2017-02-08 16:59:00

በቅዱስ አባታችን የአቢይ ጾምት መልእክት ዙሪያ የተሰጠው ጋዜጣዊ አስተያየ


ለ 2017 ዓ.ም. ዓቢይ ጾም ምክንያት ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተለያየ ምክንያት የምንገናኘው ሕይወት ጸጋ ነው በሚል ሃሳብ ላይ አማክለው ባስተላለፉት መልእክት ዙሪያ የሰብኣዊ ምሉእ እድገት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ልዑክ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ጂቫኒ ፒየትሮ ዳል ቶሶና ከድኾች ጋር በቅርበት በሰብኣዊና መመንፈሳዊ ዘርፍ አገልግሎት ከሚያቀርበው የአዳዲስ አድስማሶች ማኅበረሰብ መስራች ኪያራ አሚራንተ እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው ጋዜጣዊ አስተያየት እንደሰጡበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ አስታውቋል።

ብፁዕ አቡነ ዳል ቶሶ ቅዱስ አባታችን በዚህ የ 2017 ዓ.ም. ባስተላለፉት የዓቢይ ጾም መልእክት እያንዳንዱ ድኻ ከክርስቶስ ጋር የሚያገናኝ ተገቢኅያው ሥፍራ ነው የሚል ድኻው ካልአ ክርስቶስ እንደሆነ በማብራራት በዕለታዊ ሕይወት የምትገናኘው ድኻ ልዩ ጸጋ ነው ይላሉ። ልክ በልጇ ኢየሱስ ስቃይ ልቧ በሰይፍ እንደ ተወጋች እናቱ የተሰማት ስቃይ የድኻው ስቃይ ለእኛ እንዲዚያ ሊሆን ይገባዋል። ብዙ ጥያቄዎችን ትደረድርም ዘንድ ግድ ይለሃል። ስለዚህ በዚህ ከክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ተገቢነት ያለው ኅያው ሥፍራ ብለው ቅዱስ አባታችን በገለጡት ድኻ ሰው  እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚል ምንም ነገር የማይሳነው መሆኑ የሚገለጥበት ቤተ ተአምር ነው። ፍቅር አሸናፊ ነው። ፍቅር ከሁሉም ነገር በላይ ብርቱ መሆኑ የሚያስገነዝብ መልእክት ነው እንዳሉ የገለጡት ማሶቲ አያይዘውም፥ እውነት ነው ድኻው ከክርስቶስ ጋር የሚያገናኝ የተገባ ኅያው ሥፍራ ነው እንላለን፡ የሚያሳዝነው ግን ይሕ እውነት ለብዎቻችን ዕለታዊ ተመክሮ ሳይሆን ይታለፋል። መጠለያ የሌላቸው ስደተኞች ጎዳና ተዳሪዎች በሽተኞች በሚዘነጋ ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው። የሚዘናጋው ዓለም ሳይሆን ሰው ነው፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ድኾች እንዳይረሱ አደራ ቢሉም ድኽነት የሚፈጥረው ምክንያት እንዲወገድ ጥሪ በማቅረብ ድኽነት ለመቅረፍ በንድፈ ሃሳብ ሳይሆን በተግባር መደረግ ያለበት ጉዳይ በተለያየ ወቅትም ይገልጣሉ። እየገለጡም ነው፡ በመልእክቱ እንዲስተዋል የሚሉት ነገርም ገዛ እራስን አለ መዝጋት የሚል ሃሳብ ሥር ካንተ የተለየውን መፍራት ባለንጀራህን መፍራት ሌላው እንደ ጠላት ተሻሚ አድርጎ በማሰብና በማራቅ አሊያም ለያይ ግንብ መገንባት የሚለውን ቍሳዊ ወይንም መንፈሳዊ እንዲሁም ቁሳዊና መንፈሳዊ ያጣመረም ለያይ ግን የሚመለከት ሲሆን ይኸንን ግንብ እናፍርስ ነው የሚሉት፡ ይኽ ጉዳይ ለወቅታዊው ዓለም ትልቅ ተጋርጦ ነው፡ ሌላውን እንዳይታይ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ምንም አይነት ግንብ የለም። እውነት መሆኑም ይኸው በዓለማችን እየታየ ያለው የስደተኞች ጸዓት አብነት ነው፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የሚሉት በርን ልብን ቤትን በተለይ ደግሞ አቢያተ ክርስቲያን ክፍት ማድረግ ነው። ገዛ እራስ ክፍት ማድረግ ብቻ ነው ሕይወት የሚሰጠው። መታፈንና መዘጋት ያሚያስከትለው ችግር ለመገመቱ አያዳግትም።

ሃብት የጌታን ቃል ላለማዳመጥ ሊገፋፋ ይችላል። ልብን ወደ መዝጋት ይሸኛል። ሆኖም የሚኖረው ከሌላው ጋር ስለ ምትገናኝ ነው፡ አለ ግኑኝነት መኖር ያለ አይመስለኝም። እኛ እኛ የምንሆነው እኔ እኔ የምሆነው ተገናኛ ባህርይ ስላለኝ ነው። ገዛ እራሴን ማወቅ የምችለው ከእኔ የተለየ ሰው መኖሩን ስረዳ ነው፡ ይኸንን ሃሳብ በቲዮሎጊያዊ በሌሎች በተለያዩ የጥናትና የምርምር ዘርፎችን በተለያየ መልኩ የሚነገም እውነት ነው፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የሚያሳስቡት ተጨባጭ ሃሳብ ልብንና በርን ክፍት ማድረግ ለያይ ግንብ ሳይሆን አገናኝ ድልድይ እንገንባ ነው የሚሉት ሲሉ፡ በመቀጠልም ጋዜጣዊ አስተያየት የሰጡት የአዲሶች አድማስ ማኅበረሰብ መሥራች ኪያራ አሚራንተ፥ ክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስና የወንጌሉ አንኳር መልእክቱን ይዘነጋል። ቃሉ እንደሚለውም፥ “እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ እኔ እንደወደድኋችሁ እናንተም እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደሆናችሁ በዚህ ሁሉ ያውቋችኋ” (ዮሐ. 13,34 ተመል.)፡ ፍቅር ተጨባጭ ነው ይኽ የጌታ ትእዛዝ ጦቢያ ማለት የማደረስ የማይጨበጥ ተስፋ አይደለም። ይኸንን የጌታ ቃል ምራቅን ዋጥ አድርጎ ካለ ምንም ማወላወል ለመኖር መሞከር ግድ ነው፡ እኔ እንዳፈቀርክኋችሁ እናንተም አፍቅሩኝ ብሎ ዝም ያለ ጌታ ሳይሆን። እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ ይላል። መለያችሁም ይኽ እርስ በርሳችሁ የምትኖሩት ፍቅር ይሁን ይላል፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ የዓቢይ ጾም መልክታቸውንም ይኸንን ፍቅር ነው በተለያየ መልኩ የሚያብራሩት ካሉ በኋላ የክርስቶስ ፍቅር ክርስቲያናዊ ማኅበራዊና ግላዊ አብዮት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.