2017-02-04 11:22:00

ቅዱስነታቸው "ወንድ እና ሴት መናኒያን ከኢየሱስ ጋር ራሳቸውን በሕዝቡ መኋከል ለማኖር ነው የተጠሩት” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በጥር 26/2009 ዓ.ም. የተከበረውንና በሙሴ ሕግ መሠረት የመንፃት ሥርዓት የሚፈጸምበት እለት በደረሰ ጊዜ እናቱ ማሪያም እና ዮሴፍ ሕፃኑን ኢየሱስን ለእግዚኣብሔር ለማቅረብ ወደ ኢየስሩሳሌም ይዘውት የሄዱበት ቀን የሚዘከርበት በዓልን ምክንያት በማድረግ እና በእለቱም በተመሳሳይ መልኩም የተከበረውን በምንኩስና ሕይወት የሚኖሩ ካህናት፣ ደናግላን እና ገዳማዊያን በተጨማሪም በሐዋሪያዊ ተልዕኮ የተሰማሩ ሰዎች የሚታሰቡበት በዓልን አስመልክተው ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱም ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን የተዘከረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም በዓል በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር አገልግሎት ለየት ባለ ሁኔታ በንጽሕና፣ በድኽነት እና በታዛዥነት ለመኖር ቃል በመግባት ሕይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ሰዎች ሁሉ በሕይወታቸው ጽናት ይኖራቸው ዘንድ እግዚኣብሔር እንዲረዳቸው ጸሎት መደረጉ ታውቁዋል። ይህ ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1997 በጊዜው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩ በዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ አነሳሽነት መከበር እንደ ጀመረ የታወቀ ሲሆን በጥር 26/2009 ዓ.ም. የተከበረው 21ኛው የመናኒያን ቀነ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን ስርዓተ አምልኮ የሚከበረው በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻት ስርዓት በደረሰ ጊዜ ሕፃኑ ኢየሱስን እናቱ ማሪያም እና ዮሴፍ በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት ለእግዚኣብሔር ለማቅረብ ወደ ኢየስሩሳሌም ይዘውት የሄዱበት እለት ጋር መሳ ለመሳ የሚከበር በዓል መሆኑም የተገለጸ ሲሆን በተመሳሳይም የሻማ መባረክ ስነ-ስርዓት ከተፈጸመ ቡኋላ በሁደት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት የመስዋዕተ ቅዳሴ የሚደረግበት በዓለ ጭምር መሆኑም ይታወቃል።

በስርዓተ አምልኮ መግቢያው ላይ የሻማ መባረክ ስነ-ስርዓት የሚያመልክተው ኢየሱስ የዓለም ብርሃን መሆኑን በማሳያነት ለማቅረብ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም ወንድ እና ሴት መናኒያን ይህንን የክርስቶስን ብርሃን በዓለም ውስጥ ለማሰራጨት መጠራታቸውን ለመዘከር እንደ ሆነም ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ በእሳቸው መሪነት ተካሂዶ በነበረው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ሕይወቱን ለእግዚኣብሔር የሰጠ ጻዲቅ ሰው የነበረው እንዲሁም የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ የነበረ፣ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ያደረ፣ ስምዖን የሚባለው ሰው እና ከአሴር ነገድ የሆነችው የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ሕፃኑን ኢየሱስን ባዩት ጊዜ ባቀረቡት “የተስፋ መዝሙር” ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ታውቁዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በእለቱ ያሰሙትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የኢየሱስ ወላጆች በሕግ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዱት ወቅት ስምዖን “በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ” (ሉቃስ 2.22-40) ሕፃኑን ኢየሱስን አቅፎ “ማዳንህን በዐይኖቼ አይቻለሁ እርሱም በሕዝቦች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኽው፣ እርሱ ለአረማዊያን እውነትን የሚገልጥ ብርሃን ይሆናል። ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው!” በማለት እግዚኣብሔርን አመስግኑዋል። ስምዖን ኢየሱስን በዐይኑ ብቻ ሳይሆን ያየው ለብዙ ጊዜ በተስፋ ሲጠባበቅ የነበረውን ሕፃኑን ኢየሱስ በእጆቹ አቅፎ ይዞም ነበር። ይህም በታላቅ ደስታ እንዲሞላ አድርጎት ነበር። እግዚኣብሔር በሕዝቦቹ መኋል ለማደር በመምጣቱ የተነሳ ልቡ በደስታ ተሞልቶ ነበር የእርሱም በሥጋ በሕዝቦቹ መኋል መገኘቱም ተሰምቶት ነበር።

