2017-02-03 16:45:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ውፉይ ሕይወት መናንያን እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚሰጠው ዓቢይ ጸጋ ነው


በላቲን ሥርዓት ባሕረ ሐሳብ መሠረት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ማርያምና ዮሴፍ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቀደስ ያቀረቡበት ዕለት እክብራ ስትውል። ከዚህ ዓቢይ በዓል ጋር በማያያዝም እንደወትሮው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ዓለም አቀፍ የውፉይ (የምንኵስና) ሕይወት ቀን አስባ ውላለች። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም ይኸንን አቢይ በዓል ምክንያ በማድረግ በዚያኑ ዕለት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሮማ ሰዓት አቆጣጠ አሰዓት በኋላ ልክ አምስት ሰዓት ተኵል ገዳማውያን መነኮስና መነኰሳት በጠቅላላ ከተለያዩ ማኅበራት የተወጣጡ የውፉይ ሕይወት ማኅበር አባላት በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።

ቅዳሴው ከማረጉ ቀደም በማድረግም የውፉይ ሕይወት ምልክት የሆነውን የሻማ ብርኃን በመያዝ የውፉይ ሕይወት አባላት መንፈሳዊ ኡደት ማከናወናቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አያይዘው፥ በዚያኑ ዕለት ቅዱስ አባታችን ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ በኩል ባለው አድራሻቸው አማካኝነትም፥ “የምንኩስና ሕይወት፥ የእግዚአብሔር አቢይ ጸጋ ነው፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ እንዲሁም ለሕዝበ እግዚአብሔር የሰጠው ጸጋ ነው።” የሚል የምንኩስና ሕይወት ከእግዚአብሔር የሚለገስ ጸጋ መሆኑ የሚያስገነዝብ መልእክት ማስተላለፋቸው አስታውቋል።

ቅዱስነታቸው ወንጌላውያን ምዕዳኖችን በመቀበል ሕይወታቸው በለጋስነት የመናኝ ሕይወት በመምረጥ ለእግዚአብሔር ሕይወታቸው ስለ ሰጡት እንዲጸለይና፡ በዚህ በአሁኑ ወቅት የጥሪ ቀውስ በሚታይበት ሰዓት የጥሪ ቀውስ ብቻ ሳይሆን በውፉይ ሕይወት አማካኝነት ሕይወታቸው ለእግዚአብሔር የሰጡ  ካህናት ደናግል ወንድሞች ገዳማውያን ይኸንን የውፉይ ሕይወት ለቀው በሚወጡት ጭምር የሚታይ የጥሪ ቀውስ ያካተተ መሆኑ ገልጠው ስለ መናንያን ሕይወት ሁሉም እንዲጸልይ አደራ ማለታቸውን ይጠቁማሉ።

በዚህ አጋጣሚም ገዳማውያን ያልሆኑት ማኅበረሰብ ውፉያን የመናንያን ውፉያን ማኅበራትና የመናንያን ሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካዲናል ዥዋው ብራዝ ደ አቪዝ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስ አባታችን በዚህ ጌታችን ኢየሱስ በማርያምና በዮሴፍ ወደ ቤተ መቀደስ የቀረበበት በዓል በሚውልበት ቀን ምክንያት እና ከዚሁ ጋር በማያያዝም ቤተ ክርስቲያን የምታከብረው ዓለም አቀፍ የመናንያን ቀን ምክንያት ማርያም እና ዮሴፍ ጌታችን እየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ያቀረቡበት ዕለት፡ ማርያም ልጅዋን ሕፃኑን ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ስታቀርበው ኢየሱስ እርሷን ወደ ቤተ መቀደስ አቅፎ እንዳቀረባት የሚገልጥ ከመሆኑም ባሻገር የእግዚአብሔር ፈቃድ ማርያምንና ዮሴፍን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ያቀርቡ ዘንድ እንደመራቸው የሚያረጋግጥ ነው። በእድሜ የገፋው ስምዖንና ሐናም በደስታ ቅድስት ቤተሰብን በመቀበል ስምዖን ኢየሱስን በእቅፉ ያኖራል በሌላው አገላለጥም ኢየሱስ ስምዖን አዛውንቱን በእቅፉ እንዳኖረ የሚያረጋግጥ ሁነት ነው፡ ከጌታ ጋር መገናኘት የግኑኝነት ምስጢር መሆኑም በስፋት አብራተዉታል። ኢየሱስ እራሱን ዝቅ በማድረግ ሰው ሆኖ ሕፃን ሆኖ ነው የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ እራሱን ዝቅ አድርጐ መጣ። ከሰው ልጅ ጋር ለመገናኘት። የሰው ልጅ በተራውም ስለ ፍቅር ከሌላው ከወንድምና እህት ጋር ለመገናኘት እራሱን ዝቅ አድርጎ መምጣት ይኖርበታል። ውፉይ ሕይወት መናንያን ሁሉ እግዚአብሔር የጠራቸውም ይኸንን የሚመሰክሩ ናቸው። እግዚአብሔር የጠራቸው በፍቅር ወደ ቤተ መቀድስ የሚቀርቡ ናቸው። ይኽ ደግሞ ገዛ እራሳቸውን ቁርባን ያደርጋሉ ማለትም እራስቸውን ለየት በማድረግ ላንተ ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን ብለው ውፉያን ይሆናሉ። ይኸንን ለርእሱ ገዛ ራሳቸውን ቁርባን አድርገው የሚያቀርቡበት ሂደትም ፍቅር ሲሆን። ፍቅር ለእግዚአብሔር ፍቅር ለወንድምና እህት የሚል ነው፡ ስለ ፍቅር የሚኖር ሕይወት መሆኑ ቤተ ክርስቲያን የመናንያን ሕይወት ትርጉም መጽሓፍ ቅዱሳዊ ቲዮሎጊያዊ የቤተ ክርስቲያን ትውፊትና የአበው ትምህርት መሠረት በማድረግ የምታብራራው ትምህርት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.