Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

የተባበሩ የአመሪካ መንግሥታ፥ ዓለም አቀፍ የሕዝባውያን እንቅስቃሴዎች ማኅበረሰብ ዓውደ ጉባኤ ያወጣው መግለጫ

የተባበሩ የአመሪካ መንግሥታ፥ ዓለም አቀፍ የሕዝባውያን እንቅስቃሴዎች ማኅበረሰብ ዓውደ ጉባኤ ያወጣው መግለጫ - OSS_ROM

24/02/2017 17:00

እ.ኤ.አ. ከየካቲት 16 ቀን እስከ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ካሊፎርኒያ ግዛት በምትገኘው በመደስቶ ከተማ ዓለም አቀፍ የሕዝባውያን እንቅስቃሴዎች ማኅበረሰብ፥ ስደት የዘር ጥላቻ የሥራ የመጠለያ መብት ምኅዳራዊ ፍትሕ የተሰኙት የተለያዩ ማኅበራዊ ነክ ርእሶች ኤኮኖሚያዊ ዓለማዊ ትሥሥር የጠቆሰው ማኅበራዊ ተገሎነት በማውገዝ እይታ ሥር በመመልከት መወያየቱና ወደ እዚሁ ዓውደ ጉባኤውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም የቤተ ክርስቲያን የማኅበረሰብአዊ ጠመቅ ትምህርት ላይ ተንተርሰው መልእክት አስተላልፈው እንደነበርም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቲዚያና ካምፒዚ በማስታወስ ይኽ  የካሊፎርኒያው ጉባኤ ሁሉም ቁምስናዎች የሰው ልጅ በተለይ ደግም ስደተኛው የሚስተናገድባቸው ቤተ መቅደስ ይሆኑ ዘንድ የሚያሳስብ ጥሪ አዘል ሰነድ ማውጣታቸውንም ገልጧል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አስተላልፈዉት  በነበረውም መልእክት በዓለማችን የሚታየው የሰውን ዘር ቤተሰብ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጠው የጥቂቱን ጥቅምና ፍላጎት የሚዋስ የሰው

ን ልጅ ሰብአዊ ክብር የሚያጠቃ የሁላችን መኖሪያ የሆነውን ተፈጥሮ የሚጎዳ የገንዘብ ኃብት ያማከለ ዓለም የሚከተለው አምባገነንናዊ ሥልት ተጠያቂ መሆኑ ያስገነዘቡ ሲሆን፥

እያንዳንዱ ሰው የተቀደሰና እኩል ሰብኣዊ መብትና ክብር አለው

ዓውደ ጉባኤው ያወጣው የፍጻሜ ሰነድ ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልእክትና የማኅበረሰብአዊ ሥልጣናዊት ትምህርታቸውን መሠረት በማድረግ፥ “በዓለማችን እየታየ ያለው ሁሉም ታሪካዊ ለውጥና ይኸንን ተከትሎ እየተረጋገጠ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ሰውንና ምኅዳርን እየጎዳ ነው፡ ይኽ ችግር ለመቅረፍ የሁሉም ሕዝባውያን እንቅስቃሴዎች ተሳትፎና የተቀናጀ እርምጃ ያስፈልጋል፡ ሁሉም የሰው ልጅ የተቀደሰና ክቡር እኩል የሆነው መጠለያ  ምግብ ትምህርት ጤና ጥበቃ ሥራ የማግኘት መብት ያለው ፍጡር ሆኖ እያለ ይኸንን እውነት ወደ ጎን በማድረግ በቆዳ ቀለም በፆታና በአካላዊ ብቃት የጎሳ ወይንም የሃይማኖት ልዩነት መሠረት ያደረገ በሰው ዘር ላይ የሚፈጸመው በደል የአመሪካ ማኅበራዊ አናስራዊ ኃጢኣት ተብሎ የሚነገርለት የነጮች የበላይነት የሚል ርእዮተ ዓለም ተመልሶ አሁንም በተለያየ መልኩ ብቅ እያለ የዘረኝነት ችግር ዘለአለማዊ የሚያስመስለው ሁነትና በወቅታዊው ዓለም ሲከሰትም የሚችል መሆኑ ያለው ተጨባጭ ታሪክ ያመላክታል።። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም በኤኮኖሚው ዓለም ሥርዓትና ሕግ አልቦ የሆነው ንዋያዊነት ወይንም የግል የኤኮኖሚ ዘዴ እየተረጋገጠ ለሰው ልጅ መሰረታዊ አስፍፈላጊ  የሆነውን የማካበትና ብዙዎችን ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሰረታውን ነገሮች ንዳናያገኙ እያደረገ ስፍር ቁጥር የሌለው የዓለም ሕዝብ ለከፋ ድኽነት እየዳረገ ነው፡ የኃይማኖት መሪዎች ይኸንን ስልት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የማውገዝና ሁሉም መብታቸው ተጥሶ ወደ ድኽነት የተወረወሩትን ለመጣበቅና ስለ እነዚህ ሰዎች ሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጓች መሆን ይጠበቅባቿል፡ በአሁኑ ወቅት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እየተከተለው ያለው የስደተኛ የማስተዳደሪያ ደንብ ጉባኤው በስፋት ትችት እንደሰጠበትም ጉባኤ ካወጣው የፍጻሜ ሰነድ ለመረዳት እንደሚቻልም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ካምፒዚ አስታውቋል።

