2017-02-08 14:13:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው “እግዚኣብሔር የልጅነትና ምድርን የመንከባከብ መብትን ሰጥቶናል" ማለተቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 30/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባስሙት ስብከት እንደ ገለጹት “እግዚኣብሔር ሰውን በአማሳሉ ፍጥሮታል፣ የምድርም ጌታ እንዲሆን አድርጎታል ሴትንም ፈጥሮ ይወዳት ዘንድ ከጎኑ አስቀምጡዋታል” ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታችው በእለቱ ያሰሙት ስብከት ከላይ በተጠቀሱት እና እግዚኣብሔር በፍጥረት ወቅት ለሰው ልጆች የሰጣቸውን ሦስት ስጦታዎች ላይ ያጠነጠነ ስብከት እንደ ነበረም ልመረዳት ተችሉዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው የስብከታቸው መነሻ ያደረጉት በእለቱ በተነበበው “አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት!” በሚለው በመዝሙረ ዳዊት በምዕራፍ 8, 4 ላይ በተጠቀሰውና በእለቱ በተነበበው ከኦሪት ዘፍጥረት ከተወሰደው ሰለ የወንድና የሴት አፈጣጠር በሚገልጸው የመጀመሪያው ምንባብ ላይ  የተመረኮዘ እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ዓለምን በፈጠረበት ወቅት ለሰው ልጆች 3 ታላላቅ ስጦታዎችን እንደሰጣቸው የጠቀሱ ሲሆን “በመጀመሪያ በራሱ መልክና አምሳያ በመፍጠር የእርሱ ልጆች እንድንሆን በማድረግ የእርሱ የዘር ግድ ተካፋዮች እንድንሆን አደረገን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ ሰው ልጅ በሚወልድበት ወቅት መልሶ እንዳልተወለደ አድርጎ ሊወስደው አይችልም፣ ምክንያቱም ልጁ አንዴ ተወልዱዋል ተጨባጭ በሆነ መልኩም በአካል እየኖረ በመሆኑ የተነሳ ይህንን ሀቅ መካድ ስለ ማይችል ነው” ብለዋል።

ምንም እንኳን ይህ የተወለደ ልጅ በባሕሪው አባቱን የማይመስል ቢሆንም እንኳ የአባቱ የዘር ግንድ በውስጡ ስለ ሚገኝ አባት ልጁን በፍጹም መካድ አይችልም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በእርግጥ ልጁ መልካም ልጅ ከሆነ አባቱ በልጁ እንዲህ በማለት ይኩራራበታል ‘ተመልከቱ እስቲ እንዴት ያለ ጥሩ ልጅ እንደ ሆነ’ በማለት ጭምር እንደ ሚያሞካሸው ገልጸዋል።

ነገር ግን ልጁ በተቃራኒው  መልካም የሚባል ዓይነት ልጅ ካልሆነ ግን አባቱ በታላቅ ትዕግስት ልጁ መልካም እስከ ሚሆንለት ድረስ ይጠባበቃል ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ረገድ ኢየሱስ በወንጌል አባት ልጁን እንዴት በፍቅር እንደ ሚጠባበቅ አስረድቶናል ብለዋል። በተመሳስይ መልኩም እግዚኣብሔር የልጅነት መብትን ስጥቶናል እኛም ደግሞ የመልካም ልጅ ባሕሪን በመላበስ መኖር ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ የእግዚኣብሔር ልጆች በመሆናችን የተነሳ የአማልእክት ዓይነት ሰዎች ነን' ብለዋል።

እግዚኣብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸው ሁለተኛው ስጦታ የመፍጠር ችሎታ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደ ተጠቀሰው እግዚኣብሔር የሰው ልጅ ምድርን እየተነከባከበና እያለማ ይጠቀምበት ዘንድ በአደራ እንደ ሰጠውም ገልጸዋል። ነገር ግን እግዚኣብሔር የሰው ልጆች የንጉሣዊያንን ባሕሪ እንዲላበሱ አድርጎ ነበረ የፈጠራቸው ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም ያደረገበት ምክንያት እግዚኣብሔር ማንም ሰው ባሪያ እንዲሆን ስለ ማይፈልግ እንደ ሆነም ገልጸዋል።

“እግዚኣብሔር ዓለምን እንደ ፈጠረ ሁሉ ለእኛም ታላቅ የሆነ ሥራን ሰጥቶናል ይህም እርሱ የፈጠረውን ምድር እንድናለማ ነው እንጅ እንድናወድም አይደለም” ያሉት ቅዱስነታቸው “ምድራችንን ልንከባከባትና በእዚህ መልኩ ወደ ፊት እንድትጓዝ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል። “አንድ አንድ ጊዜ እግዚኣብሔር ለእኝ ገንዘብ ለምንድነው ያለሰጠን ብዬ ሳስብ ይገርመኛል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁሉንም ነገር እንድንጠቀምበት ሰጥቶናል ነገር ግን ጥሬ ገነዘብ አልሰጠንም” ካሉ ቡኋላ አንድ አንድ ጊዜ አያቶቻችን “ሰይጣን የሚገባው በኪሳችን በኩል ነው” የሚሉት ነገር ትዝ በሚለኝ ወቅት ሁሉ ለእዚህ ነው ለካ እግዚኣብሔር ለሰው ፍጥረትን ሁሉ ይንከባከብና የጠበቀው ዘንድ ያለ ምንም ጥሬ ገነዘብ በስጦታነት የሰው ብለዋል።

እግዚኣብሔር በፍጥረት ወቅት የሰጠን ሦስተኛው ስጦታ ፍቅር ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ፍቅር በወንድ እና በሴት መካከል በሚፈጠረው ግንኙነት እንዲጀምር አድርጎ እንደ ፈጠረም ጠቅሰዋል።

“ወንድ እና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው፣ የሰው ልጅ ብቻውን ይሆን ዘንድ የተገባ አይደለም፣ ለእዚህም ነው አጋር የምትሆነው ሴት የተፈጠረችለት” ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር በፍቅር ነው ለሰው ልጆች ፍቅርን የሚሰጠው ካሉ ቡኋላ ይህም የፍቅር ግንኙነት በቀዳሚነት ሊጀመር የሚገባው በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ገለጹት “እግዚኣብሔር አባታችን ስለ ሰጠን የልጅነት መንፈስ፣ ምድርን በኋላፊነት እንድንከባከብ ስለተሰጠን ስጦታ፣ በመጨረሻም ስለ ሰጠን የፍቅር ስጦታ ስለ እነዚህ ሦስት ስጦታዎች ልናመሰግነው ይገባል” ካሉ ቡኋላ እነዚህን የተሰጡንን የልጅነት ባሕሪን በመጠቀም ውጤታማ ተግባሮችን እንድናከናውንና ይህም ስጦታ በተግባራችን ወደ ፊት እንዲቀጥል በማድረግ በፍቅር ጸጋ ተሞልተን በየቀኑ እርስ በእርሳችን መዋደድ እንድንችል ይረዳን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ለ

ኣለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.