2017-02-21 10:43:00

ቅዱስነታቸው ክርስቶስ የበቀል ስሜትን አስወግደን የፍቅርና ትክክለኛ የፍትህ መንገድ እንድንከተል ያስተምረናል” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየካቲት 12/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የስርዓተ ሊጡርጊያ አቆጣጠር ከማቴዎስ ወንጌል 5: 38-48 ላይ የተወሰደ እና ኢየሱስ በተራራ ላይ ያደረገው ስብከት ቀጣይ ክፍል ላይ ያተኮረ አስተምህሮ ማድረጋቸው ታውቁዋል።

“ክርስቶስ ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ’ (ማቴ. 5.38) የሚለውን የበቀል ስሜት አስወግደን በፍቅር ሕግ ላይ የተመሰረተ፣ ትክክለኛ የፍትህ መንገድ እንድንከተል ያስተምረናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ክፉን ነገር በትዕግስት እንዲያልፉ ብቻ ሳይሆን የሚመክራቸው ክፉን በመልካም ነገር እንዲመሉስም ጭምር መሆኑን አብራርተው በእዚህ መንገድ ብቻ ነው የሰይጣን ሰንሰለት ሊበጣጠስና ትክክለኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችለውም በእዚህ ዓይነቱ መንገድ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ኢየሱስ “ክፉን በክፉ አትመልሱ” ከሚለው አስተምህሮ አሻግሮ በመሄድ ሕጋዊ መብታችንን የሚጋፋ በሚመስል መልኩ “አንደኛ ጎንጭህን ለሚመታህ ሁለተኛውን ጎንጭ አዙርለት፣ እጄጠባብህን አውልቀህ ስጥ” እስከ ማለት ደርሶ እንደ ነበረ በመግለጽ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ይህም ለፍቅር ስንል መከፈለ የሚገባንን መስዋዕትነት ያሳያል ብለዋል።

“ነገር ግን ይህ ታላቅ መስዋዕትነት ፍትህን ችላ ማለት ወይም ፍትህን መጻረር ማለት አይደለም” ያሉት ቅዱስነታቸው በተቃራኒው የሚያሳየው የክርስቲያናዊ ፍቅር እንዴት ባለ መልኩ በምሕረት መፈጸም እንዳለበት እና ይህም ፍትህን ለየት ባለ መልኩ የመግለጫ ምልክት እንደ ሆነ ለማሳየት ፈልጎ እንደ ሆነም ገልጸዋል።

ኢየሱስ በፍትህና በበቀል መካከል ያለውን ልዩነት ሊያሳየንና ሊያስተምረን ፈልጉዋል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ፍትህን መጠየቅ እና ፍትህን ማከናወን ተግባራችን ሊሆን ይገባል” ካሉ ቡኋላ በሌላ መልኩ ደግሞ በቀልን ከመፈጸም እና የበቀልን ስሜት በማስፋፋት ብጥብጥ ከማንሳት መቆጠብ እንዳለብን ኢየሱስ ያስተምረናል ብለዋል።

“በእርግጥ የክርስቶስ የፍቅር ሕግ ጠላቶቻችን እንድንወድ ይጋብዘናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ እውነታ ግን ክፉ አድራጊዎችንና ድርጊቶቻቸውን ማሞገስ ወይም ደግሞ ማሞካሸት ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም ካሉ ቡኋላ መጠቅ (ወጣ) ባለ መልኩ ስንመለከት በሰማይ ያለው አባታችን “ጸሐይን በክፉዎችና በደጎች ላይ እዲወጣ” እንደ ሚያደርግ ገልጸው ጠላቶቻችን የሚባሉትን ሁሉ፣ እነርሱም በእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳያ መፈጠራቸውን ገልጸው ምንም እንኳን ይህ በእግዚኣብሔር መልክ እና አምሳያ መፈጠራቸው አንድ አንዴ በሚፈጽሙት ክፉ ነበሮች ቢያጠለሹትም ክርስቶስ ግን ሁል ጊዜ በፍቅር ተነሳስተን ክፉን በክፉ እንዳንመልስ ያስተምረናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን ከመደምደማቸው እና የመልአከ እግዚኣብሔርን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከመድገማቸው በፊት እንደ ገለጹት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ይህንን አስቸጋሪ መንገድ በብቃት መጓዝ እንድንችል እንድተረዳን መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ኢየሱስ ባዘዘን መልኩ “የሰውን መብት በእውነተኛ መልኩ በማክበር በሰማይ ያለው አባታችን እውነተኛ ልጆች ሆነን መኖር እንድንችል እንድታማልደን መጸልይ ይገባል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.