Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ሳይንስና ትምህርት

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ ምዕዳን ለይፋዊ ምሉእ የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ጉባኤ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ ምዕዳን ለይፋዊ ምሉእ የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ጉባኤ - ANSA

10/02/2017 16:34

ቅዱስ አባታችን የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በጠራው ምሉእ ይፋዊ ጉባኤ ተጋባእያን ተቀብለው ምዕዳን ሲለግሱ፥ አስቀድሜ እዚህ ከእናንተ ጋር እዚህ ስገናኝ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ላስደመጡት ለካቶሊክ ትምህርቱ ጉዳይ ተነክባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በመሆን የተሾሙ ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህ ቅዱስ ማኅበር ምሉእ ጠቅላይ ጉባኤ በመራት ላይ የሚገኙት ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ ቨርሳልዲና በዚህ በሳቸው ኅየንተነት በሚመራቅ ቅዱስ ማኅበር ውስጥ ለማገልገል የተሾሙት አዲስ አባላትና ተጋባእያን የ Fondazione Gravissimum educationis - የላቀ አስፍፈላጊ ሕንጸት ማኅበር አባላትን ሁሉ ምስጋናዮን አቀርባለሁ ብለው በቀጥታ የዚህ ይፋዊ ጉባኤ ዋና ዓላማም ባለፉት ሦስት ዓመት የዚህ የቅዱስ ማኅበር አገልግሎት ለመገምገምና ይኸንን መሰረት በማድረግ ቀጣይ የሥራ ሂደቱን መስርቆ ማስተዋወቅ የሚል መሆኑ ዘክረው፡ የሥነ ካቶሊክ ሕንጸት ጉዳይ የዚህ ማኅበር ኃላፊነት ነው በመሆኑም የሥነ ካቶሊክ ሕንጸት አስተማሪዎች የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ኃላፊዎች አስተዳዳሪዎች የመጀመሪያውና ቀጣዩን ሕንጸት ምን መሆን እንዳለበት የሚያስተዋውቅ ይኽ ትምህርት ማንም የማይነጥል ሁሉን የሚያቅፍ የሃይማኖት ትምህርት መሆኑ የሚያስተዋውቅ በተለያዩ አካባቢ የሚገኙት የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች የሚያበረታታና የሚደግፍ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኣና ፖቸ አስታወቁ።

የተካሄደው ጉባኤ በካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ሕንጸት ህዳሴ Costituzione apostolica Sapientia christiana – ሓዋርያዊ መተዳደሪያ ደንብ ክርስቲያናዊ ጥበብ በሚስጢረ ተክሊል ዙሪያ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ውሳኔ መሰረት ሕገ ቀኖና ዙሪያ የሚሰጠው ሕንጸት እንዲሁም በካቶሊክ መናብርተ ጥበብ የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማእከል ባደረጉ እርእስቶች መምከሩንም ቅዱስ አባታችን በማስታወስ፡ በዚያ የወንጌል ሓሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዘንድ መናብርተ ጥበብ የማስተዋልና የማስተንተን ብቃት ለአስፍሆተ ወንጌል አገልግሎት እድገት የሚሰጠው ድጋፍ ትልቅ ነው በማለት ያብራሩት ሃሳብ አስታውሰው፡  የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ባህል በወንጌል ይሰበክ ዘንድ በዚሁ ጉዳይ ያነጣጠረ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። ሰብኣዊነት የሚያነቃቃ ሕንጸት የሚቀርብበት ያንን ሰብአዊ በመሆን ሂደት የማይበጀው ሰብኣዊነትን የሚያደኸየውን እርሱም ግድየለሽነት ለእኔ ባይነት ባህል የመሳሰሉትን ሰውን ሰብኣዊ ከመሆኑ በታች የሚያወርድ ባህል በመተንተን የምሉእ ሰብአዊ ሕንጸት የሚያነቃቃ የሚደግፍ መሆኑ ገልጠው፡ ከየትና ወዴት የሚለው መሠረታዊ መሆናዊ ጥያቄ በማስደገፍ ምሉእ የሰብአዊ ሕንጸት የሚደግፍ ባህል የሚያቀርብና የሚያስፋፋ ሲሆን ይኽ ጥይቄ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች እንደየ ዓላማቸው የኅብረተሰብ ጥቅምና ሰው ተወልዶ የሚያድግበት ቤተሰብና ሕብረተሰብ ያለው እንጂ ብቸኛዊ ፍጥረት አለመሆኑ በማስተዋል በዚያ በመፈጠሩና በሚቀበለው ጥሪ ዘንድ ያለው ይዞት የሚመጣው መሆናዊ ላይ ያነጥጠረ ሕንጸት የሚያነቃቃ ቅዱስ ማኅበር ነው እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ፖቸ አያይዘው፥ መገናኘት ውይይት ሥነ ጥበባዊ ግኑኝነት የሚያነቃቃ የሐቅ ፍላጎት ላይ የጸና ዓላማ ያለው፡ ሁሉም የትምህርት ዘርፎች እውነትን የሚሹ መሆናቸው በማብራራትም  ሐቅ የሚፈለግበት የሕንጸት ስልት እርሱም የቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ አብነት በመከተል እውነትን መሻትን የሚነቃቃ ነው፡ ስለዚህ ክዚህ አኳያ ሲታይ ሕንጸት ተስፋን የሚዘራ ነው ብለው ምዕዳናቸው ሲያጠቃልሉ፥ ቅዱስ ማኅበሩንና አባላቱን አገልግሎቱና ዓላማውን ሁሉ ለጥበብ ማደሪያ ለሆነቸው ማርያም አወክፈው፡ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ እናንተ በጸሎቴ ህልዋን ናችሁ በማለት ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው አስታውቋል።   

10/02/2017 16:34