2017-02-03 16:54:00

ብፁዕ ካርዲናል ርይልኰ አዲስ የጳጳሳዊ ቅድስተ ማርያም ታላቅ ባዚሊካ ሊቀ ካህን ሆነው ተሾሙ


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለረዥም ዓመታት የዚያ የዓለማውያን ጉዳይ ተንከባካቢ በሚል ስያሜ ይጠራ የነበረው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉት 71 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ የቅድስተ ማርያም አቢይ ባዚሊካ ሊቀ ካህን እንዲሆኑ መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን ይኸው ብፁዕ ካዲናል ርይልኮ የተሰጣቸው አዲስ ሐዋርያዊ ኃላፊነት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ያቀረቡበት ቀን እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ባከበረችበት ዕለት በባዚሊካው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ጀምሯል።

ብፁዕነታቸው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁ ከቫቲካን ራዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቀደም በማድረግ ለዚህ አዲስ ሐዋርያዊ ኃላፊነት ለሾሟቸው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን አመስግነው፡ በምዕራቡ ዓለም የመጀመሪያ ለቅድስት ማርያም የተወከፈው የዚህ አቢይ ቅድስት ማርያም ባዚሊካ ተብሎ ለተሰየመው ጥንታዊው እ.ኤ.አ. በ431 ዓ.ም. በኤፈሶን ጉባኤ የማርያም መለኰታዊ እናትነት የሚል የማይሻር ውሳኔ ጠመቅ አንቀጸ ትምህርት እወጃ ከሰጠበት ልክ ካንድ ዓመት በኋላ እ.ኤ.አ. በ 432 ዓ.ም. የተገነባና እያለም በተለያዩ ዓመታት እየታደሰና እየተሻሻለ ይኸው አሁን ያለበት ቅርጽ ይዞ ይገኛል። በባዚሊካውም የሮማ ህዝብ ድህነት በሚል ስያሜ የሚታወቀው የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል ያለበት መሆኑ አሳታውሰው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ወደ ባዚሊካው በመሄድ ጸሎት አሳርገዋል። ከዚያም ወደ ተለያዩ አገሮችና በአገር ውስጥ በጠቅላላለ ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ ሐዋርያዊ ጉዞ ከመነሳታቸው በፊትና መልስም በኋላ ወደ ባዚሊካው በመሄድ ጸሎት ያሳርጋሉ። የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ባዚሊካውን ለ 40 ጊዚያት እንደጎበኙትም ገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ርይልኮ የፖላንድ ተወላጅ መሆናቸውም ገልጠው በአገራቸው ያ በቅድስት ማርያም ታላቅ ባዚሊካ የማርያም ቅዱስ ምስል እንዳለና 37 በእርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ዘውደ የቅዱስ ጲጥሮስ ተከይነት ምልክት የተኖረባቸው በጠቅላላ 350 የቅዱስ ምስሉ ቅጆች እንዳሉና በስማሟ የሚጠሩም ከ 30 በላይ የሚገመቱ አቢያተ ክርስቲያን እንዳሉም አስታውሰው፡ የፖላንድ ሕዝብ ለማርያም ያለው አክብሮት የሚገልጥበትና በእርሷ አማላጅነትም የሚጸልይበት ቅዱስ ምስል ነው ስለዚህ የዚህ አቢይ ቅድስተ ማርያም ባዚሊካ ሊቀ ካህን ሆነው በመሾማቸው በእውነቱ ከአገራቸው ከሳቸው ታሪክ ጋር ጭምር የሚያገናኛቸው በመሆኑ ቁዱስ አባታችንን አመሰግናለሁ ብሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.