የኃይማኖት ማኅበረሰብ ተጨባጩን ወቅታዊው ችግር በነቢይነት መንፈስ መግጠም ይኖርበታል

የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ በሁለተኛው አንቀጽ የኃይማኖት ማኅበረሰቦች የሰው ልጅ ለአደጋ የሚያጋልጡትን ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ሰብአዊ ችግሮችን  በጥልቀት በመለየት ወቅታዊው ሁኔታን በነቢይነት መንፈስ በመግጠም ውሉደ ክህነት ምአመናን በጽናት  የመተባበርና የመደጋገፍ እሴቶችን በማስፍፋት ችግሮችን በመቅረፍ ተልእኮ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያብራራ የኃይማኖቶች ማኅበረሰብ የሚኖረው ሚና ላይ በማተኮርም መላውን የሰው ዘር ቤተሰብ ስደተኛም ከዘረኝነት አደጋ መከላከል ሥራ መጠለያ የማግኘት መብቱም እንዲጠበቅና የምኅዳር ጤንነት መንከባከ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ያመላክታል። ከዚሁ ጋር በማያያዝም እ.ኤ.አ. ከግንቦት 1 ቀን እስከ ግንቦ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የጸረ ዘረኝነት የጸረ ጥላቻ ቂም በቀል መንፈስና በቤተሰብ ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት የሚቃወም የእርምጃ ሳምንት ተብሎ ተሰይሞ ሁሉም ይኸንን የሚያጎላ ተግባር እንዲፈጽም የሚነቃቃበት ሳምንት እንደሚሆን ሰነዱ ያመለክታል።

ለስደተኞች ድጋፍና ትብብር

የኃይማኖቶች ማኅበረሰብ ምእመና ቁምስናዎች በጠቅላላ እያንዳንዱ ሰው ክብሩና ቅዱስ መሆኑ በማበከር ወደ መጣበት መሸኘት የሚለውን ጠቅላይ ውሳኔ በመቃወም በኃይማኖት በዘር በፖለቲካ አመለካከት ምክንያት የሚሰደዱትን ለከፋ አደጋ የሚጋለጡትን ሁሉ በመደገፍ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም የጉባኤው የፍጻሜው ሰነድ ጥሪ ሲያቀርብ። ይኽ ሰው ክቡርና ቅዱስ ነው የሚለው አመለካከትም ከዚያ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በስፋት የሚታወቀው የአዲስ ቤተ መቅደስ እንቅስቃሴ በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች በክርስቲያን ማኅበረሰብ ዘንድ ወደ መጡትበት እንዲሸኙ የሚባሉት የሕገ ወጥ ሰደተኞች ተከትሎም ለጸረ ሰብአዊ ተግባሮች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ማስተናገድና ስለ እነርሱ መሟገት የሚለው ዓላማ የሚያስተጋባ መሆኑ የገለጡ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቲዚያና አያይዘውም በዚህ ሳምንት ማብቅያም በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የካቶሊክና የወንጌላውያን አቢያተ ርስቲያን የአይሁድ ሙክራቦች በጠቅላላ በችግር ላይ የሚገኙትን ስደተኞችን ያንን አቢያተ ክርስቲያናት የእምነት እና የአምልኰ ሥፍራዎች ሁሉ የሰው ልጅ  ከተለያየ ችግር በማምለጥ መጠለያ የሚያኝባቸው ሥፍራ እንደነበሩ የሚነገረው እውንተኛው ታሪክ በመከተልም አቢያተ ክርስቲያን የሰው ልጅ ከአደጋ የሚተርፍበት ሥፍራ እንዲሆኑና ስደተኞችን የሚያስተናግዱና የሚከላለኩ መሆን እንደሚጠበቅባቸው የፍጻሜው ሰነድ ያመለክታል ብሏል።                                                                              

24/02/2017 17:00