2017-02-02 11:45:00

ቅዱስነታቸው በጥር 24/2009 ዓ.ም. ያስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ!


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በታላንትና እለት ማለትም በጥር 24/2009 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ ማድረጋቸው ይታወቃል። የእዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዜት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥  ሁላችሁም የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤ እንግዲያውስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤  እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።’ (1ተሰ 5.4-10)

ውድ ወንድሞችና እህቶች! እንደምን አረፈዳችሁ!

ባለፉት አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርታችን ከብሉይ ኪዳን በመጥቀስ ስለ ተስፋ ተናግረን ነበር፣ ዛሬ ደግሞ ይህ መለኮታዊ ኋይል የሚሰጠንን ልዩ ብርሃን በአዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመገናኘት በትንሣኤው ብርሃን የሚበራውን የክርስትያን ተስፋ እንመለከታለን፣ እኛ ክርስትያኖች ሁላችን የተስፋ ሰዎች ነን።

በትምህርታችን መግቢያ ሲነበብ የሰማነው አንደኛ የጳውሎስ መልእክት ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ከመጀመርያ ጀምሮ የሚያብራራው ይህንን ነጥብ ሲሆን ገና በመወለድ ላይ ለነበረችው የተሰሎንቄ ማሕበረ ክርስትያን ምንም እንኳ በችግርና በታላቅ ፈተና ብትገኝም በጽኑ እምነት ላይ የተመሰረተች ስለነበር የጌታ ኢየሱስ ትንሣኤን በታላቅ ደስታ ታከብራለች፣ ሐዋርያው ጳውሎስም በዚህ እጅግ ደስ ይለዋል በጌታ ትንሳኤ እንደገና ዳግም ለተወለዱትም የብርሃን ልጆች የቀን ልጆች ሲል ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስላላቸው አንድነት ይናገራል።

ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህንን መልእክት ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ሲጽፍ ከጌታ ትንሣኤ ቡኋላ ከጥቂት ዓመታት ሲሆን ማሕበረ ክርስትያኑም ከጥቂት ጊዜያት በፊት የተቋቋመ ነበረ።  ጌታ ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ሁም ያምኑ ነበር፣ ነገር ግን ስለ ገዛ ራሳቸው ሲያስቡ ሞተው የሚቀሩ እንጂ እንደ ጌታ ኢየሱስ ከሞት የሚነሱ አይመስላቸውም ነበር፣ እንዳይረድቱም ያስቸግራቸው ነበር፣ ሁሌ ከሞት ጋር ስንጋፈጥ ወይንም የምንወዳቸው ሰዎች የሞቱ እንደሆነ እምነታችን በታላቅ ፈተና ትፈተናለች፣ በአእምሮአችን የተለያዩ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች ይመጣእውነት ከሞት በኋላ ሕይወት ይኖራልን? በሞት የተለዩኝን ወዳጆቼ እንደገና አገኛቸው ይሆን?የሚሉ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች አሉ፣ ስለ እዚህ እኛም ወደ እምነታችን መለስ ብለን እግዚኣብሔር በጌታ ኢየሱስ ያደረገልንን ማሰላሰል ያስፈልጋል። ሞታችን ምን ትርጉም አለው፣ እውነት ነው ሁላችን ሞት ያስፈራናል። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ የጠቀስኩት ጥርጣሬ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ ይመልስልናል፣ አንዴ አንድ ጅግና  አዛውንትእኔ ሞት አያስፈራኝም ሲመጣ ግን ላየው ዝግጁ አይደለሁኝምያለኝ ትዝ ይለኛል፣

