2017-01-20 16:39:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የክርስትና ሕይወት ዕለታዊ ፈተናን መታገል ነው


የክርስትና ሕይወት ትግል ነው፡ በኢየሱስ ለመማረክ ፈቃደኞች እንሁን የሚል ቃል ያማከለ ስብከት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 19 ቀ 2017 ዓ.ም. እንደ ተለመደው በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ነግህ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ማሰማታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ያመለክታሉ።

ቅዱስነታቸው በላቲን ሥርዓት በዕለቱ ከእብራውያን ምዕ. 7 ቁ. 25ና ምዕ. 8 ቁ. 6 እንዲሁም ወንጌል ማርቆስ ምዕ. 3 ከቁ. 7 እስከ 12 የተወሰዱትን ምንባባት ተንተርሰው ፥ ዕለት በዕለት ወደ ተሳሳተው መንገድ የሚመሩን ፈተናዎችና እንዲሁም ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ለመዋለል የሚቃጣውን የክፋት መንፈስ ለመገሰጽ ነው የመጣው። ኢየሱስና ሕዝብ፡ በወንጌል ማርቆስ የተነበበው ላይ በማተኮር ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል መጡ በዚህ ብዙ ሕዝብ ውስጥ ፈውስን የሚሻ፡ ኢየሱስ የሚናገረውን ለማዳመጥ የሚወዱ እርሱን ማዳመጥ ደስታ የሚሰጣቸው ሁሉ ይከተሉታል ምክንያቱን እንደ የሕግ መምህራንና ሊቃውንት በደረቅ መንፈስ ሳይሆን በአቢይ ሥልጣን ቃሉን የሚያሰማ በመሆኑ ነው። ይኽ አይነቱ አነጋገር ደግሞ ልባቸውን ደስ ያሰኝ ነበር። ያ ሕዝብ ማንም ሳይቀሰቅሰው ነጋሪት ሳይነገረው በገዛ ፈቃዱ ነበር ኢየሱስ ይከተል የነበረው፡ አሁን እንደሚደረገው በቅስቀሳ ምክንያት በተሰናዱት አውቶቡስ ወደ ተለያዩ ሕዝባዊ መግለጫዎች የሚያሳፍሩ ሁሉም የተሳታፊነት ቁጥጥር እንደሚኖር በማወቅ ካለ ግል አነሳሽነት መሳተፉን ለማሳወቅ፡ ወዶ ሳይሆን ተገዶ ምናልባትም ከሥራ እንዳይባረር ፈርቶ እንደሚሳተፍ ዓይነት ሳይሆን በገዛ ፈቃዱ ሕዝቡ ኢየሱስን ይከተል ነበር።

እግዚአብሔር አብ ህዝቡ በኢየሱስ እንዲማረክ ያደርጋል

ያ ሕዝብ በውስጡ የሚሰማው ነገር በመኖሩ ኢየሱስን ይከተላል፡  እንዳውም ኢየሱስ የሕዝብ ብዛትና መጨናነቅ አይቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕር ፈቀቅ ይላል። እርሱን ለማየት የጓጉ፡ ምን ያደርግ ይሆን የሚሉ እስቲ እንየው የሚሉ ውሁዳን ተጠራጣሪያንም ነበሩ፡ ሁሉ በኢየሱ ይሳብም ዘንድ የአብ ፈቃድ ነው። ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት እንደ የሕግ ሊቅና መምህር ገታራነት በመላበስን ከሕዝብ እራቅ ብሎ ከሕዝብ ሲለዩ እጃቸውን እንደሚታጠቡ ሳይሆን ለሕዝቡ ተናግሮና ጨብጦም ሁሉንም የታመሙትን እየነካ ያ ሕዝብ እረኛ እንደሌለው እንደ ተቅበዘበዘ መንጋ ወዲያና ወዲህ ሲሉና ሲቅበዘበዙ ባየ ጊዜ እጅግ አዘነ ልቡም በሃዘን ይነካ ነበር። ያ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ እንዲከተል የሚያደርገው የኢየሱስ ተናጋሪነት የኢየሱስ የንግግር ችሎታ ሳይሆን በኢየሱስ የመማረክ ፍላጎት እግዚአብሔር አብ በሕዝቡ ልብ ውስጥ ባኖረው መንፈስ ነው።