የዛሬ ስርዓተ አምልኮ እንደ ሚያስረዳን ኢየሱስ ከተወለደ ከአርባ ቀናት ቡኋላ “በሙሴ ሕግ የተፃፈውን ለመፈጸም ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተ መቅደስ የተወሰደው በእርግጠኛነት ተወዳጅ የሆኑ ሕዝቦቹን ለመገናኘት  ፈልጎ ነው። ይህም ግንኙነት እግዚኣብሔር ከሕዝቡ ጋር በመገናኘቱ የተነሳ የመጣውን ደስታ እና ተስፋን የሚያድስ ነው።

ስምዖን ያቀረበው የውዳሴ መዝሙር አማኞች ሁሉ በሕይወታቸው ማብቂያ ግዜያት ሁሉ “በእውነት በእግዚኣብሔር ተስፋ ማድረግ መቼም ቢሆን የማያሳፍር መሆኑን” እንዲረዱት ያደርጋል። እግዚኣብሔር መቼም ቢሆን አያታልለንም። ስሞዖን እና ሐና በስተርጅናቸው ውጤታማ ሆኑ ውጤታማ መሆናቸውንም በዘመሩት የደስታ መዝሙር አረጋግጠዋል። ጌታ የገባውን ቃል የሚጠብቅ በመሆኑ ሕይወታችንን በተስፋ መኖር ጠቃሚ ነው። ኢየሱስ ራሱ ከጊዜ በኋላ በናዝሬት ምኩራብ ውስጥ ይህን ተስፋ ያብራራል:  የታመሙትን፣ እስረኞችን፣ ብቻቸውን የቀሩትን አረጋውያን፣ ኃጢአተኞችን እና ድኸ የሆኑ ሆኑ ሰዎች ሁሉ ይህን ተመሳሳይ የተስፋ መዝሙር እንዲዘምሩ ይጋብዛል። ኢየሱስ ከእኛ ጋር ነው፣ ኢየሱስ ከእነሩስ ጋርም ነው (ሉቃስ 4.18-19)።

እኛ ይህንን የተስፋ መዝሙር ከአረጋዊያን ወርሰናል። የእዚህም ሂደት አካል እንድንሆንም አድርገውናል። በፊቶቻቸው ላይ፣ በሕይወታቸው ውስጥ፣ ዕለታዊ በሆነ መሥዋዕትነት ሳይቀር ይህን ምስጋና ከነርሱ ጋር እንዴት እንደ ነበረ ማየት ይቻላል። እኛ የቀድሞ አባቶቻችን፣ ወንድሞችና እህቶች ያላፈሩበት ሕልም ወራሶች ነን። እኛም ከእኛ በፊት ያለፉት ሰዎች ቃል ወራሾች ነን። እኛንም እንደ እነርሱ “እግዚአብሔር አያታልለንም። በእርሱ ተስፋ ማድረግ አያሳፍርም” ብለን ልንዘምር ይገባል። አምላክ ሰዎችን ለማግኘት ይመጣል። እኛም ከኢዩኤል ትንቢት በማንሳት እና ይህንን ትንቢት የራሳችን በማድረግ “ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ፣ ወንዶች እና ሴቶች ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፣ ትንቢት ይናገራሉ፣ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ” ብለን ልንዘምር ይገባል (ት. ኢዩኤል 2,28)።

