2017-01-13 16:50:00

የቅድስት መንበር የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ሐዋርያዊ መሥተዳድራዊ መዋቅሮች ህዳሴ


በኢየሱሳውያን ማኅበር ሥር የሚተዳደረው በሁለት ሳምንት አንዴ የሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው መጽሔት እ.ኤ.አ. ከጥር 14 እስከ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚያወጣው ሕትመቱ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቅርብ ተባባሪዎች የአበይት ሐዋርያዊ ባለ ሥልጣናት ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳን ማኅበራት መዋቅራዊ ሕዳሴ ለማስረጽ አልመው የወጠኑት የሕዳሴ እቅድ እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ጆቫኒ ሳለ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ህዳሴ በሚል ርእስ ሥር ባጠናቀሩት የጥናት ጽሑፍ ሥር ገልጠው፥ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የበላይ ሐዋርያዊ መሥተዳድር መዋቅሮች ማለትም በኩሪያ ሮማና የሚሰባሰቡት መዋቅሮች ሕዳሴ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተካሂዶ በነበረበት ወቅት በተለይ ደግሞ De Ecclesia - ቤተ ክርስቲያን  በሚል ርእስ ሥር ብፁዓን የጉኤው አበው በሁለተኛው ክፍለ ውይይት አካሂደዉበት በነበረው ውሎ፡ የቤተ ክርስቲያን ጠመቃዊ ገጽታው በተመለከተ ሰፊ ንድፍ ያስቀመጡበት መሆኑ በማስታወስ ይኽ ደግሞ ከዚያ በስነ ቤተ ክርስቲያናዊ ጥናት ዘርፍ አዲስ የተጋባው የቤተ ክርስትያናዊነት ሱታፌ አርአያ እርሱም ጉባእያዊነት ከሚለው ሃሳብ ጋር የሚጣለፍ ቢመስልም ቅሉ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ብፁዓን አበው በዚያ ጉባእያውነት በሚለው ሃሳብ ሥር ያንን አቀባዊ ደረግታው (ሃይራርኪካል አቀማመጡን) የሚያጎላውን ጽንሰ ሃሳቡን አልፎ ለመሄድና ይኽ ደግሞ ጉባእያዊነት በሚለው ሐዋርያዊ አሰራር በማሟላት ለማሻሻል መሆኑ አባ ሳለ ባቀረቡት የጥናት ጽሑፍ ያብራራሉ።

በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የብፁዓን ጳጳሳት ሚና ምንድር ነው እንዴትስ መሆን አለበት የሚለው ጥያቄ ሁለተኛው ጉባኤ ቫቲካን በተካሄደበት ወቅት ብቻ ሳይሆን አሁንም ወቅታዊነት ያለው ሆኖ በተለያየ መልኩ የሚቀርብ ነው። እርሱም እያንዳንዱ ብፁዕ አቡን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የቀዳሚነት ሥልጣኑን የቅዱስ ጴጥሮስ የቅርብ ተባባሪዎች ዓበይት ብፁዓን ካርዲንላትና ሊቀ ጳጳሳት ሥር በሚመሩ መዋቅሮች ብፁዓን ጳጳሳሳቱ ላቸውን ሓዋርያዊ ሥልጣን በሱታፌ የሚኖሩ መሆናቸው በተጨባጭ መልኩ በክልላዊት ቤተ ክርስቲያን ጭምር እንደሚገለጥ የሚያሳይ ስርዓት ነው። …. ፡ ሰለዚህ ጠመቃዊና ጉባእያዊነት የተሰኙትን ሁለቱን ጥያቄዎች በሸምጋይነት የሚያስታርቅ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ነው በሚል ውሳኔ ላይ ጸና። እ.ኤ.አ. መሰከረም 15 ቀን 1965 ዓ.ም. ጳውሎስ ስድስተኛ በነበራቸው በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ልዩ ስልጣን አማካኝነት የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እንዲቋቋም አደረጉ። ዓላማውም ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የሚወክሉ በተለያዩ አካባቢ የምትገኘውን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን በመወክል ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣን የቅርብ አማካሪዎች በመሆን  እንዲኖሩት ለማድረግ ነው፡ በዚህ መልኩም የቅዱስ ጴጥሮስ ሥልጣን በሁሉም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲሰርጽ የሚያደርግ ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ የቅርብ ተባባሪዎች የአበይት ባለ ሥልጣናት ብፅዓን ካርዲናሎችና ሊቀ ጳጳሳት ሥር የሚመሩት ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት መዋቅራዊው ህዳሴ ያጋባው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሳይሆን ጳውሎስ ስድስተኛ ናቸው። ምክንያቱም ይኽንን መዋቅር የማደስ ሥልጣን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣን ነው በሚል ግንዛቤ መሰረት የፈጸሙት ህዳሴ ነው። እ.ኤ.አ. ነሐሴ 15 ቀን 1967 ዓ.ም. Regimini ecclesiae universae - የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማሥተዳደር የሥልጣን እካል”  በሚል ርእስ ሥር በሐዋርያዊ ሕገ መንግሥት ሥር እንዲካተት ባደረጉት የሕንግ አንቀጽ ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል። እንዲህ ባለ መልኩም የጳውሎስ ስድስተኛ ህዳሴ እርሱም በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሐዋርያዊ መዋቅር በማጽናት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን በግብራዊነት ሳይሆን በሕግ ለማረጋገጥ መቻላቸው በማመልከት ያ በቅዱስ ጽሐፈት ቤተ ተብሎ ይጠራ በነበረው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ሥር ይመራ የነበረው ሥልጣን ወደ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ስልጣን በማዛወር ያንን ሥልጣን በግብራውነት ሳይሆን በሕግ ደንግገዋል። የጳውሎስ ስድስተኛ ህዳሴ ባጭሩ ይኸንን ይመስላል። በማስከተልም ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መልካም እረኛ በሚል ርእስ ሥር የጳውሎስ ስድሰኛ ህዳሴ ሥር ተመልክቶ እንደሚገኘው የመስተዳድራዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ትኩረት የሚያደርግ እንዲሆን የሚያግዝ እካተው አድሰዉታል።

በዚያ በቅዱስ ዮሓንስ ሥር በሐዋርያዊ ሕገ መንግሥት ሥር የተካተተው የሕግ አንቀጽ ባካተተው አስተዋጽኦ የቅዱስ ጴጥሮስ የቅርብ ተባባሪዎች አበይት ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዶናላትና ሊቀ ጳጳሳት ሥር የሚተዳደሩት ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳት ማኅበራት ማለትም የኵሪያ ሮማና መዋቅሮች ሚና ክንውንና ተግባር ምን መሆኑ ዳግም በጥልቀት ያስታውሳል። “ይኽ ሥልጣን ሰብአዊ ቅዋሜ እንጂ የዚያ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ የሚታመንበት የሐዋርያዊ ሕገ መንግሥት ክትለት አይደለም፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን ሰብአዊ ቅዋሜ ነው። የሰውን ልጅ በበለጠ እንዲተዳደር የሚደግፍ ነው። ይኽ ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ ሐዋርያዊ ሥልጣን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ትልቅ ፍላጎትም ይሕ እላይ የተብራራው ህዳሴ መሆኑ አባ ሳለ በማብራራት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሕዳሴ ምን እንደሚመስልና ምንን የሚያጎላ መሆኑ ያቀረቡት ተንታኝ የጥናት ጽሕፉ አጠቃሏል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.