2017-01-19 11:59:00

የቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ በዓል በሮም በሚገኙ የኢትዮጲያ ካቶሊክ ማኅበረሰብ በድምቀት ተከበረ።


በትላንታነው እለት ማለትም በጥር 7/2009 ዓ.ም. በሮም ከተማ የሚገኙ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ የካቶሊክ ምዕመናን በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ እስቲፋኖስ የጸሎት ቤት የመጀመሪያ ሰማዕት የሆነውን የቅዱስ እስቲፋኖስ አመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት አክብረው መዋለቸው ታውቁዋል።  

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

በእዚህ በድመቀት በተከበረው የቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ በዐል ላይ 31 ካህናት እና በርከት ያሉ ምዕመናን ተገኝተው የነበረ ሲሆን የእለቱ መስዋዕተ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወደሰበት ምህለላ ዜማ እና ሽብሸባ ተደርጎ እንደ ነበረም ታውቁዋል። ከምዕለላው እና ከሽብሸባው በመቀጠል መስዋዕተ ቅዳሴ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ይህንንም መስዋዕየት ቅዳሴ በማነኛነት የተመራው በአባ ስዩም ክፍልጊዮርጊስ ሲሆኑ ከእርሳቸው ጋር በሮም የኢትዮጲያ ካቶሊክ ምዕመናን የመድኋኔዓለም ቁምስና ቆመስ የሆኑ አባ ታምሩ አዱኛ እና በሮም የኤርትራ ካቶሊክ ምዕመናን የቅዱስ ቶማስ ቁምስና ቆመስ የሆኑት አባ መሓሪ አብታይ ስርዓተ ቅዳሴውን መርተውታል።

በእለቱ ክቡር አባ ተወልደ ፉጂዬ በአማሪኛ ከቡር አባ ዮናስ ገብረሚካሄል ደግሞ በትግረኛ ቋንቋ ቃለ እግዚኣብሔር አሰምተው የነበረ ሲሆን የእንድብር ሀገረ ስብከት ካህን የሆኑት እና የነገረ መለኮት ቀኖና የሁለተኛ አመት ተማሪ የሆኑት ክቡር አባ ተወልደ ፉጂዬ “ “ በማለት ምዕመናን ማሳሰባቸው ተገልጹዋል። የከረን ሀገረ ስብከት ካህን የሆኑና የሦስተኛ አመት የስነ-ምግባር ነገረ መልኮት ተማሪ የሆኑት የሆኑት ክቡር አባ ዮናስ ገብረሚካሄል በስብከታቸው ክርስቲያኖች ሁሉ እስጢፋኖስን በመምሰል የበደሉንን ሰዎች ሁሉ ይቅር ማለት ይጠበቅብናል በማለት ማሳሰባቸው የታወቀ ሲሆን የምስዋዕተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ ቡኋላ በምዕመናን የተዘጋጀውን የጸበለ ዛዲቅ ሁሉም በጋራ ከተቋደሱ ቡኋላ የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.