እስቲ ወደ ዛሬው የወንጌል ክፍል በመመለስ አንድ ጊዜ ይህ ሁኔታ በማሰላሰል እንመልከት። በእርግጥም የስምዖንና የሐና መዝሙር በራስ ወዳድነት ወይም የግል ሁኔታቼው ትንተና እና የግምገማ ፍሬ አልነበረም። እነርሱ በራሳቸው ሕይወት ውስጥ መጥፎ ነግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት አድሮበባችው ሳይሆን በውስጣቸው የነበረው ስሜት ወደ ውጭ ገንፍሎ በመውጣቱ የተነሳ የዘመሩት መዝሙር ነው። የእነርሱ መዝሙር ከተስፋ የተወለደ መዝሙር ነው። ይህም ተስፋ እስከ እርጅናቸው ወቅት ድረስ አብሮዋቸው የዘለቀ ተስፋ ነው። የእዚህ ተስፋቸው ሽልማት ኢየሱስን መገናኘት ነበረ። ማሪያም ስምዖን ሕፃኑን ኢየሱስን እንድያቅፍ በፈቀደችበት ወቅት አዛውንቱ ስምዖን ሕልሙን መዘመር ጀመረ። እርሷ ኢየሱስን በሕዝቡ ማኋል በምታኖርባቸው ጊዜያት ሁሉ ሕዝቡ ደስታን ይጎናጸፋል። በእዚህም መንገድ ብቻ ነው እኛ ደስታን እና ተስፋን መጎናጸፍ የምንችለው፣ እየሱስ በሚገባው ቦታ በሕዝቡ መኋል ሲኖር ብቻ ነው እኛ የመኖር ጉጉት ልያድርብን የሚችለው።

ኢየሱስን በሕዝቡ መኋል ማኖር ማለት እግዚኣብሔር እንዴት በከተሞቻችን መንግድ ላይ እና በጎሬቤቶቻችን መካከል እንዴት እየተመላለሰ እንድሚገኝ የሚያሰላስል ልብ ማለት ነው። ኢየሱስን በሕዝቡ መካከል ማኖር ማለት የወንድሞቻችንና የእቶቻችንን መስቀል መሸከም ማለት ነው። ኢየሱስን በሕዝቡ ማካከል ማኖር ማለት ፈውስን በመሻት እያለቀሰ ለሚገኘው የዓለማችን ቁስል መንካት ማለት ነው። ይህም የኢየሱስን ቁስል እንደ መንካት ይቆጠራል።

ራሳችንን ከኢየሱስ ጋር  በሕዝቡ መካከል እናኑር! ራሳችንን እንደ የሐይማኖት ጉዳዮች “ተሟጋች” አድርገን ሳይሆን መቁጠር የሚገባን ነገር ግን በቀጣይነት ይቅርታ የሚደረግልን፣ በጥምቀት የተዋጀን፣ ይህንንም ቅዱስ ቅባት እና የእግዚኣብሔር መጽናናት ከሁሉም ጋር መካፈል ይኖርብናል። ይህንንም መንገድ የምንከተል ከሆንን በጣም ጥሩ ነው በጣም ነፃ እና በተስፋ የተሞላን እንሆናለን። ከራሳችን በመውጣት ሌሎችን መቀላቀል ለራሳችን ብቻ መልካም እንደ ማድረግ የሚቆተር ሳይሆን ሕይወታችንን የሚቀይር እና የተስፋ መዝሙር እድንዘምር ይረድናል።

ሕዝቦቹን ለመገናኘት ከሚሄደው  ከኢየሱስ ጋር እንቀናጅ። ወደ ፊት እንሂድ፣ ወደ ፊት ስንሄድ በማጉረምረም ወይም ደግሞ የአባቶቻቸውን ሕልም ሳይከተሉ ቀርተው በመጨነቅ ላይ እንዳሉ ሰዎች ሳይሆን ነገር ግን በግልጽነት እና በውዳሴ መዝሙ ሊሆን ይገባል። በፍርሃት ሳይሆን ነገር ግን በትዕግስት እና በመንፈስ ቅዱስ፣ የሕልማችን ባሌበት በሆነው በጌታ በመታመን መኖር ይገባል።

ክቡራን እና ክቡራት አንባቢዮቻችን ቀደም ሲል ስትከታተሉት የቆያችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 21ኛው ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን በተከበረበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ነበር። ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ “ወንድ እና ሴት መናኒያን ከኢየሱስ ጋር ራሳቸውን በሕዝቡ መኋከል ለማኖር ነው የተጠሩት” ማለታቸውም ታውቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.