እንዲህ ባሉ ፍራቻዎችና ጥርጣሬዎች ቅዱስ ጳውሎስየመዳን ተስፋንእንደ ራስ ቊር እንድንለብስ ይጠይቀናል፣ ይህን ተስፋ እንደ መልካም ምኞት ልንገምተው አይገባም፣ ለምሳሌምነገ መልካም ቀን እንደሚሆን ባለተስፋ ነኝ!ብለን ምኞታችንን እንገልጻለን። ስለ ሆነም ነገ የባሰ ቀን ሊሆን ይችላል፣ የክርስትያን ተስፋ ግን እንዲህ አይደለም፣ እንደተፈጸመ አደርጎ በእርግጠኝነት መጠባበቅ ነው፣ በቦታው ክፍት ቦታ አለ! እኔም እዛ እንደምደርስ ባለተስፋ ነኝ፣ እቦታው ለመድረስ ምን ማድረግ አለብኝ ያልን እንደሆነ በዛኛው አቅጣጫ በቀጥታ መጓዝ ነው፣ እንዲህ ያደረጉ እንደሆነ በእርግጥ ወደ በሩ ይደርሳሉ፣ የክርስትያን ተስፋ እንደዛ ነው፣ ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዞ በቀጥታ ወደ በሩ በእርግጠኝነት መጓዝ ነው፣ ይህ ለእያንዳንዳችን እንደሚፈጸም በማመን የምናደርገው ጉዞ ክርስትያናዊ ተስፋ ይባላል፣ ስለዚህ የእኛና የምንወዳቸው ሰዎች ሁሉ ከሞት መነሳት ይሆን ይሆናል ብሎ የሚታለፍ ሳይሆን በእርግጥ የሚሆን ጉዳይ ነው፣ ተስፋ ማድረግ ስንል በመጠባበቅ መኖርን መማር ነው፣ ለምሳሌ አንዲት ሴት እርጉዝ መሆንዋን ባወቀች ጊዜ በእያንዳንዱ ቀን የሚወለደውን ሕጻን ለማየት በጉጉት እየተጠባበቀች ትኖራለች፣ እኛም እንደዛው ጌታን ለማግኘትና ከእርሱ ጋር ለመኖር መጠባበቅን በመማር መኖር አለብን፣ ተስፋ ማድረግ ትሁትና ድኸ ልብን እንደቅድመ ሁኔታ ይጠይቃል ድኸ ብቻ ነው መጠባበቅ የሚያውቅና መጠባበቅን የሚችልበት።

ቅዱስ ጳውሎስ አያይዞኢየሱስ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተሲል የመጽናናትና የሰላም ቃላት ይጽፍልናል፣ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ እጅግ የምናፈቅራቸው ቤተ ዘመዶቻችንም በዚህ ተስፋ ስላለፉ ከጌታ ጋር ሙሉ መተባበር እንዲኖራቸው በጸሎት እንድናስባቸው እንጠየቃለን፣ ሌላው እጅግ አጽናኝ የሆነ የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ደግሞእንዲህ ባለ ሁኔታ ዘወትር ከጌታ እንኖራለን’ (1ተሰ 4.17) በማለት የተስፋችን እርግጠኝነት ይሰጠናል፣ ይህ ዓይነት እርግጠኝነት በኦሪት ጻዲቁ ኢዮብእኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንድቆም፥  ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል’ (ኢዮ 19.25-27) በማለት ይገልጠዋል፣በማለት ትምህርታቸውን ለማገባደድ ሲሉ በአዳራሹ ወደ ነበረው ሕዝብ መለስ በማለት እስቲ ልጠይቃችሁእንዲህ ባለ ሁኔታም ዘወትር በጌታ እንኖራለንየሚለውን ታምናልችሁ ወይ? ብለው ሲጠይቁ ሕዝቡም በህብረትአዎን” ሲሉ ከመለሱ በኋላ ይሁን እስቲ ከሞላ ጐደል ብለው ኋይል እንዲኖራችሁ ሶስቴ አብረን እንድገመው ‘ ‘እንዲህ ባለ ሁኔታም ዘወትር ከጌታ እንኖራለንሲሉ ሶስቴ ከደጋገሙ በኋላ መስግነው ትምህርታቸውን ደምድመዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.