2017-02-16 14:12:00

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው የተሰጠን የተስፋ ቃል እኛን ከሌሎች የሚለያየ የተስፋ ቃል አይደለም ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እና እሁድ የጠቅላላ አስተምህሮ ለምዕመናን እና ለሀገር ጎብኝዎች እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን የእዚህ የጠቅላላ አስተምህሮ አንዱ አካል በሆነው በየካቲት 8/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ያደረጉት አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም የክርስቲያን ተስፋ በሚል በተከታታይ ያደረጉት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የተሰጠን የተስፋ ቃል እኛን ከሌሎች የሚለያየ ወይም ደግሞ ሌሎችን እንድንንቅ እና እንድናገል የሚያደርገን የተስፋ ቃል አልነበረም በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ተስፋ ያደረገ ሰው በፍጹም አያፍርም ብለዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

እግዚኣብሔር ምርጥ የሚባሉ ሰዎችን ብቻ ለይቶ የሚያቀርብ እና ሌሎችን ደግሞ የሚያገል አምላክ አይደልም በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከትንሽ ጀምሮ እስከ ትልቅ ድረስ ቤቱ ለሁሉ የሰው ልጆች ክፍት ነው ብለዋል።

ተስፋ አሉ ቅዱስነታቸው ተስፋ በየዋህነትና በትህትና ሰዎችን እንድንገናኝ የሚረዳን የመገናኛ ሰርጥ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ልጅ በነበርንበት ወቅት መመካት ጥሩ ነገር እንዳልሆነ ያስተምሩን ነበር ካሉ ቡኋላ ይህንንም ሐሳባቸውን ለመጠናከር በማሰብ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ “መመካት የሚፈልግ በጌታ ይመካ” ማለቱን አስታውሰው  ሐዋሪያው ጳውሎስ በእዚህ ትምህርቱ በእመነት እና በፍቅር ተመርኩዘን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰጠን የተትረፈረፈ ጸጋ መመካት ይኖርብናል ብለዋል።

እነዚህንም ነገሮች በሕይወታችን በምንለማመድባቸው ጊዜያት ሁሉ በሕይወታችን እና በግንኙነቶቻችን  ውስጥ ሁሉ የእግዚኣብሔር ሰላም እንደ ሚኖር እንረዳለን ያሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ሰላም በውስጣችን አለ ማለት የፍርሃት፣ የተስፋ መቁረጥ ወይም ደግሞ የስቃይ ስሜቶች ሁሉ ከእኛ በነው ይጠፋሉ ማለት ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር እንደ ሚወደን እና ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር እንደ ሚሆን እንዲሰማን ያደርገናል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.