፍጥረትን የሚያፈቅር መንፈስ በማስፋፋት የተቻላቸውን እንዲያደርጉ ተጠርተዋል። ለዚህ አንድ አላማ ሁሉም በጋራ የፍጥረትንና የተፈጥሮን እሮሮ በማሰናገድ እንዲያዳምጡና ምላሽ በመስጠት ኃላፊነት አብሮና ተዋህዶ ለጋራ ጥቅም በጋራ መቆምን እንዲያረጋግጡ ማሳሰባቸው አስታውቋል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፥ ሁሉም በእኩል የተፈጥሮ ኃብት ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እግዚአብሔር ለብቻችን አይተወንም በማለት በትንሹ አቅማችንና ጥረታችን የምንኖርባትን የሁላችን ማደሪያ የሆነችውን ምድር መረጋጋትና መተሳሰብ የሰፈነባት ማንም ኢቤተኛ የማይሆንበት ለሁሉም የሁሉም ጥላና ሃብት ለሁልም የሚዳረስበት እንዲሆን ሁሉም ለሕይወት የሚያስፈልገውን በማግኘት በክብር እያደገ ክብሩና መብቱም ተጠብቆለት ለመኖር የሚችልባት መሬት እንድትሆን ሁላችን የሚገባንን አስተዋጽኦ እናበርክት እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ቸቺሊያ ሰፒያ አስታውቋል።    

27/02/2017 17:13