Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ቤተ ክርስትያን \ ቤተ ክርስትያን በአለም

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ፖለቲካ የሕዝቦችን ተጨባጭ ተገቢ ጥያቄ የሚያስተናግድና መልስ የሚሰጥ መሆን አለበት

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ፖለቲካ የሕዝቦችን ተጨባጭ ተገቢ ጥያቄ የሚያስተናግድና መልስ የሚሰጥ መሆን አለበት - REUTERS

15/02/2017 16:52

የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ራይ ተብሎ ለሚጠራው የኢጣሊያ የቴቪዥን ጣቢያ በሚጠቃለሉት በራይ አንድ የተሌቭዥን ስርጭት ከጋዜጠኛ ኢኛዚዮ ኢንግርው ያቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሙሉ ይዞታው በዚያው የቴለቪዥን ስርጭት ተላልፎ የነበረውን የሥርጭት መርሓ ግብር እ.ኤ.አ. የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ በተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አማካኝነት ለንባብ መቅረቡ ሲታወቅ። ብፁዕነታቸው ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ለፓለቲካው ዓለም ጥሪ ያቀረቡም ሲሆን። ጥሪውም ፖለቲካ የሕዝቦችን ተጨባጭ ተገቢ ጥያቄ የሚያስተናግድና መልስ የሚሰጥ መሆን አለበት፡ ፖለቲካ የማስተዳደር ጥበብ እንደ መሆኑ መጠን ተቀዳሚው ዓላማው የሕዝብ ተጨባጭ ተገቢ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት በኢጣሊያና ከኢጣሊያ ውጭ የሚታየው የሥራ አጥነት ችግር በመዳሰስም፡ ይህ ችግር ተቀዳሚና አስቸኳይ ምላሽ የሚያሻውና አጣዳፊ መፍትሄ ሊገኝለት የሚገባው ጉዳይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ያለውን የሥራ አጥነት ችግር እንዲሁም የኤኮኖሚ ቀውስ ግምት በመስጠት ዛሬም እንደ ጥንቱ በኅብረተሰብና በፖለቲካው ዘንድ ማኅበራዊ ትብብር መደጋገፍ የሚለው እሴት ለማንኛውም ማኅበራዊ የጋራው ሕይወት መሠረት መሆን እንደሚገባው ታሳስባለች በማሳሰብ ብቻ ሳትታጠር እሴቱ ላይ የጸኑ የተለያዩ ተጨባጭ መርሐ ግብሮችንም እየከወነች ትገኛለች እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ በሕትመቱ አስነብቧል።

በአሁኑ ወቅት ይላሉ ብፁዕነታቸው ፖለቲካና የፖለቲካው ዓለም ከሕዝብ ተጨባጭ ሁነት እርቆ የመኖሩ ሁነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደሚሉትም በገዛ እራስ ዋቢነት የሚኖር ወይንም ርእሰ ተጠቃሽ ሆኖ የሚታይ  መሆኑ አብራርተው፡ ስለዚህም ከዚህ ዓይነቱ በእራስ ተጠቃሽነት ከመኖር ተገሎ ሕዝብ ተስፋ በማድረግ ተስፈኛ ሕይወት ለመኖ ይችልም ዘንድ የሕዝብ ተጨባጭ ጥያቄ የሚስተናገድ ተጨባጭ መልስ የሚሰጥ መሆን አለበት።

ሕዝበተኛነትና ብሔራዊነት-ብሔርተኝነት የተሰኙት እጅግ አሳሳቢ የሆኑት እጅግ ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጡ፡ በአሁኑ ወቅት የፖለቲካውን ዓለም እየተኩ ያሉት የሚመስሉትን ጠቅሰው። እነዚህ ሁለት  አመለካከቶች ያስከተሉብን ችግር የቅርብ ትውስት ነው፡ ይኽ ደግሞ በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስታወሱት ጉዳይ መሆኑም አስታውሰው፡ ሕዝበተኛነት ወይንም የአብዛኛው ሕዝብ የሚባለው አመለካከት እንደ ፍጹም ዓላማ በማድረግ ሌላውን በማግለል የሚኖር ሥርዓት ማለት ነው፡ ተገቢና ትክክለኛ እሴት ላይ የጸና ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ፕሮፓጋንዳ ላይ የተመሠረተ የሃሰት ተስፋ የሚያቀርብና ብሔራዊነት ደግሞ በእራስ ላይ መታጠፍ የሚል ነው፡ ከእራስ አጥር ውጭ ግልድ ያለ ማለት ምርጫ ነው። ስለዚህ ከዚህ ዓይነቱ ፖለቲካ መቆጠብ ያስፈልጋል። እነዚህ ሁለት ዓይነት አመለካክቶች ማለትም ሕዝበተኛነትና ብሔርተኝነት ከፍርሃት የሚወለዱ ናቸው። ፍርሃት ተገቢና መልካም አማካሪ ሊሆን አይችልም፡ ፖለቲካ ተገቢና ትክክለኛው የሕዝብ መሠረታዊ ተገቢ ሰብአዊነት ማእከል ያደርገ መብትና ግዴት ተኮር ጥያቄ በማስተናገድ ምላሽ የሚሰጥ እንጂ ለማንኛው ዓይነት ሕዝባዊ ጥያቄ የሚገዛ ማለት አይደለም እንዳሉ ከሎሶርቫቶረ ሮማኖ የየካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ሕትመት ለመረዳት ተችሏል።

15/02/2017 16:52