የክርስትና ሕይወት ዕለት በዕለት ፈተናን መታገል ነው

የዕለቱ ወንጌል ስለ ብዙ ሕዝብ እና በሕዝቡ ውስጥ ይነቃቃ ስለ ነበረው ሐሴት እንዲሁም እርኩስ መናፍስት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ይጮኹም ነበር። እውነታው እርሱ ነው እያንዳንዳችን በኢየሱስ ፊት ስንገኝና ወደ እርሱ ስንቀርብ የሚሰማን እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው ነው። እርኩሳን መናፍስት ዕለት በዕለት ነው የሚፈታተኑን ሁሌ ቅዳሴ የምታስቀድስ የምትናዘዝም ብትሆን የክርስቲያን ሕይወት ይኸንን ፈተና ዕለት በዕለት መታገል ነው። አለ ፈተና የሚኖር ክርስትያናዊ ሕይወት ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው ለማለ አይቻልም። አለ ፈተና የሚኖ ክርስትና ክርስትና ሳይሆን ርእዮተ ዓለም ወይም ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወትና አምላክም መኖሩ ማወቅ አይቻልም የሚለው ዓይነት አምነት የሚከተል  ይሆናል። እግዚአብሔር አብ ህዝብ በኢየሱስ እንዲማረክ ሲያደርግ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለውም የክርስትና ህይወት ትግል ነው ስለዚህ በውስጥ የሚታገልህ ወደ ኢየሱስ እንዳትል የሚያግድ ፈተና አለ። የክርስትና ሕይወት ትግል ነው።

ኢየሱስ ሰይጣንን ለማጥፋት አጋንንትን የርኩስ መፈስን ለማጥፋት ሕዝብ ለማዳን ነው የመጣው።

እግዚአብሔር ሕዝቡ በኢየሱስ እንዲማረክ ሲያደርግ አይ ሰላሙ አለኝ ያለሁበት ዋስትና አለው ብሎ ባለበት ሥፍራ መቅረትም ይቻላል። ነገር ግን ወደ ፊት ለማለትና ዕለታዊ ፈተና ለማሸነፍ ከተፈለገ በኢየሱስ ለመማረክ መፍቀድ ያስፈልጋል። ለግል ምቾት ወይንም ለማገልገል፡ ለመዝናናት ወይንም ለመጸለይ፡ እግዚአብሔር በማምልከት ለመኖር ነውን ኢየሱስን የምከተለው? የሚለውጥን ጥያቄ አቅርበው ተአምር መጠበቅ ሳይሆን በእርሱ ለመማረክ መፍቀድ ነው በእርሱ መማረክ አቢይ ተአምር ነው። የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት በኢየሱስ የተከበረ ነው። ውስጣችንን ሲያይ ልቡ ይነካል እንዲህ መሆኑ የማላምን ከሆንኩኝ የማመኑ ጸጋ እንዲሰጠኝም መጸለይና ጉልበትን ማጠፍ ይኖብኛል። ወንድሞቼ እንግዲያውስ እያንዳንዳችን ውስጣችንን ልባችንን እንመርምር እግዚአብሔር እውነተኞች ክርስቲያን እንዲያደርገን እንለምነው። በልባችን ውስጥ የሚሆነውን ለመለየት ወደ ኢየሱስ የሚመራን በኢየሱስ እንድንማረክ የሚያደርገው እግዚአብሔር የሚያመላክተውን መንገድ ለይተን እንድናውቅ ያብቃን በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ ጂሶቲ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.