2017-02-13 16:52:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ በመዘጎርጂ ሰየሙ


በፖላንድ የዋርሳውና ፕራግ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሀንርይክ ሆሰር በመዘጎርጂ ልዩ የቅድስት መንበር ልኡክ እንዲሆን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሰየማቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

የዚህ ልዩ የቅድስት መንበር ልኡክ በመዘጎርጂ መሠረታዊ ሐዋርያዊ ሥልጣን የመዘጎርጂ ተጨባጩ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ሁነት ምን ተመስሎውን የሚያጤን በተለይ ደግሞ ከተለያዩ የዓለማችን ክልል የተወጣጡ በመዘጎርጂ መንፈሳዊ ንግደት የሚፈጽሙትን የሚሸኙበትና የሚያፈልጋቸው መንፈሳዊ እንክብካቤ ምን መሆኑ በጥልቀት በመረዳት የወደፊት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለመወጠን የሚል መሆኑ የጠቆመው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ስለዚህ የዚህ የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ ዋና ሓላፊነት የማያሻማ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ላይ ያነጣጠረ መሆኑ አስረግጦ ሲያመለክት፡ እኚህ የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ ብፅዕ አቡነ ሆሰር የዋርሶውና ፕራግ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳዊ ሐዋርያዊ ኃላታቸው እንደተጠበቀ የሚቀጥል ሲሆን፡ በመዘጎርጂ የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ ሐዋርያዊ ሓላፊነታቸው ምክንያት የሚያከናውነው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ዙሪያ ያነጣጠረ የሚያካሄዱት የግምገማው ሂደት እ.ኢ.አ. 2017 ዓ.ም. በጋ ወቅት ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑ ያመለክታል።

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዋና አስተዳዳሪ ግረግ ቡርከ የእኚህ ልዩ የቅድስት መንበር ልኡክ በመዘጎርጂ መላክ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ለመንፈሳዊ ነጋዲያን ያላቸው አሳቢነት የሚያረጋግጥ ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍረጃ እንዲሰጥ የሚያደርግ ጥልቅና ጥብቅ ምርመራ አድራጊ ሳይሆን በቀጥታ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚመለከት ሓዋርያዊ ኃላፊነት ነው፡ በመሆኑም በመዘጎርጂ ስለ የማርያማ ግልጸትና መገለጥ ስለ ሚባለው ጉዳይ ሓላፊነቱ የእምነት ጠመቅ ትምህርት ተከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በቀጥታ የሚመለከትና ኃላፊነቱም የተጠበቀ ሆኖ ልዩ ሓዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ሆሰር በዚህ ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ ጣልቃ እንደማገቡ የተሰጣቸው ልዩ ኃላፊነት በትክክል ያብራራል፡ ከአካባቢው ብፁዓን ጳጳሳት የመዘጎርጂ ቁምስና ኃላፊነቱ ከተሰጣቸው በክልሉ ከሚገኙት ከንኡሳን የፍራንቸስካውያን ወንድሞች ማኅበር አባላት ጋር እንዲሁም ከክልሉ ምእመናን ጋር ጥብቅ ግኑኝነት በማካሄድ የሚፈጽሙት አገግሎት መሆኑ ገልጠው። ከዚህ አፃርም ይላሉ ቡርከ የእኚህ የቅድስት መንበር ልዩ ልኡክ ኃላፊነት እንግዲህ የአንጻር ወይንም የተቃውሞ ምልክት ሳይሆን መፈሳውያን ነጋዲያን ላይ ያነጣጠረ መሆኑ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.